ለትብብሩ የተደረገው የቼክ ርክክብ |
ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.
ም. (February 2, 2014) ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱት እና በጎረቤት የመን ለሚንገላቱት ወገኖቻችን መርጃ እንዲሆን ወገናዊ እና የኢትዮጵያውነት ግዴታውን ለመወጣት ከጥቂት በጎ አድራጊዎች ያሰባሰውን ገንዘብ በጉዳዮ ላይ እየሰሩ ላሉት ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በተወካዮች አማካኝነት የገንዘብ እርዳታውን አበርክቷል።
እርዳታውን ለሁለቱ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በየጽሕፈት ቤታቸው ተገኝተው ያሰረከቡት ተወካዮቻችን እንደገለጹልን፣ ቅዳሜ
የIUEOTCFF ተወካዮች ከትብሩ ሃላፊዎች ጋር |
ለገዳመ ተክለሃይማኖት ቼኩን ሲያስረክቡ |
በመቀጠል እሁድ ጥር ፳፮ ቀን በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስተ ማርያም በመገኘት ለገዳመ ተክለሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የወገን ደራሽ ንዑስ ኮሚቴ እርዳታውን የተቀበሉት ሊቀ መምዕራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሣዬ ሲሆኑ የ$1000.00
እርዳታ ለወገን ደራሽነታሁን በእውነት ያሳያል በማለት አባታዊ ምክራቸውን እና ቡራኬያቸዋል። ሊቀ መምዕራን ሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆቿ
የIUEOTCFF ተወካዮች ከሊቀ መምዕራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ጋር |
በመጨረሻም፣ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ባለው የተለያየ ፈተና፣ ለመራዳት በዋልድባ ገዳማውያን ላይ ያለውን ችግር በመጠኑ ለመቅረፍ እያደረገ ያለውን አቅፍ በፈቀደ የሚደረገውን ጥረት እና እርዳታ በተጨማሪ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መድረስ ዋነኛው ሃገርኛ ጉዳይ እና ሃይማኖታዊ ምግባር ነው በማለት እንደመርህ የሚቻለውን ያህል ጥረት በማድረግ ከዕለት ጉርሳቸው፣ የተለያየ ችግሮቻቸው ሳያሰቅቃቸው፣ ለረዱን ለተባበሩን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ አምላከ ቅዱሳን ሁልጊዜም የልባችንን መሻት ከሃጢያት በስተቀር ይስጥልን ሥራችሁን ሁሉ ይባርክላችሁ በማለን ልባዊ ምስጋናችንን በማኅበሩ ስም እናቀርባለን።
የአበው በረከት አይለየን እንላለን
ከዝግጅት ክፍሉ
IUEOTCFF
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤