Saturday, May 2, 2015

ለሰማዕታት ወገኖቻችን እንዴት እንርዳበስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ኢየሱስም መልሶ  እንዲህ አለ:: አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያርኮ  ወረደ  በወንበዴዎችም  እጅ ወደቀ፤  እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በህይወትና  በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ:: ድንገትም  አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ  አለፈ:: እንዲሁም ደግሞ  ሌዋዊ  ወደዚያ  ስፍራ  መጣና  አይቶት ገለል ብሎ  አለፈ:: አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ ቀርቦም ዘይትን የወይን ጠጅ በቁስሎቹ ላይ አፈስሶ  አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ  ወስደው  ጠበቀውም:: ሉቃስ ምዕ 10 : 30–34
ስለዚህ እኛም ለወገኖቻችን እንደ ሳምራዊ እንዘንላቸው፤ በቁስላቸው ላይ መድሀኒት እናፍስላቸው ወደ እንግዶች ማደሪያም እንውሰዳቸው::
ቀድሞ ዋልድባ እንታደግ (SAVE WALDBA) አሁን ደግም በህጋዊ ሁኔታ ተመዝግቦ በማገልገል ላይ የሚገኘው አለም አቀፍ የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (IUEOTCFF) እስካሁን ለወገኖቻችን ያደረጋቸው ድጋፎች:-


  • የዋልድባ  ገዳም አባቶችና እናቶች በልማት ስም መገፋት ከጀመሩበት ጊዜ  አንስቶ  ድጋፍ  በማድረግ  ላይ ይገኛል::
  • ትርጉም አልባ የሆነ የ6ኛ ፓትሪያሪክ ምርጫ ከማድረግ ይልቅ እርቅ ይቅደም ብሎ የማስታረቅ ስራ ይሰራ ለነበረው ኮሚቴ  የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል::
  • በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮለጅ ተማሪዎች ላይ አስተዳደሪያዊ  በደል በተፈጸመባቸው ወቅት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል::
  • በሳዑዲ ዓረብያ በወገኖቻችን ላይ ጥቃት በተፈጸመ ወቅት በዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዩጵያውያን (GLOBAL ALLIANCE FOR THE RIGHTS OF ETHIOPIANS ) በሚባለው ድርጅት በኩል በባዕዳን ምድር ለሚገኙት ድጋፍ አድርጓል:: ወደ እናት አገራቸው ኢትዮጵያ  ለተመለሱት ደግሞ በገዳመ ተክለሃይማኖት የወገን ነፍስ ኣድን በሚባል ማህበር በኩል እርዳታ ልከናል::

በዚህ ሁሉ ሊመሰገን  የሚገባው ሀይማኖቴ  ብሎ  አንጀቱን አስሮ  የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው ህዝበ ክርስቲያን ነው::

ቀኖች ከትላንት ይልቅ ዛሬ በከፉብት ጊዜ ምን እናድርግ???
ትላንት እንዳደረግነው አሁንም እየሞቱና በብዙ መከራ ውስጥ እያለፎ ላሉት ወገኖቻችን ልንደርስላቸው ይገባል:: በዚህ መሰረት
1.      28ቱን ሰማዕታት ቤተሰቦች  መደገፍ፣
2.     በሊቢያ በዲያብሎስ  መልዕክተኛ  አፍንጫ ስር ለሚገኙ ወገኖቻችንን ዛሬ መድረስ፣ ነገ አይደለም::
3.     በየመን፣ በሳውደ አረቢያና  በሌሎች ቦታዎች ሁሉ የሚገኙ ወገኖቻችን መርዳት በአስቸኯይ መከናወን ካለባቸው ተግባራት ውስጥ ተቀዳሚዎቹ ናቸው። ይህ ደግሞ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው:: የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ቁልፋችንም ነው:: ስለዚህ እንደትላንቱ  ዛሬም ከጐናችን ሆናችሁ ወገኖቻችንን እንድንረዳቸው  በአምላክ ሰማዕታት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን:: ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለወገኖቻችን ስደት ተጠያቂው መንግስት ስለሆነ በዚህ ላይ ድምፃችንን ከማሰማት እንዳንቆጠብ እናሳሰባለን::
በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያን አባቶች ቄሳር ሆይ! ሺህ አመት ንገስ ማለትን አቁሙና የክርስቶስን መንጋ  ከሁለትና ከሶስት ጐራ  ከመሰንጠቅ ተቆጥባችሁ ለህዝብ ክርስትያኑ ህልውና በአንድነት ቁሙ በማለት መወትወት የውዴታ ዴታችን ነው::

ጥያቄ አለዎት?
ላለፎት ሶስት አመታት ሳይቋረጥ በመከናወን ላይ ባለው የምዕመናን የመወያያ የስልክ ስብሰባ ላይ ተገኘተው ይጠይቁ:: ሀሳቦትንም ይስጡ::                 
+ በቀጥታ በሚከተለው ቁጥር በመደወል (559)726-1200  ፒን የመግቢያ ቁጥር  157715#
ዘወትር ሐሙስ 6:00 PM. PST ወይንም  9:00 PM. EST.

የዚህ ማህበር ግልጋሎትና  አሰራር እንዲጐለብት ይሻሉ?
 በአባልነት ይመዝገቡ እንዲሁም የሚኖሩበት ግዛት (State) ተወካይ ሆነው በኮሚቴ ውስጥ ያገልግሉ።

                                   የአባልነት መመዝኛው ምንድን ነው?
የቅድስት ቤተክርስቲያንና ትምህርተ ሀይማኖት፣ ስርአትና ትውፊት ጠብቆ መገኘት::


ምስጋና ለቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔርና ለእናታችን ለወላዲት አምላክ ይሁን:: አሜን!

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤