Thursday, November 26, 2015

የእርዳታ ጥሪ ለጠጣ መድኅኒዓለም የአንድነት ገዳም ሰሜን ጎንደር

                           
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ከሚገኘው የጠጣ መድኅኒዓለም የአንድነት ገዳም አንድ ጥሪ ደረሰን፣ ጥሪውም በገዳሙ ተወስነው የሚኖሩ አበው እንዲሁም እናቶች እራሳቸው ችለው በተለያየ ጊዜ ምዕመናን ከምናስቸግር በማለት አንድ ሥራ ለመሥራት በአካባቢው ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ጥናት ተደርጎ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለማቆም እና ከዚህ የሚገኘው ገቢ ለገዳሙ እለት ተዕለት ለሚደርሰው ውዳሴ አምላክ ለአገልግሎት ማስፈጸሚያ እጣን፣ ጧፍ እንዲሁም የተለያዩ አልባሳትን ለማሟላት ጥረት የሚያደርጉበት በመሆኑ የዝግጅት ክፍላክችም ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ለመርዳት እና የበረከቱ ተካፋይ ለመሆኑ የሚያስቡ ምዕመናን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ይህንን ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን እንድናሳስብላቸው ባደረሱልም መልዕክት ገልጸውልናል፥ እኛም የጉዳዩ ባለቤት ምዕመናን ናቸውና ጉዳዩን በቀጥታ ለባለጉዳዩ በማለት ለእናንተ በሚከተለው መንገድ አቅርበነዋል ተከታተሉት፡፡

Wednesday, November 18, 2015

በአቃቂ ቃሊቲ: ለ52 ዓመታት ያገለገለው የባሕረ ጥምቀት ቦታ ለመናፈሻ በሚል ቀንና ሌሊት እየተቆፈረ ነው

 • “ክ/ከተማው ቦታው አይነካባችኹም ብሎ አዘናግቶናል፤ ለሌላ ዓላማ መዋሉ አሳዝኖናል” /ምእመናን/
 • “ለሌላ ዓላማ ሳይውል አጥቢያዎቹ በዕቅዳቸው እንዲያለሙት አመራር ይሰጥላቸው” /ቅ/ሲኖዶስ/
 • “ልማቱ በዓለ ጥምቀቱን ታሳቢ ያደረገ ነው፤ ቦታው በታቦት ማደርያነቱ ይቀጥላል” /ክ/ከተማው/
Akaki Kaliti Bahire Timket
ባሕረ ጥምቀቱን የሚያስከብር የልማት ፕሮጀክት ለማከናወን ከማንም በፊት ዐቅደን ፈቃድ እየጠየቅን ባለንበት፣ መናፈሻ 
ይሠራል በሚል የተሰጠው ሌላ አካል ፓውዛ ተክሎ፣ ኤክስካቫተር አስገብቶና የሰው ኃይል ጨምሮ ቀንና ሌሊት እየቆፈረና ከአርባ 
ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ዛፎች እያወደመ ይገኛል፤ ይህም ሕዝቡንና ቤተ ክርስቲያንን አሳዝኗል፤” /የምእመናኑ ኮሚቴ/
(አዲስ አድማስ፤ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ቅዳሜ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)
ላለፉት 52 ዓመታት በበዓለ ጥምቀት ማክበርያነት እና በታቦት ማደርያነት ሲያገለግል የነበረው የባሕረ ጥምቀት ቦታ ለሌላ አገልግሎት መዋሉ እንዳሳዘናቸው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዘጠኙ አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ምእመናን ገለጹ፡፡

Thursday, October 29, 2015

ቅ/ሲኖዶስ: የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴው በቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰነ፤ አደረጃጀቱ ከጠቅ/ቤተ ክህነት እስከ አህጉረ ስብከት ይወርዳል

 • የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በትምህርት ይከላከላል፤ ማስረጃዎችን እያቀረበ ያጋልጣል
 • የጠቅ/ቤተ ክህነቱ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ይመራል
 • ቋሚ ኮሚቴው፣ ከሰርጎ ገቦች የጸዳና አባላቱም በሃይማኖታቸው እንከን የሌላቸው ሊኾኑ ይገባል
South and West A.A Archbishop
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፤የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊ እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ መጠበቅ እና ማስጠበቅ፤ አገልግሎቷ እና አስተዳደሯ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲመራ የማድረግ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ÷ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለመከላከል እና ለማጋለጥ በመካሔድ ላይ የሚገኘው ኹለ አድማሳዊ ተጋድሎ እና እንቅስቃሴ፣ በቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰነ፡፡
ቋሚ ኮሚቴው÷ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት እና ክርስቲያናዊ ትውፊት በመበረዝ እና አስተዳደራዊ አንድነቷን በማናጋት ለመከፋፈል አልያም ባለችበት አዳክሞ ለመውረስ ወደ መዋቅሯ ሰርገው የገቡትን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችንና የዋነኛ አዝማቾቻቸውን ሤራ በማስረጃ የማጋለጥ እና በትምህርት የመከላከል ተልእኮ የተሰጠው ሲኾን ዓላማውን የሚያስፈጽምበት መዋቅርም በዘላቂነት እንዲዘረጋ ነው የተወሰነው፡፡

ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል

 • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ እና ዕውቅና የሌላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ ታዖሎጎስ እናቃለ ዐዋዲ  በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ በስም ተለይተው ተጠቅሰዋል
 • በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት፣ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየብዙኃን መገናኛ ቦርድ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው
 • በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የበለጠ ተጠናክረው አጀንዳው በልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ተወስኗል
synod tik2008 Edited
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከማእከል የተሰጠ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(EBS) የቴሌቭዥን ጣቢያ“ሃይማኖታዊ ትምህርት” የሚያስተላልፉ ፕሮግራሞች፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም እንዳይጠቀሙ ወሰነ፡፡
ምልአተ ጉባኤው በዛሬ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን፤ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረግ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
በውሳኔው÷ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ “ታዖሎጎስ” እና ቃለ ዐዋዲ”  በስም የተጠቀሱ ሲኾን በፕሮግራሞቹ አዘጋጅነት የሚታወቁት በተለይ የ“ታዖሎጎስ” ግንባር ቀደም ምንደኞች፣ ፕሮግራማቸው“ራሱን የቻለ የሚዲያ ተቋም” እንጂ  ከቅዱስ ሲኖዶሱ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጋር ተቋማዊ ግንኙነት እንደሌላቸው በይፋ በሰጡት መግለጫ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

Saturday, October 3, 2015

በዋልድባ ዳልሻሐ የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክስቲያን ማሰሪያ እርዳታ


 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

በጥንታዊነቱ የሚታወቀውና ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የሚሄዱ መናንያን ተሰባስበው ለዓለም ሠላም፥ ለሰው ልጆች ደህንነት፥ ሠላምና ፍቅር አምላክን የሚማጸኑበት ከዋልድባ ዳልሻሕ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ውስጥ የሚቀኘው የሊቀሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታሪክና አመሠራረት ለግንዛቤ ያህል ከዚህ በታች ተመልክቷል።

ይህ የተጠቀሰው የፍድቃ ሊቀሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተመሠረተው በንጉሱ በሣልሳዊ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ሲሆን አባቶች የጸለዩበት እና ሰማዕትነት የተቀበሉበት እስከ 65 ዐበመኔት ወይም መምህራን በገዳሙ ሕግና ሥርዓት አበው ለብቃት የደረሱበት፤ ከብቃታቸውም የተነሳ፦

Friday, September 11, 2015

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገረን ፪፻፰ ዓ.ም.

መልካም አዲስ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም


እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገረን
ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እንዲሁም የንሰሃ ዘመን እንዲሆንልን እየተመኘን መለያየትን፣ጠብን እና ክርክርን አስወግደን ለሃገራችን፣ ለቤተክርስቲያናችን ብሎም ለወገናችን መልካሙን ሥራ ሰርተን በታሪክ እና በትውልድ እንድንታሰብ ከወቀሳም እንድንድን አደራ እንላለን።
አዲሱ ዓመት የአዲስ ማንነት ምዕራፍ ይሁንልን፣ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የቤተክርስቲያን ልጆች ፍቅርን እና አንድነትን፣ አንድ ልብ እና አንድ መንፈስን ይስጠን መለያየትን አስወግደን ስለአንዲት ሃገር፣ ስለአንዲት ንጹህ ጥርጥር ስለሌለባት ተዋሕዶ ሃይማኖታችን እምናስብበት እና እምንጋደልበት እድሜውን እና ጤንነቱን ይስጠን፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ ያዳነንን መድኅኒዓለም ክርስቶስ በልባችን ተስሎ የምንኖርበት ዓመት ያድርግልን አሜን።

የወላዲተ አምላክ ምልጃና ጸሎት፣
የቅዱሳኑ በረከት፣ የአባቶቻችን ጥርጥር የሌለበት ንፁህ እምነታቸው እና በረከታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት

IUEOTCFF
ከባሕረ ሃሳብ የተወሰደ የዘመን መቁጠሪያችን 


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Friday, August 28, 2015

የሊቢያው ሰማዕት አወቀ ገመቹ ቤተሰቦች ተጎበኙ

ታላቅ ወንድም ቶሎሳ ገመቹ መንገድ መሪያችን ነበር ።

የአወቀ ወላጅ አባትና ሀዘን ያደቀቃቸው ወላጅ እናቱ በቀዬአቸው ።

ወላጆች በቅርብና ከአጠገባቸው ካሉት ቀሪ ልጆቻቸው ጋር ።

ከቤተ ዘመድና ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ።

ሟች አወቀ ገመቹ ይህ ነበር ።

የእናት ልቅሶ ብዙ ለማውራት አልተመቸንም ነበር ። ምክንያቱም የእናት አንጀት ነዋ ።

የዋዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉልኝ ከፍተኛ ትብብር ለሰማዕቱ አወቀ አባት ለአቶ ገመቹ በእኔ በኩል የተላከውን 49760 ብር የባንክ ደብተር በስማቸው አውጥቼ አስረክቤያለሁ ።


ወደ ሊቢያ ሂዶ በግፈኛው ISIS እጅ ከመውደቁ በፊት አወቀ ገመቹ በካርቱም የተነሳው ፎቶና ከመገደሉ በፊት የተገኘው ምስሉ ።
ይህንን ጽሁፍ ከመምህር ዘመድኩን የፌስ ቡክ ፔጅ ሲሆን መምህር ዘመድኩን በተለይ በሊቢያ ከተሰውት ሰማዕታት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መሰዋት በኃላ በፍጹም ቅንዓት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትን በማፈላለግ ለቤተሰቦቻቸው መጽናኛ የሚሆን መጠነኛ እርዳታ ከተለያዩ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰበውን ሲያደርስ፥ ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች መጽናኛ ሲሆን ተመልክተናል በእውነት ይሄ ነው ኦርቶዶክሳዊነት ብሎም ኢትዮጵያዊነት፤ ወገን ለወገኑ ሲደርስ እነዚህ በእውነት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጨካኝ ከይሲዎች ጧሪ ቀባሪ የሚሆን ልጅን ሲቀማ ብግፍ ሲያርድ በእጅጉ ያሳዝናል አለሁ የሚል ወገን የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ አለሁ በማለት ሃገር አቋርጦ በመሄድ ወገኖቹን ኢትዮጵያውያንን በመደገፉ ብእውነት ሊመሰገን የሚገባው ወንድም እንደሆነ ከማናችንም የተሰወረ እውነታ አይደለም
ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም በእንዲህ ዓይነት የተቀደሰ ተግባር ላይ የየግል ተሳትፏችንን እንድናደርግ የዝግጅት ክፍላችን በአጽንዖት ያስገነዝባል፤ እኛም ጽሁፉን በቀጥታ ከመምህር ዘመድኩን ገጽ በመውሰድ ለአንባቢያን እንዲደርስ በማሰብ እንደሚከተለው አቅርበነዋል መልካም ምንባብ . . .

Thursday, August 20, 2015

እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሰን

  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ተራራ በገለጸበት ጊዜ

  ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ የኛማ ጌታ የአለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
  ትኁት መሐሪ በደረ ታቦር የተገለጸው
  ፊቱ እንደ ጸሐይ በርቶ የታየው
  የድንግል ማርያም አንዱ ልጇ ነው...
  ድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና [2]
  የቡሄው ብርሃን ለእኛም አበራልን
  ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
  አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
  አባትም አለ ልጄን ስሙት
  ቃሌ ነውና የወለድኩት
  ኪዳነ ምህረት [2]
  ባርኮ የሰጠሽ ኢትዮጵያን አስራት
  ጭንቀት ይርቃል ይቀርባል ሰላም
  ስሟ ሲጠራ የድንግል ማርያም
  በተዋሃዶ ወልድ የከበረውTuesday, July 7, 2015

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በ፴፪ኛው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ በዓል ተሳትፎ አደረገ

ከሰኔ ፳፩ እስከ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓም በተደረው የESFNA ፴፪ ኛ ዓመታዊ በዓል ላይ ተሳተፈ
በበዓሉ ላይ IUEOTCFF በርካታ ሥራዎችን ለኢትዮጵያውያን በማቅረብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሞክሯል
በዚሁ በዓል መጠናቀቂያ ላይ IUEOTCFF ትልቅ ጉባኤ በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ አዘጋጅቶ ለምዕማናን በገዳሙ ላይ እየደረሰ ያለውን እና በገዳሙ አካባቢ የደረሰውን ተዓምራት ለምዕመናን ተገልጿል
ይሄንኑ የESFNA በዓል ተከትሎ የማኅበሩ አጠቃላይ ጉባኤ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን አድርጎ የውሳኔ ሃሳቦችን አስተላልፏል

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ከተመሠረተበት ሦስት ዓመታት ከግማሽ ጀምሮ ጉባኤ ዘርግቶ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን በማዛጋጀት ለትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ የዓለም ማኅበረሰብ የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት፣ ለዓለም ማኅበረሰብ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል በመገናኘት ገለጻዎችን በማድረግ ብሎም በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመገኘት እየደረሰ ያለውን ጥፋት እና እንግልት ለኢትዮጵያውያን ሲያስገነዝብ እና የእምነቱ ተከታዮችን አለኝታነታቸው እንዲያሳዩ ሲያሳስብ መረጃዎችን ሲያደርስ ቆይቷል። አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ሰሜን አሜሪካ ፴፪ኛው ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት ለምዕመናን እንዲሁም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያን በዋልድባ ገዳም ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስውር ደባ፣ በምዕመናን ላይ እየተፈጠረ ያለውን ውዥንብር ለኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘዴዎች ለማድረስ ጥረት ተደርጓል፤ ከነዚህም መካከል

Wednesday, June 17, 2015

ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ( July 5, 2015) ከ 2:00 - 7:00 pm.


ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
“. . . እግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኽታቸው ናቸውና. . . “
መዝሙር ፴፬ ፥ ፲፭
የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት
ሰማዕትነት በ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
በሚል ርዕስ ሃይማኖታዊ ትምርት እና የውይይት ርኃግብር ተዘጋጅቷል፥ በመርኃግብሩ ላይ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ካታ ካህናት አባቶች እና ሰባኪያነ ወንጌል ተገኝተው መንፈሣዊ ትምህርት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። ከዚህም በተጨማሪ ትምርታዊ መንፈሣዊ ጭውውት እና ያሬዳዊ ዝማሬም በዲሲና አካባቢ በሚገኙ የሰንበት /ቤት አባላት ይቀርባል። በመሆኑም እርሶም በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት ዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ እንዲታደ ከታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

         ቀኑና ሰዓቱ
ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፯ .. July 5, 2015
                                ከ2:00 PM - 7:00 PM.                                                

  አድራሻው
Howard University West Ballroom 
2397 Sixth Street, NW. 
Washington, DC 20059                     በበለጠ ለመረዳት 702-576-8323 ወይም 703-307-9478 ወይም 571-299-0975 ደውለው ይጠይቁን
              
                     
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን በረደኤት ይጠብቅልን አሜን
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነተ ተከታዮች አንድነት
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, June 14, 2015

Saturday, June 6, 2015

“የድረሱልኝ ጥሪ” ያሰሙት የስልጤ ዞን ቂልጦ ቅድስት ማርያም ምእመናን “ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” ተብለው ፍርድ ቤት ቀረቡ

 • ፳፩ የምርመራ ቀናት የጠየቀባቸው የወረዳው ፖሊስ የ፲ ቀን ጊዜ ተፈቅዶለታል
 • በድረሱልኝ ጥሪው÷ ከሥራቸው የታገዱ፣ ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ እና የታሰሩ አሉ
 • የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና ምእመናኑ ከወረዳው አስተዳደር ጋር እየተነጋገሩበት ነው
 • በተቃጠለው የቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው መቃኞ ሰኔ ፳፩ ይመረቃል
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 15 ቁጥር 803፤ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.)
silte-kilto-orthodox-christians-plightበደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት “ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋል” በሚል ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የወረዳው ፖሊስ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ እና በዚኽ ሳምንት ሰኞ ስድስት የሰበካ ጉባኤውን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ሥር በማዋል በቂልጦ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል፡፡
ምእመናኑ፣ “የድረሱልኝ ጥሪ” በሚል “ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ጽሑፍ ጽፈው በፌስቡክ አሰራጭተዋል” ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ የሰበካ ጉባኤው ሊቃነ መናብርት “የድረሱልኝ ጥሪ” በሚል ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢያምኑም በፌስቡክ አለመልቀቃቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ምእመናን ላይ የማጣራው ነገር አለ በሚል የኻያ አንድ ቀን የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ቢኾንም ፍርድ ቤቱ የዐሥር ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለታል፡፡

Sunday, May 31, 2015

የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅድስት ሃና ወቅዱስ ዑራኤል ገቢረ ተዓምራት

የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅስት ሐና ወቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው ፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስሐንስ የቅዱስ ዑራኤል፣ እና የእናታችን የቅድስት ሐና ቤተክርስቲያን ጸበል ለመባረክ ከመበረ ክብራቸው ተነስተው የግንቦት ልደታ እለት ከቤተክርስቲያኑ ወጥተው በመመለስ ላይ እያሉ በግምት ወደ ት መቶ  ሜትር ርቀት ላይ ርሱበት ጊዜ ናታችን የቅድስት ሃናን ጽላት የተሸከሙት አባት ራቸው ይተሳሰራል፣ መራመድ ሳናቸዋ በዚህም ከሌሎቹ ታቦታት ወደኃላ በሚቀሩበት ጊዜ ካሕናት አባቶች እና በቦታው የነበሩ አባቶች በሁኔታው ተደናግጠው ምክንያታቸውን ባለማወቃቸው የቅድስት ሃናን ታቦተ ጽላት ወደተሸከሙት አባት ጠጋ ብለው እንዳመማቸው ወይንም እንደደከማቸው  ቢጠይቋቸውም ምንም እንዳላመማቸው እና ነገር ግን መራመድ እንዳልቻሉ ይናገራሉ፣ ምናልባት ባታችን ደክሟቸው ይሆናል የእግዚአብሔር የቃልኪዳኑ ታቦት እሳተ መለኮት የሚያድርበት በመሆኑ በሌላ  እንሞክር ተብሎ ሞከራ ሌላኛውም አባት ተቀብለው ለመራመድ ክሩ እንደፊተኛው እግራቸው በገመድ የታሰረ ያህል ከነበሩበት መንቀሳቀስ ይሳናቸዋል በሌላ  በድጋሚ እንሞክር በማለት ለመጨረሻ ጊዜ ተቀይረው ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ልክ እንደፊተኞ በነበሩበት ቦታ ተተክለው ይቀራሉ ወዲያው አይ ምናልባት ቅድስ ሃና በእዚሁ ለማደር ፈቅዷ ሊሆን ይችላል እና በዚሁ ኳን ደኩነን በዚሁ አዳር ይሁን እና በሚቀጥለው ቀን በእናታችን ፈቃድ ለመንቀሳቀስ እንሞክራለን በማለት በዕለቱ አዳር በዚያው ቦታ ይሆንና በሚቀጥለው ቀን ከጸሎት እና ከኪዳን በኃላ የቃልኪዳኑን ታቦት ከመንበረ ክብሯ ለመመለስ በድጋቢ ሙከራ ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞ በዚያው አዳር ይሆናል፥ በዕለቱም ሌሊቱን ካህናት አባቶች በጸሎት ተጠምደው የነግህ ጸሎትም አድርሰው ኪዳኑንም አቅርበው ያድራሉ።

Thursday, May 14, 2015

በስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ ሓላፊነት በማይሰማቸው ጽንፈኛ ባለሥልጣናት በደል ‹‹ወረዳው ሊቢያ ኾኖብናል፤ ለእኛም አልቅሱልን›› እያሉ ነው

 • ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁ ከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻ ይደረግባቸዋል፤
 • የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤ ይህም ኾኖ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤት በምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል
Kilto Gomoro St. Mary Church
የወረዳው ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፣ የጽንፈኛ እና ዓምባገነን ባለሥልጣናትን በደል ተቋቁመው የሚያሠሯት የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
 • እየተሠራ ባለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹ጉልላት ለምን አስቀመጣችኹ›› በሚል ሦስት ጊዜ የማቃጠል ሙከራ ተደርጓል፤ በዚኽ ሳቢያ በዞኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ተወቅሰዋል የሚባሉት የወረዳው አስተዳደርና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጉዳዩን በውይይት ስም እያድበሰበሱ ክርስቲያኖችን በማይመለከታቸው ጉዳይ በደመወዝ ከመቅጣት፣ ከሥራ ከማባረር እና ከመኖርያቸው ከማሳደድ ውጭ መፍትሔ ሰጭ የእርምት ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤

Sunday, May 10, 2015

ግንቦት ፪ ቀን (May 10, 2015) በዋሺንግተን ዲሲ በሊቢያ ለተሰዉት ሰማዕታት ድምጻችንን እናሰማ

ግንቦት ፪ ቀን (May 10, 2015) በዋሺንግተን ዲሲ የዋሺንግተን ሞናመንት አጠገብ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በገዳመ ተክለሃይማኖት የወገን አድን መኅበር አማካኝነት በሊቢያ በግፍ ለተሰዉት ሰማዕታት ድምጻችንን እንድናሰማ በቨርጂኒያ፣ በሜሪላን፣ እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጋብዘዋል።
በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ካሕናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በቦታው ተገኝተው ለፈጣሪያችን በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰብን ያለውን ግፍ እና በደል ለመድኅኒዓለም ለማመልከት ብሎም ለመላው ዓለም ማሕበረሰብ ለማሳወቅ ይህ ሕዝባዊ ስብሰባ ተጠርቷል።
በቦታው ተገኝተው የበኩልዎን ያበርክቱ
ቦታው: በዋሺንግተን ሞናመንት ዋሺንግተን ዲሲ
በሜትሮ ለምትመጡ: Smithsonian Metro Blue and Orange Line ያለበት ሜትሮ ስለሆነ የሁለት ብሎክ መንገድ ነው
ሰዓት: 3:00 PM. EST
ቀን: ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. (May 10, 2015) 
አስታውሱ ለሰማዕታቱ ወገኖቻችን ብለን በአንድነት እንቁም


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!