Friday, November 22, 2013

ዜና ፥ ዋልድባና አበሳው


-   ኢሕአዴግ በዋልድባ የመነኮሳትን የእጅ ስልክ ነጠቀ።
-   ኅዳር ፰ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም. የአርባእቱ እንስሳን ባዕለ ክብር ለማክበር ወደ ዋልድባ በመሄድ ላይ የነበሩትን ወጣቶች አሳደደ።  ወጣቶቹም ሸሽተው ሁመራ ገቡ።
-   ኢሕአዴግ ኅዳር ፲፮ ቀን ፪፲፻፮ ዓ.ም. የራሱን መነኮሳትና የራሱን ሰዎች ከትግራይና ከጎነደር በመጥራት ጎንደር ላይ ስብሰባ ለማድረግ እየተሰናዳ ለመሆኑ መረጃ ደርሶናል።  ስብሰባው ሁለት ዓላማ አለው።
o      ፩ኛ - “መነኮሳቱ”  -  “ዋልድባ አልታረሰም፣ ባለፈው ታረሰ ብለን ስለተናገርን አጥፍተናል። ይቅርታ እንጠይቃለን; የልማቱ ተባባሪዎች ነን” የሚል መግለጫ አውጡ በማለት በዜና አውታሮች ለማሰራጨት ሲሆን፥
o      ፪ኛው ዓላማ ደግሞ “ተሰብሳቢዎቹ በፈቃዳቸው ራስ ዳሽንና አካባቢው በትግራይ ክልል ሥር እንዲሆን ተስማሙ” የሚል መግለጫ ለማውጣት እንደሆነ ከደረሱን ምንጮች ለመረዳት ችለናል።
    አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ የኢሕአዴግ አገልጋይ የሆኑ “መነኮሳት” ዓላማውን ለማሳካት መነኮሳትን ለማባበል በመንኮሳት አካባቢ  እያንዣበቡ መሆኑም ታውቋል።

    ዝርዝሩን በቅርቡ እናቀርባለን።


    ይቆየን።

Monday, November 18, 2013

ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።

ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።
ከኃይለሚካኤል፥ ኅዳር ፱ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም.


ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት  ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ አስተዳደር  የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።[1] ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።[2] ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ።  ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር። እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር ግጥም መፎካከር   የዐረቦች ባህል ነበር።[3] እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።


Tuesday, November 12, 2013

ዜግነት ዋጋ ሲያጣ

Friday, November 8, 2013
(PDF):- ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በአረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል? ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አን ይሆን?ትናንት ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችባቸው 5 ዓመታት ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አድርሳለች። ከነዚህ መካከል  በግራዚያኒ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የደረሰው የየካቲት 12 ጭፍጨፋ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በግፍ የተጨፈጨፉት የየካቲት 12 ሰማዕታት በሚዘከሩባቸው ቀናት አንድም ፈረንጅ በአዲስ አበባ መንገድ ዝር አይልም ነበር አሉ። ኢትዮጵያውያን በቁጭት ስለሚወጡ። እንኳን ጣሊያን እና የጣሊያን ዝርያ ያለው ቀርቶ ሌላ ፈረንጅም ቢሆን ይፈራ ነበር። ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ጥቃት ይኼን ያህል ቁጭት ነበራቸው።

Wednesday, November 6, 2013

ዘመቻ ፀረ-ተሃድሶ በደብረ ብርሃን

  • ‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ምዕመንም ሆነ ካህን በሀገረ ስብከቴ እንዲኖር አልፈቅድም››ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም
  • ‹‹አምስት ዓመት ከጣልያን ጋር የተዋጋነው ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለሃይማኖታችን ጭምር ነው›› አባት አርበኛ
  • ‹‹የዘርያቆብ ከተማ ኑፋቄ አይዘራባትም›› የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ካህናት

ኑፋቄ የተገኝበት መጽሐፍ ታገደ


ዳዊት ደስታ
  • መጽሐፉ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ መነኩሴ የጻፉት ነው፡፡

(አንድ አድርገን ጥቅምት 26 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ  ባደረገው ስብሰባ ‹‹ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት›› በመል ርዕስ በዋልድባ ገዳም በሚኖሩት በመ/ር አባ ገ/እግዚአብሔር አብርሃ የተዘጋጀውን ቅጽ አንድና ሁለት መጽሀፍ በሊቃውንት ጉባኤ አስመርምሮ የኑፋቄ ትምህርት ያለበት መሆኑን ስለተረጋገጠ እንዳይራጭና እንዳይሸጥ አገደ፡፡