Thursday, December 5, 2013

ዜና - ዋልድባ አብረንታንት

ዋልድባ አብረንታንት ዉስጥ በሀይማኖት ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ተነስቶ አብዛኛዉ መነኮሳት እየተሰደዱ ነዉ። ባለፈዉ ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ዋልድባ በነበረ “መነኩሴ” የተጻፈ የኑፋቄ መጽሐፉ ገብያ ላይ እንዳይዉል - እንዳይሸጥ ተብሎ ቢታገድም ገዳሙ ዉስጥ ብጥብጡ እንደቀጠለ ነዉ::  በአሁኑ ሰአት አብዛኛዉ መነኮሳት ወደ በርሀ እየፈለሱ ነዉ። በተለይ ለብዙ ዘመናት በገዳሙ የቆዩ አባቶች እየለቀቁ ነዉ። ያሉተም የቤተ ጣእማን መስቀል በግድ ተሳለሙ እየተባሉ ነዉ። የማይጸብሪ አስተዳደር በሀይማኖት ጣልቃ እየገባ ነዉ።  ህዳር ፳፯ ቀን ፪፲፻፮ .. የማየጸብሪ አስተዳደር ማህበረ መነኮሳቱን ከገዳሙ በመሄድ ይሰበስባል የቤተ ጣዕማን መስቀል አልሳለምም ብሎ የሚበጠብጥ መነኩሴ ካለ ገዳመን መልቀቅ አለበት ብሎ መመሪያ ሰጥቷል።


ሌላዉ በወልቃት ስኳር ፕሮጀክት (ዋልድባ) ምክንያት በሚቀጥለዉ አመት ቤቶችን ስለምናፈርስ በቅርብ ቀን ግምት እንገምታለን ብለዉ ባለስልጣኖቹ ያለፈው እሁድ እለት ለህዝቡ መህርገጽ ቅደስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ቁመዉ ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤