Tuesday, December 31, 2013

መለከት ሲነፋ፣ ነጋሪትም ሲጎሰም ከሰማይ ተሰማ።

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔርን አጥብቀው የሚሹት የአባቶቻችን ጸሎት፣ ምሕላ፣ ዝማሬ፣ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዚቅ፥ ማህሌት፣ ወረብ፣ ቅኔ፣ ቅዳሴ የት ደረሰ?  ብርሃን በጨለማ ተከብባ ትቀራለችን? እውነት በኃሰት ተዳፍና ትቀራለችን? እነሆ የአባቶቻችን ጸሎት መሬት ላይ እንደሚቀር ትቢያ እንዳልሆነ ከዚህ በታች ይመልከቱና ይረዱ።  

ከ ፪፲፻፩ ዓ.ም. ጀምሮ ከስማይ መለከት ሲነፋ፣ ነጋሪትም ሲጎሰም ከአፍሪካ በቀር በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው።   በተለይ ከ፪፲፻፭ ዓ.ም. ወዲህ መለከቱና የነጋሪቱ ድምጽ በድግግሞሽ በበርካታ ስፍራዎች በመሰማት ላይ ይገኛል።  በመቶ በሚቆጠሩ ሥፍራወች በሚሰማው በዚህ ደምጽ ብዙ የአውሮፓና የአሜሪካ ሰዎች ሲሸበሩ ይታያሉ። የሳይንስ ሰዎች ደግሞ ሳይንሳዊ ትንታኔ ለመስጠት እየተንገዳገዱ ነው።  


ሻውን ፉሴል የሚባል በቴክሳስ የሚኖር የሙዚቃ መሣሪያዎች ባለሙያ ከብዙ የዓለም አካባቢዎች ከሰማይ ተሰምተው ሰዎች በቪድዮና በድምጽ መቅጃ የቀዷቸውን የመለክትና የነጋሪት ድምጾች ሰብስቦ ባንድ ላይ አጫወታቸው። ባንድ ላይ የሚጫወቱትን ቅጂዎች ቀረብ ብሎ ሲዳምጣቸው ከፍና ዝቅ የሚል ሞገድ ያለው ዜማ እንደሆነ አየና ፓውል ሃግሌይ ለሚባል አንድ የፕሮቴስታንት እምነት ሰባኪ ቀድቶ ሰጠው። ፓውል ሃግሌም ቅጂውን በዩ ትዩብ አሠራጨው።  ሻውን ፉሴልም ይሁን ፓውል ሃግሌይ ይህን ዜማ ሰምተውት አያውቁም።  ከሰማይ የሚሰሙት የመለከትና የነጋሪት ድምጾች በአንድ ላይ ሲሆኑ ይህን ይመስላሉ፥ (ከዚህ በታች የሚታየውን አኣቪዲዮ ይጫኑ)እርስዎስ፡ሰምተውት ያውቃሉን? ሰምተውት፡የማያውቁ ከሆነ ከዚህ፡በታች ያለውን ያሬዳዊ ማህሌት ያዳምጡ። ጌታችን መድኃኒታችን በኢሳይያስ አንደበት የላከልንን ትንቢት አንርሳ።፡እንዲህም አለ፥ 
                                                                                                            
በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት ምድር ወዮላት፥

መልእክተኞችን
 በባሕር ላይ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል!   ፈጣኖች መልእክተኞች  ወደ ረዢምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቆረጡና የተረገጡ ህዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሃገር ይኖራሉ። በየሃገራቸው ይቀመጣሉ። ከተራሮች ራሶችም እንደ ዓላማ ይይዙታል፤ እንደ መለከት ድምፅም ይሰማል። 

እግዚአብሔር፥ "እንደ ቀትር ብርሃን ፥ በአጨዳም ወራት እንደጠል ዳመና በማደሪያየ ጸጥታም ይሆናል" ብሎኛልና። እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቆርጣል።  ጫፎቹንም ይመለምላል፥ ያስወግድማል። ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት  ቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር  አውሬዎችም  ሁሉ ይሰበስቧቸዋል። በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ህዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሃገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ህዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል። 

ምሳሌውንም ከበለስ እንማር፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደቀረበ እናውቃለንና። መለከት እየተነፋ፣ ነጋሪት እየተጎሰመ ጆሮ ዳባ ልበስ አንበል። እንደ ክፉ ሰውም አምላካችን መምጫው ይዘገያል ብለን አናስብ። እድላችን ከግብዞች ጋር እንዳይሆን በደብረ ጽዮን መሰብሰቢያችን  ዛሬውኑ፥ አሁን መሆኑን እንገንዘብ፥ እናድርግም።                                                                                                           የፓውል ሃግሌይን ሁኔታ ይመልከቱ። ድምጹ የሰማይ ኦርኬስትራ ነው ይላል።                                                                           
በቅርቡ ከተሰሙት መለከቶች በተናጠል አንዳንዶቹን እነሆ።እንዲሁም እነሆ፥
በተጨማሪም እነሆ፥
በ፪፲፻፭ ዓ.ም. ከዛ በፊት የነበሩት ከሰማይ የተሰሙ መለከቶች ድምጽና የተ የት ቦታ እንደተሰሙ የሚያሳይ ካርታ ይህን ማገናኛ (ሊንክ) በመጫን ይመልከቱ፥  Trumpets From The Sky

በነቢዩ በኤርምያስም አንደበት እንዲህ ተነገረ፥                                                
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል። የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ አንተንም የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው።
ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ ይወላገዱማል ያብዳሉም።
ከእግዚአብሔርም እጅ ጽዋውን ወሰድሁ፥ እግዚአብሔርም እኔን የሰደደባቸውን አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና መደነቂያ ማፍዋጫም እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ነገሥታትዋንም አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
የግብጽንም ንጉሥ ፈርዖንን ባሪያዎቹንም አለቆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ፥
የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ፥
ኤዶምያስንም፥ ሞዓብንም፥ የአሞንም ልጆች፥
የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፥ በባህር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥
ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ ጠጕራቸውንም የሚቈርጡትን ሁሉ፥
የዓረብ ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድረ በዳ የሚቀመጡ የድብልቅ ሕዝብ ነገሥታትንም ሁሉ፥
የዘምሪ ነገሥታትንም ሁሉ፥ የኤላም ነገሥታትንም ሁሉ፥
የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥ የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፤ የሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።
አንተም። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።
ይጠጡም ዘንድ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ፈጽማችሁ ትጠጣላችሁ በላቸው።
እነሆ፥ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ያለ ቅጣት አትቀሩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ። እግዚአብሔር በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢያተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፥ ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል።
በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዩች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም አይቀበሩምም።
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።
ሽሽትም ከእረኞች ማምለጥም ከመንጋ አውራዎች ይጠፋል።
እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል።
ከእግዚአብሔር ጽኑ ቁጣ የተነሣ የሰላም በረት ፈርሶአል።

እንደ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፤ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው ባድማ ሆናለችና።                                                             ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

1 comment:

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤