Thursday, April 23, 2015

እራሱን የእስልምና መንግስት እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ ውስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ።ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ በPDF እዚህ ይጫኑ
To see English Version  የእንግሊዘኛውን ግልባጭ ለማንበብ


ሚያዚያ ፲፬ ቀን ፳፻፯ ..
ቁጥር : 04232014/0041
                            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ።አሜን!!!
 “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ማቴ. ፲፮፥ ፳፭
                                
እራሱን የእስልምና መንግስት እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ ውስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን        እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት በክርስቶስ ደም የተመሰረተች፤ በነቢያትና በሐዋርያት፡ በጻድቃንና በሰማዕታት በአጠቃላይ በቅዱሳን መስዋዕትነት የጸናች ርትዕት ኃይማኖት ናት።እነዚህ ቅዱሳን የከፈሉት መስዋዕትነት እንደ ዋዛ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን በውስጡ ብዙ መከራ ያለበት ነው።ምክንያቱም ክርስትና መንገዱ ጠባብ የሆነ የተጋድሎ ህይወትና የመስቀል ጉዞ በመሆኑ ነው። ይህንን ለመረዳት የቅዱሳኑን ገድልና ድርሳን በሚገባ መመልከት ያስፈልጋል።


በዘመናችን ጽላት ተቀርጾላቸው፤ ቤተ_ክርስቲያን ታንጾላቸው፤ የመታሰቢያ ዕለት ተሰጥቶአቸው በየጊዜው የምናከብራቸውና የምናገናቸው ብዙዎቹ ቅዱሳን የጽድቅ አክሊል የተቀዳጁት በወቅቱ ከነበሩ አላውያን ነገስታትና መምለክያነ-ጣዖት ገዢዎች እንዲሁም የዚህ ዓለም ፈጣሪና መጋቢ ልዑል እግዚአብሔር መሆኑን ካልተረዱና ምድራዊ ሥልጣናቸውን ዘለዓለማዊ አድርገው ከሚቆጥሩ ግፍ ፈጻሚዎች ጋር በመታገል ነው። ትግላቸውም የማያልፈውን የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማርና የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና አዳኝነት በመመስከር ነበር።
 ይህንንም በማድረጋቸው እንደ ጎመን እየተቀረደዱ፤ እንደ ሽንኩርት እየተላጡ፤ በድንጋይ እየተወገሩ፤ በሰይፍ እየተቀሉ፤ በመጋዝ እየተሰነጠቁ፤ ለአራዊት እየተሰጡ፤ በእሳት እየተቃጠሉ፤ በወኅኒ እየተሰቃዩ በብዙ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ ሆነዋል። ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፴፪ እስከ ፴፰ ላይ እንግዲህ ምን እላለሁ ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ፤ ስለ ሶምሶን ስለ ዮፍታሔም፤ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል። . . . ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፤ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉና እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ።”  በማለት አስፍሮታል።
የእነዚህን ቅዱሳን እምነት የሚከተሉ ኦርቶዶክሳውያንም ይህንንና ይህንን የመሰለውን መከራ በመቀበል በእሳት እንደሚፈተን ወርቅ በችግርና በስቃይ እየተፈተኑ ተዋህዶ ኃይማኖታችንን ለእኛ አስረክበውናል። እነርሱም ምንጊዜም የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊል አግኝተዋል።

ሰሞኑን የሰይጣን መልዕክተኛ በሆነውና አውሬያዊ ባህርይ ባለው አይስስ በተሰኘው የአረመኔዎች ቡድን በስለት ተቀልተውና በጥይት ተደብድበው በሊቢያ በረሃ ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈው ወንድሞቻችን የእነዚህ ቅዱሳን ወገኖች ናቸው። የእምነታቸው ጽናት ለኛም የበለጠ የሃይማኖት ጥንካሬን አስተምሮናል።እነዚህ የዘመናችን የኃይማኖት አርበኞችና የእውነት ምስክሮች እንደ ቅዱሳን አባቶቻቸው ከልዑል እግዚአብሄር ዘንድ ሰማያዊ ዋጋ እንደሚያገኙና የክብር አክሊል እንደሚቀበሉ ምንም ጥርጥር የለንም።  ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የሰማዕትነት ክብር እንደምትሰጣቸው እናምናለን።
በሌላ በኩል ግን ክቡር የሆነውን የሰው ልጆችን ሕይወት እየቀጠፈና የንጹሃንን ደም እያፈሰሰ ለአጋንንት የሚሰዋ አሸባሪ የአረመኔዎች ቡድን ፍጹም ሊወገዝ የሚገባው የሠይጣን መልዕክተኛ በመሆኑ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በጽኑ ያወግዘዋል፤ ከዚህም ጋር በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍና ቀሪዎቹም በሰቀቀን እንዲኖሩ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ወርቅ ላበደረ ጠጠር የሚያሰኝ እኩይ ተግባር በመሆኑ ይህንንም ተቋማችን አጥብቆ የሚያወግዘው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ከዚህ ሌላ
፩/ ሕዝበ ክርስቲያኑን የመጠበቅና የማስጠበቅ መለኮታዊ አደራ የተቀበሉ አባቶች  ቅድስት ቤተክርስቲያን ያላትን የሰውና የገንዘብ ኃይል ተጠቅማ እንዲሁም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የሚኖሩ ምዕመናንን አስተባብራ በባእዳን ሀገራት በተለይም በሊቢያ፣ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አደጋ ካለበት ቀጠና የሚወጡበትንና ሕጋዊ ከለላ የሚያገኙበትን መንገድ እንድትፈልግላቸው፤ በሰማዕትነት ላለፉት ወጣቶችም ተገቢውን ክብር እንድትሰጣቸውና በቋሚነት እንዲዘከሩ መታሰቢያ እንድታቆምላቸው፤ ለቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርግላቸው፤
፪/ ወገኖቻችን ሀገራቸውን ለቀው ለስደት፣ ለእንግልትና ለሞት እየተዳረጉ ያሉት በእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ነጻነታቸው ስላልተከበረላቸውና ሰርቶ የመኖር ዕድል ስለተነፈጋቸው በመሆኑ መንግሥት የዜጎችን መብት እንዲያከብርና ትውልዱ በሀገሩ ላይ ሰርቶ ማደር የሚችልበት ሁኔታ እንዲመቻችለት መንግሥትን አጥብቃ እንድትጠይቅ፤
፫/ በየጊዜው በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጥቃትና ውርደት፣ መከራና ሥቃይ የመጀመሪያ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደመሆኑ መጠን መንግሥት አሁንም ከተጠያቂነት ለመዳን የዜጎችን ሰብዓዊ መብት አክብሮ ሕዝቡን እንዲጠብቅና ሁሉንም በእኩልነት በማስተዳደር መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በትክክል እንዲወጣ፤
፬/ ሕዝቡም ለአደጋ ወደሚያጋልጥ ሀገር ከመሰደድ ይልቅ የመከራው ጊዜ እስከሚያልፍ ድረስ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው ወደ ኃያሉ አምላክ ልመናውን በማቅረብ ችግሩን ታግሶ ኑሮውን ለማሸነፍ እንዲሞክርና ለከፋፋዮች ወሬ ጆሮውን በመድፈን አንድነቱን ጠብቆ ሀገሩንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኑን ከጥቃት እንዲከላከል፤
፭/ በልዩነትና በጥላቻ ውስጥ ሆኖ የሚቀርብን ጸሎት አምላካችን እግዚአብሔር የሚቀበል አይደለምና ካህናትም ሆንን ምዕመናን እኔ የጳውሎስ እኔ የአጵሎስ ነኝ የሚለውን ክፍፍል ትተንና ሬቱን በማር በመለወስ የእግዚአብሔርን ቃል ለእራሳቸው ሀሳብ እንዲመች አድርገው የሚነግሩንን ሰባክያን ሳይሆን ትክክለኛውን የሃይማኖት ትምህርትና የወንጌል ቃል የሚያስተምሩንን አባቶች ተቀብለን እምነታችንን፣ ሥርዓታችንንና ትውፊታችንን ጠብቀን እንድንጓዝ፤

፮/ በቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በሀገራችን ውስጥ ለሚታየው ምስቅልቅል ሁኔታ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለው የብጹዓን አባቶች መለያየትና የአስተዳደር ክፍፍል መፈጠር ስለሆነ አባቶች ይህንን ከልብ በማጤን ያለማንም ጣልቃ ገብነትና ተጽእኖ ክፍፍሉ የሚወገድበትንና ስምምነት የሚወርድበትን ሁኔታ በቁርጠኝነት በመሻት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ወደቀደመ ክብሯ እንድትመልሱልን፤
፯/ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያላት እንደመሆኗ መጠን ዓለም ተባብሮ ይህንን አሸባሪ ቡድን እንዲያስወግደው ለዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ለአኃት አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ ጥሪዋን እንድታስተላልፍ፤
፰/ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከዚህ የሰይጣን መልዕክተኛ ቡድን ጋር ኅብረት እንደሌላቸው የምናምን ቢሆንም ይህ አሸባሪ ድርጅት እድል ካገኘ እኩይ ዓላማውን በሌሎችም ውስጥ ለማስረጽ ከመሞከር ስለማይቆጠብ ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር ለረዥም ጊዜ ተከብሮ የቆየው አብሮነታችን ዘለቄታ ያለው ሆኖ እንዲቀጥል ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችሁ ጋር አብራችሁ እንድትቆሙ በመንፈሳዊ ትሕትና አጥብቀን እንጠይቃለን።
በመጨረሻም ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በላከው መልዕክቱ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፩ ላይ “ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና።” እንዳለው እኛም ከእንቅልፋችን ነቅተን በመነሳትና መለያየቱን ትተን በአንድነት በመቆም ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ተዋሕዶ ኃይማኖታችንን እንድንጠብቅ መልዕክታችንን እያስተላለፍን፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከንፈር ከመምጠጥ ወጥተን የሰማዕታቱን ቤተሰቦችና በስደት ውስጥ ሆነው በስቃይ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ሁሉ ለመርዳት ፈጥነን እንድንረባረብና ዘላቂ መፍትሔ በመፈለግ ላይ እንድናተኩር መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የወንድሞቻችንን ነፍስ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር ይደምርልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ያድልልን። አሜን!!!
ሚያዝያ ፲፬ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም

                   ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት
April 30, 2015
Number: 04302014/0044
       In the Name of the Father, the Son and the Holy Spirit, One God. Amen!!!
For whosoever will save his life shall lose it: and whosoever will lose his life for my sake shall find it.
Mathew 16:25
Communiqué by the International Unity of Ethiopian Orthodox Tewhado Church Faith Followers on the Martyrdom of Ethiopian Christians in Libya
The Ethiopian Orthodox Tewahdo Church was founded through the blood of the Lord Jesus Christ and fortified through the martyrdom of the prophets, the apostles, the righteous and generally through the sacrifice of the saints. The martyrdom of the saints is not an ordinary matter but an extraordinary suffering borne by the Christian, for narrow is the path of Christianity and the traveler bears the cross and takes up the affliction that comes with it. A closer look at the documented acts and homilies of the saints furnishes a clearer picture of what it means to be a Christian.     
The saints of old, that we commemorate in our time for whom tablets are hewed and memorial sanctums built, were graced with the crown of righteousness for their virtue in standing up to unjust rulers, to worshipers of idols, to the wicked who refused to believe that God created the world and that He alone feeds his creation, to the cruel who considered their earthly powers as eternal. The saints declared the Godhood of our Redeemer the Lord Jesus Christ in all places that required sacrifice to doing so. 
For what virtue they had the saints endured great tribulations- they were shredded like cabbage, peeled like onion, stoned, beheaded, dismembered by hacksaw, given up to the beasts of the field, thrown into fire and locked to languish in jails.  As Saint Paul wrote in his epistle to the Hebrews (Hebrews 11: 32-38): "And what shall I more say? for the time would fail me to tell of Gedeon, and of Barak, and of Samson, and of Jephthae; of David also, and Samuel, and of the prophets.  _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _   Women received their dead raised to life again: and others were tortured, not accepting deliverance; that they might obtain a better resurrection. And others had trial of cruel mocking and scourging, yea, moreover of bonds and imprisonment. They were stoned, they were sawn asunder, were tempted, were slain with the sword: they wandered about in sheepskins and goatskins; being destitute, afflicted, tormented" he scribed.
The Orthodox Tewahdo faithful who followed the footsteps of the saints also confronted similar tribulation and were tested in fire like gold and preserved the Tewahdo Church for us to this day. They too attained eternal heavenly glory. 
To the saints also belong our brothers in Christ, who were slain recently by a cruel act of beheading and gunshot in the hands of the cruel messengers of Satan who adventure with beastly nature calling themselves ISIS. The steadfast faith of these martyrs has imparted to us a sense of strength in our faith. No doubt these valiant defenders of our faith who bore witness to the truth have joined their fathers, the saints, to receive heavenly crown from the Lord God. We believe our blessed Church will grant them the honor of martyrdom.      


On the other hand, we, the International Unity of Ethiopian Orthodox Tewhado Church Faith Followers, deplore the evil act of extinguishing the precious soul of innocent humans as an offering to the devils being carried out by this terrorist group of assassins. We also deplore the savage act of murder being committed in South Africa as it lends to the old adage, "to he who supplied gold is returned pebbles of chastisement."   
Moving beyond this, we implore:
1. The fathers of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church, who are entrusted by the Lord to look after the children of the Church, to use the human and financial resources of the Church, and by leveraging resources of the Church's children inland and overseas, to seek ways to disentangle Ethiopians suffering in Libya, Yemen and South Africa and also to accord the necessary honor to the martyred young faithful as well as to provide support to their families
2. Since the reason our compatriots are forced to flee their country is the lack of freedom to live and the absence of opportunities to work, we implore the fathers to appeal to the government for the dignity of citizens and for the prevalence of an environment conductive to fruitful work.   
3. Since the responsibility to the indignity and affliction of the citizens is the governments, we petition the government to restore human dignity and to fulfill its duty of catering equal opportunity to all the citizens.   
4. Instead of seeking refuge in dangerous foreign lands, we beseech citizens of Ethiopia to try and weather the pain at home by prayer and by supplicating to the Lord in the Highest until the withdrawal of the period of tribulation.
5. The Lord our God does not accept prayers offered in rancor and acrimony and therefore we, clergymen or laymen, should immediately vacate this division of claiming I am of Paul; and I of Apollo’s. We should renounce honey coated sermons of poison served by self serving preachers and embrace sermons of criticism and correction by fathers who hold fast the canon of true faith preserved in apostolic succession.  
6. The principal contributor to the adversity in our Church and in our country is the administrative breakup and division that transpired between our fathers. We demand that our fathers consider the matter in greater concern without allowing outside intervention, and entreat the fathers to seek in earnest a remedy for the division so our Church can return to her former glory.  
7. Since our Church is universal, we beg the Church to call upon sister Churches and upon appropriate international organizations to unite to seek ways to get rid of this terrorist group. 
8. Although we trust that Ethiopians of the Muslim faith would not have unity with this satanic terrorist group, we have reason to believe that the satanic group will try to imbue others of similar faith with malicious feelings to try and get them to do its bidding. We humbly caution the Muslims to maintain the age-old tradition of respect for each other and ask the Muslims of Ethiopia to stand by their Ethiopian kinsfolk.  
In conclusion, as the great apostle Saint Paul said in his epistle to the Romans (Romans 13: 11): "knowing the time, that now it is high time to awake out of sleep: for now is our salvation nearer than when we believed", we call upon all Ethiopians to be awake out of sleep and cast off division and stand together in


unity and defend our country and our Tewahdo faith. In spiritual humbleness we call upon all residing in Ethiopia and upon all those residing abroad to desist the biting of lips in vexation and instead to reach out for the families of the martyrs and to extend your loving hands to our brothers and sisters in refuge who are being afflicted by hardship and privation.     
May the souls of our slain brothers be added to the company of martyrs and may the Lord provide comfort and consolation to their families. Amen.
April 30, 2015


IUEOTCFF


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

5 comments:

 1. “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። “ ማቴ. ፲፮፥ ፳፭

  ReplyDelete
 2. እግዚአብሔር ያስበን ምነው ኢትዮጵያዊ በእንዲህ ጊዜ እንኳን አንድነት ማሳየት እንዴት ተሳነን? ስለምን ተብሎ አንዳንዶች የራሳቸውን ፖለቲካል ጌን ብቻ ለማግኘት ይራወጣሉ እረ ስለ ኢትዮጵያ አምላክ ብለን ስለ እነዚህ ሰማዕታት ብለን እባካችሁ በእነዚህ ሰማዕታት ደም አንዘባበት። እንደው ምን አለበት በዚህ ጊዜ እንኳን አብያተ ክርስቲያናት በየቦታው በየጎጆው ጸሎተ ምህላ እናርግ ከሚሉ በአካባቢያቸው ካሉት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በአንድነት በመሆን በጋራ ሕዝበ ክርስቲያኑን በአንድነት አድርጎ ሰሎቱ ቢደረግ ወደ ሰማይ ወደ ፈጣሪ ሊደርስ ይችላል ነገር ግን ሁሉም በየራሱ ጎጆ የራሱን ፖለቲካዊ ካልሉሌሽን ተጠቅሞ በራሱ ቦታ ብቻ ነው እንዲደረግ የሚያደርገው ለምሳሌ በዚህ በካሊፎርኒያ አካባቢ እውነት እነዚህን ሰማዕታት ለማሰብ ከሆነ ዓላማቸው ነፍሳቸን በደጋጎቹ አባቶቻን ቅዱሳን ቦታ እንዲያኖርልን ከሆነ ስለምን ብለው በአካባቢው ያሉት ቤተክርስቲያናት በአንድ ላይ ጸሎተ ፍትሃቱ አይደረግም የምን የመለያየት አባዜ ነው የያዘን ኢትዮጵያውያኑን ዛሬ እንኳን በዚህ ጊዜና ሰዓት እንዴት አንማርም። እረ የፈጣሪ ያለህ . . . ምን አለበት እንደው ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝ ነን አይደለም እንዴ የሚለው ወይስ ማሊያ ብቻ ነው ተመሳሳይ፣ ተመሳሳይ ማሊያ ለብዞ ለተቃራኒ መጫወት የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን ነገር ግን በግልጽ እግዚአብሔር እስኪያሳየን ድረስ ኦርቶዶክሳዊያን ነን እስከሚሉ ድረስ ስለም ተብሎ ነው በአንድ ላይ ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎቱ የሰመረ እንዲሆን በጋራ የማይደረገው? ? ?
  ሌላው ደግሞ በሲያትል አካባቢ ያሉ ሰዎች ቀኖና ቤተክርስቲያን በማይፈቅው መልኩ ለሰማዕታቱ ጸሎት እናድርግ ተሰብስበን ይላሉ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ ምንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች እስላም ይሁኑ ፕሮቴስታንት ይሁኑ ወይም ቡዲስቶች አይታወቅም (እስላም ጸሎት ማድረግ የለበትም ለማለት አይደለም) ሁሉም በየቤተ እምነቱ ወደ ፈጣሪው ኢትዮጵያውያኖች ላይ የደረሰብንን የሞራል፣ የሐዘን፣ የጸጸት እንዲሁም የዜግነት ድቀት ለማንሳት እና ወደፈጣሪ መለመን ይገባል ባይ ነኝ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስም ከሆነ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦቱ ባለበት፣ በእውነት ፈርሃ እግዚአብሔር በሚኖርበት ጸጥታው፣ እርጋታው፣ ተማጽኖው እና ስዕላቱ ባሉበት እንዲሆን አስተምህሮ ቤተክርስቲያን ያዘናል ነገር ግን ዛሬ ዛሬ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ብቻ ለማሳካት የሚሞክሩ ጥቂት ተረፈ አርዮሳውያን በሰማዕታቱ ስም ኑና እንጸልይ ይሉናል እነማናችሁ ስማችሁን ወይም ድርጅት ከሆናችሁ ድርጅታችሁን፣ ማኅበራት ከሆናችሁ የማን ማኅበር ናችሁ ወይስ ቤተክርስቲያን ከሆናችሁ ስለምን በቤተክርስቲያኑ ስም አትጠሩም እንደው ዝም ብሎ ኑና እንጸልይ ማለቱ ትንሽ ወጣ ያለ የተንጋደደ አካዬድ ነው እና እባካችሁ የእናንተ ማኅበር ለነዚህ ሰዎች ሃሳብ ቢሰጥ ትንሽ እናንተ የዚህኛው ነን ወይም የዛኛው ነን ስትሉ ሰምተን ስለማውቅ የተሻለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተቋም ነው ብለን እናምናለን እና የቤተክርስቲያኒቱን ሕግጋት የማስከበር የናንተ ሥልጣን ባይሆንም እነዚህን እኩይ አካሄድ የሚሄዱትን ሰዎች ቢቻል ብትገስጿቸው ካልሆነም ብትመክሯቸው የተሻለ ነው ብዬ አስተያየቴን እሰጣለው።
  በተረፈ ግን እባካችሁ ጥቁር ለባሾች ካህናት በሙሉ በዚህ ጊዜ አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን እናንተ የምትከፍት በር ዛሬ ስንቱን መናፍቅ እና አርዮሳዊ እንዳስገባ ሳትገነዘቡት የምትቀሩ አይመስለንም እውን መነኮሳት የሆናችሁ ለዚህች ቤተክርስቲያን ከእናንተ በላይ ዘብ ሊቆምላት የሚገባ ሰው እኮ ባልበረ ነበር ነገር ግን እናንተም አፍራሾች የሆናችሁበት ጊዜ ነውዛሬ። አያድርገው እና እነዚህ እኩይ የሆኑ አይ ሲስ የሚባሉ ሰዎች እኮ ቢሳካላቸው ዓለምን በሙሉ እናሰልማለን ብለው ነው ዓላማቸው እንደው በህልማቸው እንኳ ቢሳካላቸው እና ቢሆን ነገ ምዕመኑ መቼም ዛሬን እንዴት አድሬ ስለሚል ሊሰልም ይችል ይሆናል ነገን ለማየት ልጄን ለማሳደግ፣ እናቴን ለመጦር፣ ሃገሬን ለማየት እንዲያበቃኝ እና የመሳሰሉትን ትርኪ ምርኪ ደርድሮ ይሰልማል እንበል እናንተስ??? መነኮስን ስትሉ መቼ ምን ቢመጣ ምን ቢሆን ሰማይ ከፍ ቢል ምድርም ዝቅ ብትል ከእግዚአብሔር መንገድ ላትወጡ፣ ፍቅረ ክርስቶስ ይዟችኊ መንገዱን (መስቀሉን) ተሸክማችሁ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እንደምትጓዙ በቤተክርስቲያን በታቦቱ በቅዱሳኑ ስም ምላችሁ እና ተገዝታችሁ ፍታት ተደርጎላችሁ ነው የመነኮሳችሁት እውን እውነት ቢሆን ምን ልትሆኑ ነው ከዚህ ሁሉ ምኅላ በኃላ ከዚህ ሁሉ ግዝት በኃላ አትሰልሙም ቆባችሁንም አትጥሉም ብዬ አምናለሁ፥ እንደዚያ ከሆነ እውነታው ከማንም በላይ እኮ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት መስራት ያለባችሁ እናንተ ነበራችሁ፣ ከማንም በላይ ቤተክርስቲያን እንዳትጠፋ አማኞች ክርስቲያኖች እንዲጸሉ ማድረግ ያለባችሁ እናንተ ነበራችሁ የራሳችሁ ማንነት እና ሕልውና በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ስለሆነ ክርስቲያኖች እኮ ባይኖሩ ምን ልትሆኑ ነው? ክርስቲያን ሁሉ ወደ ሌላ ሃይማኖት ቢሄድ ማንን ቀድሳችሁ ልታቆርቡ ነው ማንንስ ልትናዝዙ ነው ወይንስ እናንተም ቆባችሁን አውልቃችሁ ምዕማኑ ወደሚሄድበት ትሄዱና አሁንም እኛው ነው ከቆባችን በስተቀር ልትሉ ነው?? ኽረ ተው ይሄ ጊዜ ያልፋል እግዚአብሔርም ይታዘባል ስለገንዘብ ብላችሁ ስለጊዜያዊ ክብር ብላላችሁ እና ስለጥቅም ብላችሁ ችላ የምትሉትን መንጋ የመጠበቅ ሃላፊነት ተሰጥቷችኊ ሳትጠብቁ ያቆያችሁን መንጋ በትናችሁ ሃምሳ ተሰጥቷችሁ ሁለት ካስቀራችሁ መጨረሻችሁ ምን እንደሚሆን አስቡት ስለ ሰማዕታት ደም ብላችሁ "አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን" ስለ ኢትዮጵያ አምላክ ብላችሁ
  ኡ .. ኡ . . ኡ . .ኡ . .የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ ፊትህን ወደኛ መልስ ኤሎሄ . . .ስማን ዝም አትበለን የዓለም ቢለዋ በላችን . . .ኡ . . .ኡ

  ReplyDelete
 3. የወንድሞቻችንን ነፍስ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር ይደምርልን

  ReplyDelete
 4. ኡ .. ኡ . . ኡ . .ኡ . .የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ ፊትህን ወደኛ መልስ ኤሎሄ . . .ስማን ዝም አትበለን የዓለም ቢለዋ በላችን . . .ኡ . . .ኡ
  ቃለሔወት ያሰማልን !

  ReplyDelete
 5. ኡ .. ኡ . . ኡ . .ኡ . .የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ ፊትህን ወደኛ መልስ ኤሎሄ . . .ስማን ዝም አትበለን የዓለም ቢለዋ በላችን . . .ኡ . . .ኡ
  ቃለ ሒወት ያሰማልን!

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤