Thursday, April 30, 2015

የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና… አንድ መኾን በቀል ነው

ethiopian and coptic christians
ግብጻውያን እና ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት (ሥዕል: ዘሪሁን ገብረ ወልድ)
‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡
‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው ምሥራቅን፣ እስያን እና አፍሪቃን በማካተት እገነባዋለኹ ያለውን ሙሉ በሙሉ በሱኒ አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ እስላማዊ ከሊፋየሚያሳይ ካርታም ይፋ አድርጓል፡፡ በአፍሪቃ ከምድር ወገብ በላይ ሦስት ንኡሳን ከሊፋዎችን የሠየመው ቡድኑ÷ ‹‹የሐበሻ ምድር››በሚል ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሶማልያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማእከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክንና ካሜሩንን ያካተተ ሲኾን ግብጽ፣ ሰሜን ሱዳን፣ ቻድ እና ከፊል ሊቢያ ደግሞ ‹‹የአልካና ምድር›› በሚል አካትቷቸዋል፡፡
እስላማዊ ከሊፋውን የመገንባት የተስፋፊነት ሕልሙን እውን እናደርጋለን በሚል ለቡድኑ ርእዮት እና አስተዳደር ማደራቸውን ያወጁበየሀገሩ የሸመቁ ጽንፈኞች እየበረከቱ ናቸው፤ ባለፉት ዐሥር ወራት ብቻ ከቡድኑ ጋራ ማበራቸውን ያወጁ እንደ ቦኮ ሃራም ያሉ ዐበይት ሸማቂዎች ከ30 በላይ ተቆጥረዋል፤ ዋነኞቹ የቡድኑ ታጣቂዎች ኢራቃውያን እና ሶርያውያን ሱኒዎች ቢኾኑም በድረ ገጽ በሚያካሒደው ቅስቀሳና ምልመላው ተነሣሥተው፣ ለመዋጋት እና ለመሞት ፈቅደው የተቀላቀሉት ኮብላይ ተሰላፊዎች(ጂሐዲስቶች) ከ80 በላይ አገሮች እንደተውጣጡና ከ12 ሺሕ በላይ መድረሳቸው ተነግሯል፡፡

Thursday, April 23, 2015

እራሱን የእስልምና መንግስት እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ ውስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ።ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ በPDF እዚህ ይጫኑ
To see English Version  የእንግሊዘኛውን ግልባጭ ለማንበብ


ሚያዚያ ፲፬ ቀን ፳፻፯ ..
ቁጥር : 04232014/0041
                            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ።አሜን!!!
 “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ማቴ. ፲፮፥ ፳፭
                                
እራሱን የእስልምና መንግስት እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ ውስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን        እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት በክርስቶስ ደም የተመሰረተች፤ በነቢያትና በሐዋርያት፡ በጻድቃንና በሰማዕታት በአጠቃላይ በቅዱሳን መስዋዕትነት የጸናች ርትዕት ኃይማኖት ናት።እነዚህ ቅዱሳን የከፈሉት መስዋዕትነት እንደ ዋዛ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን በውስጡ ብዙ መከራ ያለበት ነው።ምክንያቱም ክርስትና መንገዱ ጠባብ የሆነ የተጋድሎ ህይወትና የመስቀል ጉዞ በመሆኑ ነው። ይህንን ለመረዳት የቅዱሳኑን ገድልና ድርሳን በሚገባ መመልከት ያስፈልጋል።

Tuesday, April 21, 2015

ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ ከነገ ሚያዝያ ፲፬ ቀን ጀምሮ የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፤ ቤተሰቦች የተሠው ክርስቲያኖችን ፎቶ፣ ስመ ክርስትና እና ሙሉ አድራሻ እንዲያቀርቡ አዘዘ – ‹‹ልጆቻችን የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን ናቸው››

  • ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹ግፉዓን ይትመሰጥዋ ለመንግሥተ ሰማያት፤ በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል››(ማቴ.11÷12) በሚል ርእስ በሰሜን አፍሪቃ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀልን በተመለከተ ዛሬ፣ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀትር ላይ በድጋሚ ባወጣው ባለዘጠኝ ነጥብ ወቅታዊ የአቋም መግለጫ፡- በግፍ የተሠውት ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉየሃይማኖት መስተጋድላን መኾናቸውን አረጋገጠ፤ ቤተሰቦቻቸውንም አጽናና፡፡
Qirqos parents and relatives mourns‹‹የመዋች ቤተሰቦች የኾናችሁ ወገኖቻችን ኹሉ፡- 
በዚኽ ግፍ የተሞላበት ጭካኔ የገደሉት ልጆቻችን በዚኽ ዓለም የመኖር መብታቸው በአጭሩ ቢቀጭም ጌታችን፣ ‹‹የተገፉ መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል ማለትም ይወርሷታል›› ባለው አምላካዊ ቃለ እግዚአብሔር፣ ዕንባቸውን አብሶ በመንግሥቱ የሚቀበላቸው መኾናቸውን ዐውቃችኹ፤
እንደዚኹም ልጆቻችን ‹‹ወኩን መሃይምነ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት፤ እስከ ሞት ድረስ የታመንኽ ኹን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለኹ፤››(ራእይ 2÷10) ያለውን የጌታችንን ቃል ጠብቀው ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት በሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን ስለኾኑ የጀግና እናት አታለቅስም እንደተባለው የልጆቻችኹ ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚኽ ከሐዘናችኹ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡››

ቅ/ሲኖዶስ: በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወገዘ፤ ‹‹በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ኹሉ እናደርጋለን››

terrorist kills Ethiopian 11
‹‹ሃይማኖታችንን አንለውጥም›› በማለታቸው በአይ ኤስ የግፍ ተግባር በሰሜናዊ ሊቢያ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ ለሰማዕትነት ክብር የበቁት ኢትዮጵያውያን እና ኦርቶዶክሳውያን ወገኖች፤ በረከታቸው ይድረሰን፡፡

Terrorist 2
‹‹ሃይማኖታችንን አንለውጥም›› በማለታቸው በአይ ኤስ የግፍ ተግባር በደቡባዊ ሊቢያ በረሓ ለሰማዕትነት ክብር የበቁት ኢትዮጵያውያን እና ኦርቶዶክሳውያን ወገኖች፤ በረከታቸው ይድረሰን፡፡