Friday, December 13, 2013

የሰይጣን ውጊያው እንደቀጠለ ነው!

ዋልድባ
የሰይጣን ውጊያው እንደቀጠለ ነው!
  • ·         ዘራቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩ ካሕናት ተብዪውች ዋልድባን የመታደግ ጥረትን ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው
  • ·         በዋልድባ የቤተ ጣዕመ ክርስቶስ አባቶች ልማት አንቃወምም፥ ገዳሙንም አይነካም በማለት የአዞ እንባ እያነቡ ነው
  • ·         አፍቃሪ መንግሥት (ካድሬዎች) ዋልድባን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት ለመቃወም በየመንደሩ አሉባልታ እየነዙ ይገኛሉ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪካዊውን እና ጥንታዊውን የዋልድባ ገዳም አፍርሶ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደገዳማዊ ገዳማውያን የሚባሉ፣ ነገር ግን ዘራቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩ የበግ ለምድ ለብሰው በጠቦቶች መካከል የሚዘዋወሩ ተኩላዎች፥ ይህንን ታሪካዊ እና ጥንታዊ ገዳም ለመታደግ የሚንቀሳቀሰውን ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በመባል የሚታወቀውን ተቋም የተለያየ አሉባልታ በመንዛት ጥረቱን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል።
ይህ ተቋም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የዋልባ ገዳም አባቶች ላይ የመንግሥት ካድሬዎች የሚያደርሱባቸውን እንግልት፣ በደል፣ እና ስደት አቅም በፈቀደ ለመርዳት ይህ ተቋም ብዙ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ከነዚህም ጥረቶች መካከል ለመጥቀስ ያህል


፩ኛ/ ለአበረንታት መድኅኒዓለም ገዳም ለመርዳት $6000.00
፪ኛ/ ለዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም $3000.00
፫ኛ/ ለሰቋር ኪዳነ ምሕረት የእናቶች ገዳም መርጃ $2500.00
፬ኛ/ አባቶች እና እናቶች ወደጎንደር በተሰደዱ ጊዜ ለእህል ውሃ ማቅመሻ $500.00
፭ኛ/ እናቶች በአዲስ አበባ እርዳታ ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት ለእናቶች መርጃ የተላከ $800.00
፮ኛ/ ለዳልሻሕ ኪዳነ ምሕረት እናቶች ገዳም መርጃ የተላከ $4000.00

በጠቅላላ ለዋልድባ ገዳም የተላከው የገንዘብ መጠን እስከ ዛሬ ድረስ $16,800.00 መላኩን በመረጃዎች የተደገፈ ማስረጃዎች በእጃችን አሉ ነገር ግን እነዚህ ለመንግሥት እና ለቤተክርስቲያን ደብል ኤጀንት ሆነው እየሰሩ የሚገኙ ከሃይማኖታቸው ይበልጥ ለዘራቸው እና ለጎጣቸው አመዝነው በአብዛኛው ጊዜ ይህንን ጥረት ለመቃወም በተለያየ አውደ ምሕረት ላይ የሚናገሯቸው ነገሮች በእጅጉ የእነዚህን ዘረኞች ማንነት ልንመረመምር እና ልናውቃቸው እንደሚገባን ከወዲሁ ለመረዳት ችለናል። እነዚህ ሰዎች በየመንደሩ እየዞሩ፣ በየንሰሐ ልጆቻቸው ቤት በመሄድ እንዲሁም አጋጣሚውን ባገኙት ጊዜ ሁሉ ከሚናገሯቸው ንግግሮች መካከል ለአብነት ለመጥቀስ ያህል:

፩/ ለዋልድባ ገዳም ብላቸው የላካችሁት ገንዘብ ለግንቦት ሰባት መሳሪያ ተገዝቶበታል፣
፪/ ዋልድባ እየታረሰ ነው ብለው የሚያስወሩ ሰዎች የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው (የመንግሥት ተቃዋሚዎች)
፫/ ገንዘባችሁን ዝም ብላችው አታስበሉ (አትስጡ) ለሕዳሴው ግድብ ግን እርዱ . . .
፬/ ለዋልድባ ለመርዳት ከፈለጋችሁ ለእኛ ስጡን እኛ በጣም ታማኞች ነን እንወስድላችኃለን፣
፭/ ቤተክርስቲያን ልማትን ትደግፋለች እንጂ አትቃወምም፣ ስኳር ፋብሪካው ለገዳሙ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም
፮/ ገዳሙ በፖርክ መልክ ቢከለል እኮ ከወርቅ ጫሪዎች እና አዳኞች ገዳሙ ይከለላል፣ ጎብኚዎችም መጥተው ገዳሙን ይጎበኙታል ወዘተ . . .
በማለት ለማደናገር ሲሞክሩ መሰማታቸው በእጅጉ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ እነዚህ ለከርሳቸው እና ለዘራቸው ለጎጣቸው ያደሩ የደፉትን ቆብ እንኳ የማያከብሩ ለሆዳቸው ያደሩ መነኮሳት ነን ባዮች (ስማቸውን ከነፎቶዋቸው፣ እንዲሁም ከነ የድምጽ መረጃዎቹ) በቅሩቡ በቪዲዮ በተደገፈ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን። በያዙት አሉባልታ በመጠመድ መንግሥት እያደረሰ ያለውን ጥፋት የሃገር የወገን ቅርስ የሆኑ ብርቅዬ ቅርሶቻችንን ለአውሮፖ ገበያ እያዋሉ ያሉ እነዚህ ስግብግቦች አሁንም የዚህ ጥፋት ተበባሪ በመሆን እየሰሩ ለመሆናቸው ሁላችንም ልብ ልንለው ይገባል።

እነዚህ የዘር እና በጎጥ የተበተቡ ጎጠኞች እንደቀደሙት አባቶቻቸው ዘጠኝ መለኮት ብለው የሚያምኑ የእምነትም ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ጥቁር እራሶችን ሰብስበው ከመርካቶ በተሸመተ ቆብ ቀሚስ በማልበስ እኛ መነኮሳት የልማት ተቃዋሚሆች አይደለንም፣ ዋልድባ ላይ ስኳር ቢለማ እኛ መነኮሳቱ አሳ እንበላለን በማለት ወትወታቸውን ቀጥለዋል፥ ይልቁንም በአሁን ሰዓት መንግሥት እራሱ እጁን ሳያስገባበት እንደማይቀር የሚያጠራጥረው ዘመቻቸው በቪዲዮ በተደገፈ መረጃ አለን በሚል መልኩ “እኛ የልማት ተቃዋሚዎች አይደለንም” “መንግሥት ያወጣውን የአምስት አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደግፋለን” “ልማቱ ገዳማችንን አይነካም” በማለት ውትወታቸውን ከጀመሩ ውለው አድረዋል። የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት እንደተቋም እነዚህን የእናት ጡት ነካሽ ካሃዲያን ሰምቶ ዝም ማለት ብቻ ሳይሆን የለበሱትን የበግ ለምድ ገፎ እርቃናቸውን ማስቀረት ዋነኛው ተግባራችን መሆኑን እንዲያውቁት ይገባል። በዚህም መሰረት በቅርብ ጊዜ እነዚህ ዘረኞች ሲቀዣብሩ በድምጽ የተቀረፁትን ቃላቸውን በቪዲዮ በተደገፈ መረጃ ለማቅረብ እንወዳለን በዚህም ምዕመናን የእነዚህን ዘረኞች ማንነት አውቆ እና ተገንዝቦ እንዲጠነቀቃቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።

የእነዚህ ጎጠኞች ዋናው ድርሻቸው መንግሥት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ እየፈጸመ ያለውን አሳፋሪ እና አስነዋሪ ተግባር የአዞ እንባ በሚያነቡት መነኮሳት ነን ባዮች ሕዝቡን ማደናገር፣ የመንግሥት ክፉ ገጽታዎች መሸፈን፣ በተቻላቸው መጠን ለዘራቸው (ለጎጣቸው) ታማኝነታቸው ማሳየት በመሆኑ በአገኙት አጋጣሚ ወይም በደረሱበት ቦታ ሁሉ የዚህን ተቋም መልካም ስም እና ምግባር ለማጉደፍ እየተሯሯጡ እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል። የተቋሙ ተወካዮች በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እና ችግር፣ ይልቁንም በገዳማት፣ በአድባራት ብሎም በካሕናት እና መነኮሳት ላይ መንግሥት እያደረሰ ያለውን እንግልት እና ግፍ እንዲያስቆሙ ለመጠየቅ እና ለማሳሰብ የተቋሙ ተወካዮች ቅዱስ ፓትርያሪኩን ለማግኘት በሄዱበት ወቅት ከእነዚህ ዘረኞች መካከል አንደኛው (አባ . .) “የላካችሁት ገንዘብ እኮ ገዳም አልደረሰም” ብለው በደፋሩ አንደበታቸው ሲናገሩ መሰማታቸው በእጅጉ ብዙዎችን አሳዝኗል እኛም የእነዚህን መሰሪ ተኩላዎች ግብራቸውን ገልጸን ማንነታቸውን በመረጃ አሳይተን እንድንጠነቀቃቸው እግረ መንገዳችንን ለማሳሰብ እንወዳለን።
ለዛሬ በዋልድባ ከተላኩት ገንዘቦች መካከል የሁለቱን የመልስ ደብዳቤዎች ከእዚህ መልዕክት ጋር ለአንባቢያን ይፋ አድርገናል ይመልከቷቸው።እግዚአብሔር አምላክ ሃገራችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ከከሃዲያን ይጠብቅልን አሜን

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

1 comment:

  1. btmam ygermal emesu msrat yenebechewe ineant slesehurechte news!! nsha b iguvu yshalachewoal yetetselachewon adera r
    restew lesew mengst siyagonevesu dightegna tre indaymeta wakdba tarese ager ferse !! yemetf tenveet mefepemiye kemehon
    IGEZIABHER ytabuken AMEN!!

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤