Sunday, May 3, 2015

የመልካም ምኞት መግለጫ ለብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

                     እንኳን ለ፳፭ኛው በዓለ ሲመትዎ በሰላም አደረሰዎ ቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆርዮስ
የIUEOTCFF ተወካዮች በበዓሉ ላይ በተገኙበት ሰዓት

እግዚአብሔር አምላክ አለ “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ . . .” ሮሜ ፲፪ ፥ ፲፭
ዛሬ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በዋሺንግተን ዲሲአካባቢ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፳፭ኛ በዓለ ሲመት በተከበረበት ወቅት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ለብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እንኳን ደስ አለዎት በማለት መልካም ምኞታችንን ለመግለጽ ብሎም አምላከ ቅዱሳን ፈጣሪያችን በሕይወት አቆይቶ የቤተክርስቲያንን ትንሳኤ ምዕናን እንድናይ ብፁዕነታቸውን በይበልጥ ግንባር ቀደም ሆነው ለማየት እንዲያበቃን መልካም ምኞቻችንን በመግለጽ የልዑካን ቡድናችን ደርሶ ተመልሷል።
የልዑካን ቡድኑ በቦታው ተኝቶ መልካም ምኞቱን ከመግለፁም ባሻገር አብረዋቸው ለብፁዕነታቸው እና ለሊቃነ ጳጳሳቱም ለሁሉም በየአህጉረ ስብከታቸው የዚህ ማኅበር ዓላማውን እና ምኞቱን ለሁሉም ብፁዓን አባቶች እንዲደርስ ጥረት አድርጓል የደብዳቤውንም ሙሉ ይዘት ከዚህ መግለጫ ጋር አያይዘንዋል እና በስተ መጨረሻ ላይ በPDF መመክከት ይችላሉ


+ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የመልካም ምኞታችንን መግለጫ ደብዳቤ ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

+ ለብፁዓን አባቶች የተማጽኖ ደብዳቤ በወቅታዊ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከብፁዕ አቡነ መልከፄዲቅ ጋር

የበዓሉ አከባበር በካቶሊክ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ


የበዓሉ አከባበር በካቶሊክ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ

የበዓሉ አከባበር በካቶሊክ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ

1 comment:

  1. “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ . . .” ሮሜ ፲፪ ፥ ፲፭

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤