Friday, December 5, 2014

ዛሬም በዋልድባ እሥራቱ እንደቀጠለ ነው “አባት ሆይ ይሄ ሁሉ ግፍና በደል የሚቆመው መቼ ይሆን?"


 • ሁለት ታላላቅ ሊቀ አበው ባለፈው ሳምንት ወደ ማይጸብሪ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ተፈቱ
 • የእነ አባ ገብረ ሕይወት መስፍን ስልታዊ የመንግሥት ተወካይነታቸው ቁልጭ ብሎ ታውቋል
 • ወታደሮች ዛሬም ድረስ በገዳሙ እንደሚገኙ አባቶች ይናገራሉ፣ ምክንያታቸው ግን ምን እንደሆነ አይታወቅም
 • የግድቡ ሥራ ከየትም ሊደርስ ባለመቻሉ የመንግሥት ሰዎች ዓይናቸውን ወደ ሌላ ለማዞር እየሞከሩ ነው
 •  በመስከረም ወር ላይ በችግኝ ማፍያ አካባቢ የተነሳውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በሚል መንግሥት የሚረጨው መድሃኒት በርካታ የወልቃይት አውራጃ ነዋሪዎችን ከብቶች ፍጅቶባቸዋል
 • መንግሥት አሁንም 3900 የሚሆኑ አባወሮችን ከመዘጋ ወልቃይት እንደሚያስነሳ እየተነገረ ነው
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ ነው ከማይጸብሪ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ታጣቂዎች እንደተለመደው ወደ ገዳሙ ዘልቀው በመግባት ሁለት ሊቃነ አበውን ምክንያት በሌለው ነገር እንደ ወንጀለኛ አስረው ወደ ማይጸብሪ አውራጃ ፖሊስ ጣባያ በመውሰድ በእስር ቤት አጉረው ከወንጀለኛ ጋር አሳድረው ለቀዋቸዋል፡፡ በሁኔታው ያዘኑ በርካታ መነኮሳት ምን በድለው ነው? ምን ጥፋት ተገኝቶባቸው ነው? በማለት ቢወተውቱም መልሱ ግን ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው ዓመት ከመንፈቅ በፊት በአቶ ሲሳይ መሬሳ የሚመራው የአውራጃው አስተዳደር በአበንታንት ዋልድባ ገዳም ያለውን የነበረውን የአበውን ትውፊት ወደጎን ብለው፥ በጉልበታቸው እና በሥልጣናቸው የእግዚአብሔርን ቦታ እና ቤተመቅደስ የሚያስተዳድሩትን አባቶች በጉልባቱ መርጦ በማስቀመጥ
1ኛ/ አባ ገብረዋሕድ መምሕር የአበረንታንት መድኃኒዓለም ገዳም አበመኔት
2ኛ/ አባ ገብረሕይወት መስፍን (የቀድሞ ታጋይ) እቃ ቤት አድርጎ ከሾመ በኃላ ነው ችግሮች እየበዙ እና እየጠነከሩ የመጡት። በዚህም መሰረት በተለይ የቀድሞው ታጋይ እያንዳንዷን በገዳሙ ውስጥ የሚደረጉትን እና የሚታሰቡትን በሙሉ በመቅረጸ ድምጽ በተደገፈ ማስረጃ ለመንግሥት በማቀበል፥ በእነሱ አመለካከት “ጸረ ልማት” ወይም “ጸረ ሰላም” ናቸው ብለው የሚሏቸውን መናንያን፣ መነኮሳት እንዲሁም ባሕታውያን ጭምር በፈለጉ ጊዜ ወደ እስር እንዲጋዙ፣ በድብደባ፣ እና ለስደት እንዲዳረጉ ከኃላ ሆነው መመሪያውን እየሰጡ ያሉት እኒሁ በውስጣቸው ተቀምጠው ያሉት ጉዶች እንደሆኑ አባቶች በሐዘን ይናገራሉ። “መድኃኒዓለም ጥዋው የሞላለት . . . ወይውላቸው” ነበር ያሉት አንድ የገዳሙ አባት።

Thursday, October 23, 2014

ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር ይቆጠራል::ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.
ቁጥር : 10102014/0038
                           በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር  ይቆጠራል::
ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችን ሕልውና ዘወትር በትጋት በማገልገል ላይ የሚገኘውን ማኅበረ-ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተካሔደ ያለውን እንቅስቃሴ በመቃወም ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የወጣ መግለጫ
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ:: እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሏቸዋል:: በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል:: ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አይዘገይም:: ፪ኛ ጴጥሮስ  ፪ ፥ ፩ -

Monday, October 13, 2014

የዚህ መንግሥት ባለሥልጣናት ትልቁ ችግር ከታሪክ ጋር መጣላታቸው ነው ፤ ስለተጣሉም ከታሪክ አይማሩም

 መስከረም 28 2007 ዓ.ም
(ወንድወሰን ውቤ)

ሩሳዊያን የሶሻሊስት አብዮትን ተከትሎ ቤተክርስቲያንን አንይ አሉ። ያው እምነት የለሹ ሥርዐት በሩሲያኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የግፍ በትሩን በጭካኔ አሳረፈ። ካህናቱ ተጨፈጨፉ፣ ተሰደዱ። እግዚአብሔርንማመን ወንጀል ሆነ። ብዙ አብያተክርስቲያናት ተዘጉ። በምትካቸው የቦልሸቪክስ ፓርቲ ጽሕፈት ቤቶች ተከፈቱ።በስታሊን እግር የተተካው ክሩሽኔቭ ሞስኮ ውስጥ የሚገኝ አንድን ግዙፍ ካቴድራል እንዲፈርስ ያዛል። አፍራሾቹማፍረሱን ከጉልላቱ ጀመሩት። 

Monday, October 6, 2014

ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!

 • ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡
 • ‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
 • ‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡›› /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ/
*              *             *
 • ‹‹ሚኒስትሩ የመንግሥትን ሴኩላርነት ለማረጋገጥ በሚል የሰጧቸው አስረጅዎች የግልጽነትም የአግባብነትም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚበዛው ኢትዮጵያዊ አማኝ ከመኾኑ አንፃር ትርጉም እንዳለውና በሕገ መንግሥቱ እምነት ነክ ድንጋጌዎች እንደተንጸባረቀ ከሚታመነው የሴኩላሪዝም ፈርጅ (positive secularism) ይልቅ በርእዮትና አሠራር የተደገፈ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን የማዳከም (negative secularism) አዝማሚያዎች ያይልባቸዋል፡፡ ከእምነት ተቋማት ጀርባ የግንባሩን አባላት ጨምሮ ሰፊው አማኝ ሕዝብ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ‘በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር’ እንደሚኖር በመንግሥት የኢንዶክትሪኔሽን ጽሑፎች ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ጋራም የሚጣጣሙ አይደሉም፡፡ በተለይ ከቤተ ክርስቲያናችን አንፃር ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የሚመስል ‘issue’ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ በዚኽ አኳኋን እንዴት ነው ዜጎች ‘ሚዛናዊ አስተሳሰብ’ እንዲያዳብሩ የሚጠበቀው? ከመንግሥት ጋራ አብሮ መሥራትስ እንዴት ይቻላል?››
 • ‹‹ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው ነው፡፡ በሚኒስትሩ የተብራራው የሴኩላሪዝም መርሖ ግን ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ያስመስላል፡፡››
 • ‹‹ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር ስለ መንግሥት የሴኩላሪዝም መርሖ የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾን ያሰጋል፡፡››
/የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች የኾኑ ኦርቶዶክሳውያን የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
*              *             *
Dr shiferaw Teklemariam
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
የክርስቲያንነት መለዮአችን፣ የርትዕት ሃይማኖት ምስክራችን የኾነውን ማዕተብበመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ተቋማት አስሮ ከመታየት ልንከልከል እንደምንችል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው መናገራቸው ተሰማ፡፡
የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖና የፀረ አክራሪነት አጀንዳ ተገን በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ርእዮታዊ እና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን በማስተጋባት የሚታወቁት ሚኒስትር ሺፈራው፣ ይህን መናገራቸው የተጠቆመው፣ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ድረስ በዘለቀውና በኹለት ዙሮች በተካሔደው የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ ነው፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደውና 800 ያህል መካከለኛ አመራሮች በተሳተፉበት የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ግንባታና ፈተናዎቹ›› የሚለውን ሰነድ የሚያብራራና በፓወር ፖይንት የተደገፈ ጽሑፍ ያቀረቡት ሚኒስትሩ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ መነሻ ያደረገ ነው የተባለ ጥያቄ ከአንዲት ተሳታፊ ቀርቦላቸዋል፡፡
እንደ ስብሰባው ምንጮች፣ የተሳታፊዋ ጥያቄ፣ ‹‹በቢሮ ፊታቸውን ተሸፍነው የሚመጡ ሙስሊሞችን አለባበሳቸው ከቦታው አንፃር ያለውን ተገቢነት በማንሣት እንዲያወልቁ ስንጠይቃቸው ‘እኛ ይኼን የምናወልቅ ከኾነ ኦርቶዶክሱም ክሩን ይበጥስ’ ይሉናል፤ ይኼን እንዴት ነው የምንታገለው?›› የሚል ነበር፡፡

ማዕተብ: የክርስትናችን ዓርማ የነፍሳችን ሰንደቅ ዓላማ

 • ሦስት ቀለማት ያላቸው ክሮች የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲኾኑ አንድ ላይ መፈተላቸው ወይም አንድ መኾናቸው ቅድስት ሥላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በመለኰት በህልውና አንድ አምላክ መኾናቸውን ያመለክታል፡፡ ጥቁሩ፡- ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት የሚቀበለው መከራ የሚሸከመው መስቀል፣ ቀዩ፡- በሰማዕትነት ደም የማፍሰስ ሲኾን ቢጫው ደግሞ የክርስቲያን ተስፋ የሃይማኖት ምልክት ነው፡፡
 • ክርስቲያን ለክርስቶስ ታማኝ በመኾኑ በነፍሱ ሞግዚት በቄሱ እጅ ከሕፃንነቱ ጀምሮ የድኅነቱ ምልክት በሚኾን አንገቱ በማዕተበ ክርስትና ይታሰራል፡፡ ማዕተብ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ስለ እኛ ቤዛ ለመኾን የብረት ሀብል /የብረት ገመድ/ በአንገቱ ታስሮ በአይሁድ መጎተቱን ስለሚያስታውሰን ለታማኝነታችንና ለክርስቲያንነታችን ምልክትነቱ ማረጋገጫ ስለኾነ አናፍርበትም፡፡
 • አንዲት ሀገር ነፃና ሉዓላዊ መኾኗ የሚታወቀው ወይም ራሷን የቻለች መንግሥት ያላት ከባዕድ ቀንበር ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣች መኾኗ በቀዳሚነት የሚለየው በባንዴራዋ ምልክትነት እንደኾነ እንደዚኹም አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ በጥምቀት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ነፃ መውጣቱ፣ ነፃነት ያለው አማኝ መኾኑ የሚታወቀው በማተቡ ምልክት ነው፡፡
 • አንዳንድ ሰዎች የማዕተብ ሥርዐትን ለመቃወምና ዘመናውያን መስለው ለመታየት ‹‹እምነት በልብ ነው›› ይላሉ፤ ተሳስተዋል!ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም፤ የጠቅላላው ሕዋሳት ኹሉ ናት፡፡
 • አጋንንት የለከፏቸው ሰዎች ማተብና መስቀል አይወዱም፡፡ የሰፈረባቸው ርኩስ መንፈስ ማተብ እንዲበጥሱ መስቀል እንዲጥሉያደርጋቸዋል፡፡ ማተብ በሰይጣን ዘንድ ከተጠላ በአጋንንት ላለመለከፍ የማዕተቡ መኖር ይጠቅማል ማለት ነው፡፡
* * *
Ethiopian girl wearing a cross shaped tattoo on her forehead
ዕቱባን አንትሙ በቅድስት ጥምቀት
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በአንገታቸው ላይ ክር ያስራሉ፤ ለሕፃኖቻቸውም ክርስትና ሲነሡ ክር ያስሩላቸዋል፡፡ በሕፃናቱም ኾነ በዐዋቂዎቹ ክርስቲያኖች አንገት ላይ የሚታሰረው ክር በግእዝ ማዕተብ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቃሉ የወጣው ዐተበ ካለው ግእዛዊ ግስ ነው፡፡ ዐተበ ፍቺው አመለከተ፣ ባረከ ማለት ነው፤ ማዕተብ ፍቺው ከዚኽ ይወጣል፡፡ ምልክት ማለት ነው፡፡

Saturday, August 2, 2014

እንደሚታረዱ በጎች ሆንን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“. . . ወኮነ ከመ አባግፅ ዘይጠብሁ. . .”
“. . .እንደሚታረዱ በጎች ሆንን . . .” መዝሙር ፵፫

የክርስትና ሃይማኖት በጌታችን በመድኅኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በዕለተ ዐርብ የተመሠረተች፣ በበዓለ ሃምሳ በርዕደተ መንፈስ ቅዱስ ያሸበረቀች እንከን የሌለባት ንጽህት ሃይማኖት ናት። ያለ ክርስትና የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይደለም ወርሶ ሊኖርባት ቀርቶ በዓይኑ እንኳን ሊያያት አይችልም።ዘአተጠምቀ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ አይከል ርዕዮታ ለመንግሥተ እግዚአብሔርዮሐ. በመሆኑም ይህች ሃይማኖት በነፍስ ዘላለማዊ ሕይወት የምናገኝባት፣ ዘላለማዊ ደስታ የምንጎናፀፍባት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንደርስባት በሥጋ ምድራዊ በረከት የምናገኝባት መንገድ ናት።

Wednesday, July 2, 2014

ልዩዋ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጓት ሃያ ስምንት ምክንያቶች።

፩- የተመሠረተችው በሰባኪ ወይም በአሳማኝ ወይም  በአስገዳጅ ወይም ጥሬ ሃብትና መልክዓ ምድርን  በሚሹ ወራሪዎች አይደለም። በመንፈስ ቅዱስ እንጂ።  የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ጥምቀት በቀጥታ ከመንፈስ ቅዱስ የታዘዘ ነው። [የሐዋርያት ሥራ ፰፣ ፳]። ጃንደረባው ጥምቀትን እንደጠየቀ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲጀመር ወደ ቅዱስ ማርቆስ መንበር የላኩ አብርሃና አጽብሃ ናቸው።

፪- አይሁድ የነበረች አንዲት አገር በመንግሥት አዋጅ ክርስቲያን የሆነች አገር ኢትዮጵያ ብቻ ስትሆን ይህን ሽግግር የፈጸመች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናት።

፫- በአዋጅ፣ በእምቢልታና በእልልታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሠ ነገሥቴ ነው ብላ ያወጀች አገር በምድር ላይ ኢትዮጵያ ብቻ ስትሆን ይህን አዋጅ በቤተክርስቲያን ቡራኬ ያጸናች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። 

The Choice One

Twenty eight reasons why the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church is special

1- Its foundation is not from those seeking real-estate and natural recourses, nor is it from preachers and enforcers, but directly from the Holy Spirit [Acts 8:20]. As the Ethiopian Eunuch himself requested baptism so did the kings of Ethiopia Abraha and Atsbaha request for church service and sent for the See of Saint Mark.

2- Ethiopia is the only nation on earth that was Jewish that transitioned to Christianity by official government decree. The Ethiopian Orthodox Tewahdo Church consecrated the decree and carried out the transition.  

3- Ethiopia is the only country on earth that proclaimed Jesus Christ King of Kings over it by official promulgation. The Ethiopian Orthodox Tewahdo Church performed the service to establish it.

Wednesday, June 4, 2014

ዜና ዋልድባ

ግንቦት ፲፬ ቀን ፪፲፻፮ ዓ.ም. ኢሕአዴግ የዋልድባን መነኮሳት በመሰብሰብ ቦታችሁን ልቀቁ፣ ካሳ እንከፍላችኋለን በማለት ካሳን እንደመደለያ አድርጎ አቀረበ። በምንኩስና ስም የኢሕአዴግ አገልጋዮች የሆኑ ሶስት ሰዎች እነሱም፥

፩ኛ- አባ ገብረህይወት የሚባሉ እቃ ጠባቂ (የኢሕአዴግ ታጋይ)
፪ኛ- አባ ኃይለሚካኤል የሚባሉ ለኢሕአዴግ የሚሠሩ
፫ኛ- አባ ፈቃዱ የሚባሉ ቄስ ሆነው ሳለ መነኩሴ ነኝ የሚሉ  

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ሰዎች መሣሪያ በማድረግ የዋልድባን መነኮሳት ለማግባባት ቢሞክርም መነኮሳቱ ቦታው የመድኃኔዓለም እንጂ የኛ አይደለም። የመድኃኔዓለምን ንብረት ካሣ ተቀብለን ልንሸጠው ልንለውጠው አንችልም ብለው በእምነታቸው ጸንተዋል።  ኢሕአዴግ መልሳቸውን ካዳመጠ በኋላ እንቢ ካላችሁ በግድቡ ውኃ ትጥለቀለቃላችሁ በማለት ዝቶባቸዋል።


መድኃኔዓለም የባረከውን ዋልድባን ይጠብቅ። የብጽእት ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ  ዋልድባን ይጠብቅ። የቅዱሳን መላእክት ልመና ዋልድባን ይጠብቅ።  የቅዱሳን ጸሎት ዋልድባን ይጠብቅ። አሜን።

Thursday, May 22, 2014

ፒቲሽኑን በመፈረም በሱዳን የምትገኝ ክርስቲያንን ነፍስ ለማዳን እንረባረብ

 Don't execute 8 months pregnant Mariam Yehya Ibrahim for being Christian #SaveMariamሰሞኑን በተለያየ ድኅረ ገጾች እንደመለከትነው ማርያም ይሄያ ኢብራሂም የተባለች ሱዳናዊት ከክርስቲያን እናት (ኢትዮጵያዊት) እና ከሙስሊም አባት የተወለደች፣ ነገር ግን ሙስሊም አባቷ እሷን እና እናቷን ጥሎ በመሄዱ እናቷ በክርስቲያን ምግባር እና ስርዓት አስተምራ ለቁም ነገር አብቅታ የአንድ ወንድ ልጅ እናት እና የክርስቲያን ሚስት በመሆኗ ብቻ የሱዳን መንግሥት የሞት ፍርድ ፈርዶባታል። ማርያም የስምንት ወር ነፍሰ ጡር በመሆኗ ውሳኔው ወዲያው ባይወሰድባትም ልጇን ከወለደች ከሁለት ዓመት በኃላ የሞት ፍርዱ እንዲፈጸም ወስኗል። ይህች እናት ወይም እህት የዶክተሬት ዲግሪ ያላት ለሃገሯ፣ ለወገኗ ብሎም ለመላው ሕዝብ ብዙ ሥራዎችን ልትሰራ የምትችል መሆኗ እየታመነ፣ ነገር ግን የሱዳን የሙስሊም ሸሪያ ሕግ ክርስቲያን በመሆኗ ብቻ የሞት ፍርድ እና 200 የጅራፍ ግርፋት ተፈርዶባታል። እጅግ የሚያሳዝነው የተከሰሰችበት ክስ እምነቷን በመካድ በሚል ሲሆን ነገር ግን ማርያም ሙስሊም አልነበረችም ያደገችውም በእናቷ በኢትዮጵያዊቷ ክርስቲያናዊ ምግባር ያደገች መሆኗ እየታወቀ ያለምንም ይግባኝ የሞት ፍርድ ተፈርዶባላል። እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው እና ይህችን እህት ነፍሷን ለማዳን የመላው የዓለም ሕብረተሰብ ብዙ ጫና ለማድረግ የሞከረ ነው ስለዚህ እርስዎም በሚከተለው ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ወደ ፒቲሽኑ ገብተው የበኩልዎን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። 

ክርስቲያን እህታችንን ነፍስ ለማዳን ፒቲሽኑን ይፈርሙ 

Sunday, May 11, 2014

መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመስራት ላይ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከቻይና መንግሥት የገንዘብ ብድር አገኝ

መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ 32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ  አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኋላ በሀገሪቱ የተጀመሩት 10 የሥኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገነባው መሆኑ ይታወቃል፡፡  ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከሚቆጣጠራቸው ፕሮጀክቶቹ ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠርና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡  ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው በማንሳት መንግሥት 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መክፈሉ ይታወቃል፡፡ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራውም የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት አብያተ ክርስቲያናት ቅድመ የማግባባት ስራ በአካባቢ አስተዳደር በኩል እንዲሰራ ትዕዛዝ መውረዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡