Saturday, October 26, 2013

እዩና እመኑ፥ መልከ ጸዴቅ ገዳም

                                         source: sodere.com

Thursday, October 17, 2013

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ሲከራከሩና በአንዳንድ ኹኔታዎችም ኤክስፐርቶቹን ሲገሥጹ ውለዋል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ÷ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ÷ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታና ከቀረበው ጽሑፍ እየተነሡ በመረጃ፣ በጥያቄና በትችት ስለ መቻቻል ጽሑፍ ያቀረቡ የሚኒስቴሩን ባለሥልጣናት ፈተና ላይ ጥለዋቸው አምሽተዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳቱ ምስክርነት‹‹የባዕድ እምነት አራማጆች በቤተ ክርስቲያንና በካህናት ላይ ልዩ ልዩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉና ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ታላቅ ድፍረት እንደሚፈጽሙ›› ቀደም ሲል ለአጠቃላይ ጉባኤው የቀረቡ ሪፖርቶችን በገሃድ የሚያጠናክሩና የሚያጸኑ ናቸው፡፡
የሚኒስቴሩ አማካሪዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ቅሬታዎቹ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተደግፈው በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤበኩል ቢቀርቡላቸው መፍትሔ እንደሚሰጧቸው፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተገለጹት በላይ ያልተነገሩ ቅሬታዎች ስለመኖራቸው በየወረዳው ተዘዋውረው መረጃዎችን አሰባስበው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ‹‹ሕግ የተያዙት ጉዳዮች በሕግ እንደተያዙ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ›› ለዚህም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንካሬ አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል፡፡
የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጥያቄ፣ አስተያየትና ትችት በከፍተኛ ጥሞና የተከታተለው የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊ የሞቀ ድጋፉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የውይይት አጀንዳ አጋጣሚውን እንደ ምቹ ኹኔታ ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉትና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የሚመስሉት አቡነ ሳዊሮስ ውይይቱን ሳይጨርሱ አቋርጠው ሲወጡ ታይተዋል፡፡

Sunday, October 13, 2013

ዋልድባን ለማስታወስ

                                         ክፍል ፩


                                         ክፍል ፪

                                         ክፍል ፫

Sunday, October 6, 2013

ዘመነ ጽጌ

ዘመነ ጽጌ አትም ኢሜይል
መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ክረምቱ አልፎ  በጋ ሲተካ ተራውንም ለዘመነ መፀው ሲያስረክብ የመጀመሪያው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ sidet2ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠራር በዘመነ ጽጌ ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚደርሰው ስብሐተ እግዚአብሔር የሚቆመው ማኅሌቱ ደግሞ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይጠራል፡፡ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው ማኅሌተ ጸጌ እየተባለ የሚጠራው መልክ መሰል ድርሰትም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ እየተቃኘ አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜም ይኸው ዘመነ ጽጌ ነው፡፡ ባሉት ሰንበታትና እንዲሁ ወርኀ በማለት ይደርሳል፡፡

ማኅሌተ ጽጌ የተባለው የድርሰት ክፍል እመቤታችንን በጽጌ ማለት በአበባ ልጇን መድኀኔዓለምን በፍሬ እንደገናም እሷንም ልጇንም በአበባና በፍሬ እየመሰለ ልብን በሚመስጥ ምሥጢራት ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገር ድርሰት ሲሆን፤ በውስጡ ስለ ሥላሴ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትና ስለ ቅዱሳን ጻድቃን የሚናገርና ገድላቸውን ትሩፋታቸውን መከራቸውን ከብሉይ ከሐዲስ አስማምቶ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡

Friday, October 4, 2013

ግልጽ ደብዳቤ ለብፁዓን ወቅዱሳን አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ማትያስ፤


ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ/ም
ግልጽ ደብዳቤ
ለብፁዓን ወቅዱሳን አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ማትያስ፤

ግልባጭ፤
ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ፤ ለእግዚአብሔር፤
ለእመቤታችን፤ ለቅድስት ማርያም፤
ለሊቃነ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤልና ለቅዱስ ገብርኤል፤
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናን።

አቤቱታ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ለተጋረጡት ከባድ ችግሮች መፍትሔ አግኙልን!
“ዕርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ እነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ. ም5/9
ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች ሆይ!

በመጀመሪያ፤ ዝቅ ብዬ እጅ በመንሳት፤ መንፈሳዊ ሰላምታዬን በከፍተኛ አክብሮትና ትሕትና አቀርባለሁ።
በመቀጠልም፤ ምንም እንኳ ኢምንት፤ ተራ ምእመን ብሆንም፤ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው ለሚገኙት ከባድ ችግሮች መፍትሔ ሊገኝ የሚችለው፤ በፍጡራን ደረጃ፤ ከሁሉም በላይ፤ ሁለታችሁ ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች፤ በአምላክ በተጣለባችሁ ግዴታና ኃላፊነት፤ ተግባራችሁን ከናንተ በሚጠበቅ ብርታት ስትወጡ መሆኑን ስለማምን ይህንን ግልጽ ደብዳቤ፤ ለሚመለከታቸው ሁሉ ግልባጭ በማድረግ በታላቅ ትሕትና አቅርቤላችኋለሁ። መልሳችሁን በአክብሮት፤ በጥሞናና በጸሎት እጠብቃለሁ።

"ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም" ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

"ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም" ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

 ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዕንቁ  መጽሔት መስከረም 2006 ዓ.ም እትም ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር ‹‹አንድ አድርገን›› ፍሬውን ከላይ ዝርዝሩን ከታች አድርጋ እንዲህ አቅባላችኋለች

·   ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ አመኔታ ያለው የዕምነት ተቋም የለም፤ ጠንካራ እምነቶች ግን አሉ፡፡
· ማኅበረ ቅዱሳን እስከ አሁን ድረስ አክራሪ ሆኖ ያመጣው ነውጥ፣ ያስነሳው ነገር፣ የደበደበው፣ የገደለው ሰው፣ ያቃጠለው ቤተ እምነት የለም፡፡
·  ማኅበረ ቅዱሳንን አክራሪ ለማሰኘት የሚያበቃ ምንም፣ አንድም መከራከሪያ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ ከሳቸውም በፊት የነበሩት ሌሎች ሰዎች እንደ እርሳቸው ብለዋል፡፡
·         ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች ምንጫቸው መታየት አለበት፡፡  ‹‹ቂጣም ከኾነ ይጠፋል፤ ሽልም ከኾነ ይገፋል›› እንደሚባለው በተያዘው ሐቅ መቀጠል ነው
·    ማኅበሩ አንድ የሚጎድለው ነገር ቢኖር ማስረዳት ነው፡፡ መልስ መስጠት እንጂ ቀድሞ የማስረዳት ነገር ውስጥ ብርቱ አይደለም፡፡
·        ‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን ተጠብቃ፣ ሥርዐቷን ይዛ ወደሚቀጥለው ትውልድና ዘመን መሻገር አለባት›› የሚሉትን አካላት ነው አሁን ‹‹አክራሪ›› ማለትና ዝም ማሰኘት ነው የሚፈለገው
·        በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አክራሪነትን ሊያበቅል የሚችል መሬት አይገኝም፡፡