Saturday, February 15, 2014

ጥንታዊው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ተፈታ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የሰሜን ሸዋ /ስብከት ሞረትና ጅሩ ወረዳ የሚገኘው  የመካከለኛው
መቶ ክፍለ ዘመን የደብረ ብሥራት  አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም ተፈትቶ፣ መናንያኑና  መነኰሳቱ መበተናቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ  ገለጹ፡፡
ጥንታዊው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና  ማርቆስ ገዳም ተፈታ ገዳሙ ጨርሶ ሳይጠፋ ጉዳያቸው በሲኖዶሱ እንዲታይ መናንያኑ ጠይቀዋል ጥንታዊውን ገዳም ለመፈታት፣ ማኅበረ  መነኰሳቱንም ለመበተን ያበቃቸው በአካባቢ  ተወላጅነት የገዳሙን መሬት በተለያዩ ጊዜያት  ተቆጣጥረው ለግላቸው ይጠቀሙ ከነበሩ ግለሰቦች  ጋር ተፈጥሮ የቆየውና በተለያዩ ምክንያቶች  እየተካረረ የመጣው አለመግባባት መኾኑን ምንጮቹ  ተናግረዋል፡፡
በኅዳር ወር 2006 . መጀመሪያ ላይ ገዳሙን  ለቀው የወጡት በቁጥር 50 - 80 የሚገመቱ  መነኰሳት፣ መነኰሳዪያትና መናንያን ከተለያዩ  አህጉረ ስብከትና ክልሎች የተሰባሰቡ ሲኾኑ  በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ከአስተዳዳሪነት የተነሡትን  አበምኔቱን / አባ ተክለ ብርሃን ሰሎሞንን  ጨምሮ ከፊሎቹ በአሁኑ ወቅት በደነባ በኣታ  ለማርያም ገዳም ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

Thursday, February 13, 2014

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ባለፈው ቅዳሜ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን በመኖሪያ ቤታቸው አነጋገሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ከተቋቋመ ማግሥት ጀምሮ ለብዙ ጊዜ ሲመኘው እና ሲሰራበት የነበረው እውን ሆኖ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን በመኖሪያ ቤታቸው ለማግኘት በመቻሉ የፈጣሪያችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን።

ቀኑ ቅዳሜ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. (February 8, 2014) ከእኩለ ቀን በኃላ ነበር ስድት የሚሆኑ የማኅበሩ ተወካዮች በሜሪላንድ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ አባታችን መኖሪያ የደረሰው። በወቅቱም ከብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ጋር አቡነ ሳሙኤል እና አቡነ ያዕቆብ አብረዋቸው ነበር የልዑካን ቡድኑን መምጣት እየተጠባበቁ የነበረው፥ የልዑካን ቡድኑ በቦታው እንደደረሱ በመልካም አባታዊ አቀባበል እና ቡራኬ ተቀብለው በመልካም ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ተቀብለው ነበር የተስተናገዱት። ክብር ለመድኅኒዓለም ይሁንና ብፁዓን አባቶች በተገኙበት የልዑካን ቡድኑ የመጣበትን እና ለብፁዓን አባቶች መኅበሩ ከየት ተነሥቶ የት እንደደረስ የተነሳበትን ዓላማ እና ግብ ካስረዳ በኃላ በተለይ በአሁኑ ወቅት በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ያጠላውን የመከራ ድባብ ለማስረዳት ተሞክሯል።

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በሳውዲ ዓረቢያ ለሚንገላቱ ወገኖች የ$2000.00 እርዳታ አደረገ

ለትብብሩ የተደረገው የቼክ ርክክብ
ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፮ . . (February 2, 2014) ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱት እና በጎረቤት የመን ለሚንገላቱት ወገኖቻችን መርጃ እንዲሆን ወገናዊ እና የኢትዮጵያውነት ግዴታውን ለመወጣት ከጥቂት በጎ አድራጊዎች ያሰባሰውን ገንዘብ በጉዳዮ ላይ እየሰሩ ላሉት ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በተወካዮች አማካኝነት የገንዘብ እርዳታውን አበርክቷል።

እርዳታውን ለሁለቱ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በየጽሕፈት ቤታቸው ተገኝተው ያሰረከቡት ተወካዮቻችን እንደገለጹልን፣ ቅዳሜ

የIUEOTCFF ተወካዮች ከትብሩ ሃላፊዎች ጋር
ጥር ፳፭ ቀን Global Allieance for Ethiopians ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን በመባል ለተቋቋመው ድርጅት $1000.00 እርዳታውን የተቀበሉት አርቲስት ታማኝ በየነ የትብብሩ ተቀዳሚ ሰብሳቢ እና / ማርታ የትብብሩ ገንዘብ ያዥ ሲሆኑ፥ በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ አርቲስት ታማኝ እንደተናገሩት ይህንን እርዳታ ስንቀበል በደስታ ነው በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነታችንን በማንኛውም መስክ ተባብረን ወገኖቻችንን ከሚደርስባቸው በደል ለመታደግ የዚህኛው ወይም የዛኛው ወገን ሳንባባል መድረሳችን ያስመሰግነናል በታሪክም ከወቀሳ እንድናለን በማለት ተናግረዋል። በመጨረሻም ለወገን መድረስ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወገን በተለያየ የዓለማችን ክፍል ብዙ እንግልት እና ሐፍረት ሲደርስበት እኛ በዚህ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ወገኖች በተሻለ ቦታ እንደመኖራችን መጠን የወገን አለኝታነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ በማለት ሥነ ስርዓቱ ተፈጽሟል።

Sunday, February 2, 2014

በጥንታዊው እና ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ፈረንሳዊው የታሪክ ተመራማሪ ፊልም ሊሰራ ነው


ፈረንሳዊው ፍራንሷ ለዶክተሬት ትምርቱ ጥናት ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ባደረገበት ጊዜ ነበር ዋልድባን ትግራይን እና የሰሜኑን ሃገራችንን ክፍል ለመጎብኘት እድሉን ያጋጠመው። በመቀጠልም በዋልድባ ገዳም በመሄድ ከአባቶች ጋር በመግባባት እና የአካባቢውን ሁኔታ በመመልከት በበለጠ ስለቦታው ለማወቅ ጉጉት ያደረበት። ያንንም ያየውን እና የተገነዘበውን ለተቀረው ዓለም ለማሳወቅ የወሰነው ከዚህም የተነሳ በአሁኑ ሰዓት ጥናታዊውን ፊልም ለማዘጋጀት እላይ እታች እያለ ባለበት ወቅት ነበር የዶቼ ዌሌ ዘጋቢ ስለሁኔታው ዝርዝር ለአድማጮች ያዘጋጁት። እንከታተለው

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!