Friday, December 5, 2014

ዛሬም በዋልድባ እሥራቱ እንደቀጠለ ነው “አባት ሆይ ይሄ ሁሉ ግፍና በደል የሚቆመው መቼ ይሆን?"


  • ሁለት ታላላቅ ሊቀ አበው ባለፈው ሳምንት ወደ ማይጸብሪ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ተፈቱ
  • የእነ አባ ገብረ ሕይወት መስፍን ስልታዊ የመንግሥት ተወካይነታቸው ቁልጭ ብሎ ታውቋል
  • ወታደሮች ዛሬም ድረስ በገዳሙ እንደሚገኙ አባቶች ይናገራሉ፣ ምክንያታቸው ግን ምን እንደሆነ አይታወቅም
  • የግድቡ ሥራ ከየትም ሊደርስ ባለመቻሉ የመንግሥት ሰዎች ዓይናቸውን ወደ ሌላ ለማዞር እየሞከሩ ነው
  •  በመስከረም ወር ላይ በችግኝ ማፍያ አካባቢ የተነሳውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በሚል መንግሥት የሚረጨው መድሃኒት በርካታ የወልቃይት አውራጃ ነዋሪዎችን ከብቶች ፍጅቶባቸዋል
  • መንግሥት አሁንም 3900 የሚሆኑ አባወሮችን ከመዘጋ ወልቃይት እንደሚያስነሳ እየተነገረ ነው
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ ነው ከማይጸብሪ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ታጣቂዎች እንደተለመደው ወደ ገዳሙ ዘልቀው በመግባት ሁለት ሊቃነ አበውን ምክንያት በሌለው ነገር እንደ ወንጀለኛ አስረው ወደ ማይጸብሪ አውራጃ ፖሊስ ጣባያ በመውሰድ በእስር ቤት አጉረው ከወንጀለኛ ጋር አሳድረው ለቀዋቸዋል፡፡ በሁኔታው ያዘኑ በርካታ መነኮሳት ምን በድለው ነው? ምን ጥፋት ተገኝቶባቸው ነው? በማለት ቢወተውቱም መልሱ ግን ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው ዓመት ከመንፈቅ በፊት በአቶ ሲሳይ መሬሳ የሚመራው የአውራጃው አስተዳደር በአበንታንት ዋልድባ ገዳም ያለውን የነበረውን የአበውን ትውፊት ወደጎን ብለው፥ በጉልበታቸው እና በሥልጣናቸው የእግዚአብሔርን ቦታ እና ቤተመቅደስ የሚያስተዳድሩትን አባቶች በጉልባቱ መርጦ በማስቀመጥ
1ኛ/ አባ ገብረዋሕድ መምሕር የአበረንታንት መድኃኒዓለም ገዳም አበመኔት
2ኛ/ አባ ገብረሕይወት መስፍን (የቀድሞ ታጋይ) እቃ ቤት አድርጎ ከሾመ በኃላ ነው ችግሮች እየበዙ እና እየጠነከሩ የመጡት። በዚህም መሰረት በተለይ የቀድሞው ታጋይ እያንዳንዷን በገዳሙ ውስጥ የሚደረጉትን እና የሚታሰቡትን በሙሉ በመቅረጸ ድምጽ በተደገፈ ማስረጃ ለመንግሥት በማቀበል፥ በእነሱ አመለካከት “ጸረ ልማት” ወይም “ጸረ ሰላም” ናቸው ብለው የሚሏቸውን መናንያን፣ መነኮሳት እንዲሁም ባሕታውያን ጭምር በፈለጉ ጊዜ ወደ እስር እንዲጋዙ፣ በድብደባ፣ እና ለስደት እንዲዳረጉ ከኃላ ሆነው መመሪያውን እየሰጡ ያሉት እኒሁ በውስጣቸው ተቀምጠው ያሉት ጉዶች እንደሆኑ አባቶች በሐዘን ይናገራሉ። “መድኃኒዓለም ጥዋው የሞላለት . . . ወይውላቸው” ነበር ያሉት አንድ የገዳሙ አባት።