![]() |
የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅስት ሐና ወቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ |
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው ፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ የቅዱስ ዑራኤል፣ እና የእናታችን የቅድስት ሐና ቤተክርስቲያን ጸበል ለመባረክ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው የግንቦት ልደታ እለት ከቤተክርስቲያኑ ወጥተው በመመለስ ላይ እያሉ በግምት ወደ ሁለት መቶ
ሜትር ርቀት ላይ በሚደርሱበት ጊዜ የእናታችን የቅድስት ሃናን ጽላት የተሸከሙት አባት እግራቸው ይተሳሰራል፣ መራመድ ይሳናቸዋል በዚህም ከሌሎቹ ታቦታት ወደኃላ በሚቀሩበት ጊዜ ካሕናት አባቶች እና በቦታው የነበሩ አባቶች በሁኔታው ተደናግጠው ምክንያታቸውን ባለማወቃቸው የቅድስት ሃናን ታቦተ ጽላት ወደተሸከሙት አባት ጠጋ ብለው እንዳመማቸው ወይንም እንደደከማቸው ቢጠይቋቸውም ምንም እንዳላመማቸው እና ነገር ግን መራመድ እንዳልቻሉ ይናገራሉ፣ ምናልባት አባታችን ደክሟቸው ይሆናል የእግዚአብሔር የቃልኪዳኑ ታቦት እሳተ መለኮት የሚያድርበት በመሆኑ በሌላ አባት እንሞክር ተብሎ ይሞከራል ሌላኛውም አባት ተቀብለው ለመራመድ ሲሞክሩ እንደፊተኛው እግራቸው በገመድ የታሰረ ያህል ከነበሩበት መንቀሳቀስ ይሳናቸዋል፣በድጋሚ በሌላ አባት በድጋሚ እንሞክር በማለት ለመጨረሻ ጊዜ ተቀይረው ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ልክ እንደፊተኞቹ በነበሩበት ቦታ ተተክለው ይቀራሉ ወዲያው አይ ምናልባት ቅድስት ሃና በእዚሁ ለማደር ፈቅዷ ሊሆን ይችላል እና በዚሁ ድንኳን ደኩነን በዚሁ አዳር ይሁን እና በሚቀጥለው ቀን በእናታችን ፈቃድ ለመንቀሳቀስ እንሞክራለን በማለት በዕለቱ አዳር በዚያው ቦታ ይሆንና በሚቀጥለው ቀን ከጸሎት እና ከኪዳን በኃላ የቃልኪዳኑን ታቦት ከመንበረ ክብሯ ለመመለስ በድጋቢ ሙከራ ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞ በዚያው አዳር ይሆናል፥ በዕለቱም ሌሊቱን ካህናት አባቶች በጸሎት ተጠምደው የነግህ ጸሎትም አድርሰው ኪዳኑንም አቅርበው ያድራሉ።