Thursday, January 30, 2014

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ በደል እና ግፍ ካቶሊክ ቤ/ክ ይቅርታ እንድትጠይቅ!

የካቶሊኩ ጳጳስ ወደ ኢትዮጵያን ለመውጋት የተዘጋጀውን ጦር እና ቦምቡ ሲባርክ
Global Alliance for Ethiopia በመባል የሚታወቅ ማኅበር ነው፣ በዋናነት የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር ቅድስት ሃገራችንን በእብሪተኝነት ወረራ ለማድረግ ሲነሳ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መድፉን ባርከው ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጨፈጭፍ እና ብዙ እልቂት እንዲያደርስ ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው፥ በሃገራችን ኢትዮጵያም ከ60 ሺህ በላይ ንጹሐን ዜጎቻችን እንዲሁም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በግፍ ተመዝብራለች፣ ተቃጥላለች፣ ካህናት ታርደዋል ተረሽነዋል ከነዚህም ካህናት መካከል በዋናነት ሰማዕቱ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ እንዲሁም አቡነ ሚካኤል እና በርካታ መነኮሳት ተረሽነዋል በግፍ ተገለዋል። የካቶሊካዊቱ ቤተክርስቲያን በፈጸመችው አስነዋሪ ተግባር ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ በሚል።

ከዚህ በተጨማሪ በየካቲት ፲፪ ቀን ፲፻፱፵፭ ዓም በርካታ ንጹሐን ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በመርዝ ጭስ የፈጀው የፋሺስቱ መሪ ግራዚያኒ የተመራው የኢጣሊያ ጦር በወቅቱ ጭፍጨፋ ለደረሰባቸው ንጹሐን ዜጎች ካሳ እንዲፍል ለማጠየቅ።
የሚከተለው የpetition ተዘጋጅቷል እና ይህንን በጎ ሀሳብ የምትስማሙ ወጎኖቻችን በሚከተለው ሊንክ በመጠቀም ትፈርሙ ዘንድ በታላቅ ትህትና እንገልጻለን።
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ሃገራችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን።

Petition ለመፈረብ ይህንን ይጫኑ  


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, January 26, 2014

ዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ዋልድባ የእናቶች ማኅበረ ደናግል ገዳም እርዳታ በተደረገላቸው ጊዜ የምስጋና መልዕክት


       

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት የዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት የእናቶች ገዳም ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በተላከላቸው የገንዘብ እርዳታ
በአጠቃላይ እርዳታ $4000.00 (72,500.00 የኢትዮጵያ ብር) ደርሷቸው፥ ለአረጋውያን እናቶች አቅም ላጡ እና ችግሩ በጣም ለጠናባቸው እንዲሁም በአጠቃላይ ለማኅበረ ደናግላኑ በሙሉ የሚከተሉት እቃዎች ተገዝተው ተከፋፍለዋል። በዚህ በክፍል ፪ መልዕክታቸው ዘላቂ ለሆነው ችግራቸው ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ውሃ ማውጫ ወይም ውሃ በቀላሉ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገዶች እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል። እስከ አሁን ለተደረገላቸውም እርዳታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተላከው ገንዘብ የተገዙት:
* 60 ጣቃ አቡጀዲ ለእናቶች ልብስ
* 40 ኩንታል ማሽላ እና ዳጉሳ
ተገዝቶ ለማኅበረ ዳንግል ዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ደርሷል
በቪዲዮው ላይ እንደምትመለከቱት ገዳማውያኑ በአጸፋው ማኅበረ ምዕመናኑን በጸሎታቸው እያሰቡ እና እየተራዱ እንዳሉ ለመገንዘብ ችለናል።
የእናቶቻችን በረከት አይለየን አሜን
IUEOTCFF


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Saturday, January 25, 2014

የዋልድባ ዳልሻሐ ኪዳነምሕረት የእናቶች አንድነት ገዳም ለተደረገላቸው እርዳታ የምስጋና ደብዳቤ


ቀን 7 - 4 - 2006 ..
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን
በደላችንን በሞቱ፣ ሃጢያታችንን በቸርነቱ ያጠፋልን እስከ ሞት ድረስ የወደደን የአበው አምላክ እግዚአብሔር ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የከበረ የተመሰገነ ይሁን አሜን።

ገዳማውያን እናቶች ከተገዛው አቡጀዲ ጋር
ምንጊዜም ሠላምን ጠንነትን ለምንመኝላችሁ የቤተክርስቲያን እና የገዳማትእረዳት ለሆናችሁት የክርስቶስ ቤተሰቦች ለዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ማኅበር በሙሉ ለተከበረው ውድ ጤንነታችሁ እንደምን ከርማችኃል እንደምን አላችሁልን እኛ ገዳማውያን መነኮሳይት ለጤናችን አምላከ አበው ይክበር ይመስገን ደህና ነን።

አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መራባችንን እና መታረዛችንን በመስማታችሁ $4000.00 ዶላር  72,500.00 (ሰባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ልካችሁልን
ገዳማውያን እናቶች ከተገዛው የአቡጀዲ ጋር 

1/ 60 ጣቃ አቡጀዲ (ለአንዱ ጣቃ 550 ብር በመግዛት በአጠቃላይ 60 x 550 = 33,000 (ሠላሳ ሦስት ሺህ ብር) ተገዝቶ መጥቶልን ገዳመ መነኮሳይቱ አንድ ጣቃ አቡጀዲ ለአራት መነኮሳይት ደርሶናል በድምሩ 240 መነኮሳይት አልባሳት አገኝተዋል።

2/ እህሉም ዛሬማ ገበያ ተገዝቶልን 40 ኩንታል ማሽላ እና ዳጉሳ ለአንድ ኩንታል እህል 900 ብር (ዘጠኝ መቶ ብር) በመግዛት 40 x 900 = 36, 000 (ሠላሳ ስድስት ሺህ ብር) በአጠቃላይ እህሉ ሲገዛ በቀሪው ብር በግመል እስከ ገዳሙ ተጭኖ ተረክበናል።