Friday, August 28, 2015

የሊቢያው ሰማዕት አወቀ ገመቹ ቤተሰቦች ተጎበኙ

ታላቅ ወንድም ቶሎሳ ገመቹ መንገድ መሪያችን ነበር ።

የአወቀ ወላጅ አባትና ሀዘን ያደቀቃቸው ወላጅ እናቱ በቀዬአቸው ።

ወላጆች በቅርብና ከአጠገባቸው ካሉት ቀሪ ልጆቻቸው ጋር ።

ከቤተ ዘመድና ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ።

ሟች አወቀ ገመቹ ይህ ነበር ።

የእናት ልቅሶ ብዙ ለማውራት አልተመቸንም ነበር ። ምክንያቱም የእናት አንጀት ነዋ ።

የዋዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉልኝ ከፍተኛ ትብብር ለሰማዕቱ አወቀ አባት ለአቶ ገመቹ በእኔ በኩል የተላከውን 49760 ብር የባንክ ደብተር በስማቸው አውጥቼ አስረክቤያለሁ ።


ወደ ሊቢያ ሂዶ በግፈኛው ISIS እጅ ከመውደቁ በፊት አወቀ ገመቹ በካርቱም የተነሳው ፎቶና ከመገደሉ በፊት የተገኘው ምስሉ ።
ይህንን ጽሁፍ ከመምህር ዘመድኩን የፌስ ቡክ ፔጅ ሲሆን መምህር ዘመድኩን በተለይ በሊቢያ ከተሰውት ሰማዕታት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መሰዋት በኃላ በፍጹም ቅንዓት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትን በማፈላለግ ለቤተሰቦቻቸው መጽናኛ የሚሆን መጠነኛ እርዳታ ከተለያዩ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰበውን ሲያደርስ፥ ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች መጽናኛ ሲሆን ተመልክተናል በእውነት ይሄ ነው ኦርቶዶክሳዊነት ብሎም ኢትዮጵያዊነት፤ ወገን ለወገኑ ሲደርስ እነዚህ በእውነት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጨካኝ ከይሲዎች ጧሪ ቀባሪ የሚሆን ልጅን ሲቀማ ብግፍ ሲያርድ በእጅጉ ያሳዝናል አለሁ የሚል ወገን የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ አለሁ በማለት ሃገር አቋርጦ በመሄድ ወገኖቹን ኢትዮጵያውያንን በመደገፉ ብእውነት ሊመሰገን የሚገባው ወንድም እንደሆነ ከማናችንም የተሰወረ እውነታ አይደለም
ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም በእንዲህ ዓይነት የተቀደሰ ተግባር ላይ የየግል ተሳትፏችንን እንድናደርግ የዝግጅት ክፍላችን በአጽንዖት ያስገነዝባል፤ እኛም ጽሁፉን በቀጥታ ከመምህር ዘመድኩን ገጽ በመውሰድ ለአንባቢያን እንዲደርስ በማሰብ እንደሚከተለው አቅርበነዋል መልካም ምንባብ . . .


“ይህን ጽሑፍ Share ማድረግ እነኚምስኪንና ቤተሰቦች ከሚረዳቸውአቅካላቸው ሰዎችንደማገናኘት ይቆጠራል ።”

ጽሑፉ የዘገየው ማስታወሻ የያዝኩበት ደብተሬን ንጋፋው ልጄ ማኅተመ መድኩን መሽቶብን ደርንበት ሆቴል ረስቶት በመምጣቱ እንደገና የሟች ወንድም ቶሎሳ ገመቹ መጥቶ ስሞችን መተ ምህረቶችን የባንክ ጥሩን ምር አረጋግጦ እስኪነግረኝ ድረስ መጠበቅ ስለነበረብኝ ነው
በሰማዕታቱ ዙሪያ የጀመርኩትን መረጃ ለእናንተ ለጓደኞቼ የማቅረቡን ነገር ከሰማዕቱ መንግስቱ ጋሼ በኋላ ላ አዲስ ሰማዕት እስኪገኝ ድረስ ለጊዜው የሊብያውን ሰማዕታት ታሪክን በተመለከተ መጻፌን እንዳቆምኩ ነግሬአችሁ ነበር ።
ሆኖም ግን ደቡብ አፍሪካ ሳለሁ በሀገረ ጀርመን የሚኖሩ እናት ላ አዲስና መልኩ የተለየ ቶውም የተገኘ ሰማዕት እንዳለና ተሰብም መርዶ ተረድተው"እርማቸውን" እንዳወጡ ከሀገር ቤትም አብረው ወደ ስደት ወጥተው እሱ ተሳክቶለት አሁን ጀርመን የሚገኝ ወንድም አለውና እባክህን አግኘው ብለው ያገናኙኛል ።
እኔም ከዚህ ከተባለው የሟች ወንድም ጋር አስፈላጊውን መረጃ ከተለዋወጥን በኋላ አዲስ አበባ ከሚኖር የሟች ታላቅ ወንድሙ ጋር ተገናኝተን ቤተሰብ ጋር የምንሄድበትን ሁኔታ አመቻችተን እነሆ ቀኑ ደርስ ጉዞአችንን ወደ ምስራቅ ወለጋ ወደ አዲሱ የሊብያ ሰማዕት ቤት አድርጌአለሁ ።
ለጉአችን መሳካት ደግሞ ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት ጓደኞቼ ወንድማማቾቹ " የፎቶ ወንድወሰን ባለቤቶች የሆኑት " አቶ ወንድወሰን ተምትምና ታናሽ ወንድሙ አፈወርቅ ተምትም ይመሰገናሉ ። ወንዴ ጉዳዩን እንደሰማ ለአፈወርቅ በመንገር ሎንግቤዝ ላንድሮቨር መኪናቸውን ከነሹፌሩ በመስጠት ያንን አስቸጋሪና አድካሚ መንገድ ከቤታቸው ወጥተው የማያውቁትን ልጆቼን ይዤ እንዳልቸገር በእጅጉ ረድተውኛል ። በእውነት በህዝብ ትራንስርት ህፃናቱን ይዤ ሄጄ ሆን ኑሮ እንዴት እቸገር እንደነበር በዚህ ዘመናዊ መኪና ላይ ያየነውን ድካም ሳስበው ነው ።
እንደተለመደው ወደ ሰማዕቱ ቤት እንደምሄድ እስራኤል ሆኜ በጻፍኩት ማስታወሻዬ ላይ ጠቁሜ ስለነበር ከበረከቱ ለመሳተፍ የፈለጉ ወዳጆቼና መልእክቱን ያነበቡ ጥቂት ደግ ልብ ያላቸው ትዮጵያውያን በግላቸው የእዝን አድርስልን ብለው በላኩልኝ መሰረት አጠቃላይ መጠኑ በስተመጨረሻ የተጠቀሰውን ብር አስረክቤአቸዋለሁ።
አሁን ጉዞ እንጀምር እናንተም በምናባችሁ ተከተሉኝ ። የጉዞ መስመራችንን በምእራብ ዋ በኩል አድርገን የአምቦ ከተማን አልፈን ጌዶ ከተማ ስንደረስ በስተቀኝ በኩል እንታጠፍና ወደ ንጭሀ ስኳር ፋብሪካ የሚወስደውን መንገድ ይዘን በመኪና ሳይሆን ፈረስ እየጋለብን የምንሄድ ይመስል እያዘለለ በሚንጠን የገረጋንቲ መንገድ ላይ አሰልቺና አድካሚ ጉዞ እናደርግና በስተመጨረሻ ወደ ሊብያው ሰማዕት ቤት እንደርሳለን ።
አሁን ከመኪናዋ ወርደን በስተ ምስራቅ አቅጣጫ በእግራችን ጥቂት ደቂቃዎችን ጉዞ ካደረግን በኋላ በሆሮ ጉዱሩ ምቦልቻ ሬፍ ጉደኔ ቀበሌ ውስጥ በደሳሳ ጆና በአረንጓዴ የበቆሎ ማሳ በተከበበ የገጠር የሚያምርና ውብ ግቢ ውስጥ እንደርሳለን ። በዚህ ግቢ ነው እንግዲህ የሊብያው ሰማዕት አወቀ ገመቹ ተወልዶ ያደገው።
ጆ ቤቷ ለእንግዶች አትመጥንም በሚል እሳቤ ከአጠገባቸው ባለና አሁን በቅርብ በተሠራ ምርጊቱም ባልደረቀ መጠነኛ ጎጆ ቤት ውስጥ አስቀድሞ መምጣታችን የተነገራቸው ወላጆቹና ዘመዶቹ ተሰብስበው ነበር የጠበቁን።
ያው እንደሚታወቀው እኔ የሀረር ቆቱም አይደለሁ? ሮምኛዬ የሀረር ቢሆንም እንደምንም ያችኑ ያልረሳኋትን እና በመጠኑም ቢሆን ከሰው ጋር የምታግባባኝን ሮምኛ እየሰባበርኩም ቢሆን አማርኛም እየቀላቀልኩ ወጋችን ቀጠልን። አረ ተመስገን ነው ይህችንም ታህል እንዳልረሳ ወዳጆቼ አትሌት ተስፋዬ ፋር እና የሲድኒ ኦሎምፒኩ ጀግና አትሌት ተስፋዬ ቶላ በአካልም ሆነ በስልክ ባገኙኝ ቁጥር በኦሮምኛ ባያወሩኝ ኖሮ ጉድ ሆኜ በቀረሁ ነበር ። በዚህ አጋጣሚ ሁለቱ ተስፋዬዎች ትመሰገናላችሁ ።
የሰማዕቱ ወላጅ እናት ልቅሶ በየመሃሉ እየገባ ቢያቋርጠንም እንደምንም ብለው ስለ ልጃቸው እንዲያጫውቱኝ የጠየኩዋቸውን እና እነሱም የነገሩኝን ታሪክ እነሆ ተከታተሉት ።
የሟች ሰማዕት ስሙ አወቀ ገመቹ ይባላል ። የትውልድ ዘመኑም 1979 መተ ምህረት ነው ። በ1961 ዓመተ ምህረት ጋብቻቸውን የመሰረቱት ኦቦ ገመቹ ቡባ እና አዴ ጉቱ ብርሃኑ በትዳር ዘመናቸው ካፈሩአቸው 11 ልጆች መካከል አወቀ ሰባተኛ ልጃቸው ነው ። እስከአሁን አወቀን ጨምሮ 2 ልጆች በህይወት የሌሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ልጆቻቸውም ገሚሱ ትዳር መስርቶ ገሚሱም በትምህርት ገበታ ላይ ሌላውም ራ ፍለጋ በየቦታው ተበታትኖ ይገኛል ።
አወቀ እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በወላጆቹ ቤት በእረኝነት ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ። ሌሎች ከእሱ በኋላ የተወለዱት ለአቅመ ራ ስለደረሱና የእረኝነት ሙያውን የሚያግዙት መሆናቸው ሲረጋገጥ እሱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በ1990 ዓም እንዲገባ ተደረገ ። ገመቹ በትምህርት ቤት የቆየው ለ7 ዓመታት ያህል ብቻ ነው ። ከ7 ተኛ ክፍል ወደ 8 ተኛ ክፍል እንደተዘዋወረ ትምህርቱን የሚያቋርጥበት አጋጣሚ ተፈጠረ ። አጋጣሚውንም አባቱ አዛውንቱ አቶ ገመቹ እንዲህ በማለት ይናገራሉ ።
"እርግጥ ነው ገጠር ነውና ያለነው በገጠር ደግሞ ለገበሬ ልጅ እንደ ሃብትም የሚቆጠር በመሆኑ በተከታታይ 11 ልጆችን አፍርተናል ። በዚህም ምክንያት እናት በወሊድ ምክንያት ህመምተኛ በመሆኗ እኔም አቅም እያጣሁ በመምጣቴ ምክንያት ለልጆቻችን የሚያስፈልጉአቸውን ነገሮች ለሟሟላት አቅም ማጣት ጀምርን ።
ይህ የእጅ ማጠርና የአቅም ማጣት ደግሞ በቤተሰቡ አባላትና በዘመድም ዘንድ እየታየ መጣ ። በዚህን ጊዜ ነው እንግዲህ ቀድማ ወደ ሱዳን ሄዳ የነበረች የባለቤት ወንድም ልጅ እዚህ በመምጣት በሱዳን ስላለ ሥራ በማውራት የሟችን እና ሌላ የወንድሜን ልጅ በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ይዛቸው እንዲወጡ ያደረገችው ።
አወቀ በሱዳን ካርቱም ቆይታው ወቅት ምን እንደሚሠራ ባይነግረኝም አልፎ አልፎ ገንዘብ ይልክልኝ ነበር ። ሞባይል ስልክም ከመጣ ጀምሮ ድምፁን ያሰማንም ነበር ። " አባ አየረዞህ ጥቂት ቀን ነው አሁን ከምልክልህ ብር የበለጠ እልክልሃለሁ ይለኝም ነበር "
ለ9 ተከታታይ ዓመታት በካርቱም ምን እንደሚሠራ ሳናውቅ ከቆየ በኋላ አሁን ወደ ፈረንጅ ሀገር ሊሻገር ሲሄድ አግኝተውት ልጄን ገደሉብኝ ።
ሰዳንን ለምን እንደለቀቀ ታወቋል? የእኔ ጥያቄ ነበር ።
" አዎን በሚገባ እንጂ ። ይኸውልህ ያ የአጎቱ ልጅ አብረው ከሃገር ከወጡ በኋላ በሱዳን ለ 8 ዓመታት አብረው ቆይተዋል ። በ8 ተኛ ዓመቱ ያ ወንድሙ እስቲ ወደ ሊብያ ልሂድና ወደ አውሮፓ በመሻገር እድሌን ልሞክር በማለት ጉዞ ይጀምራል ። ታዲያ በሊብያ ብዙ መከራ ከደረሰበት በኋላ እድል ቀንቶት ወደ አውሮፓ ይገባል ። አሁን ያለውም ጀርመን ሀገር ነው ።
ጀርመን ገብቶ ዓመት ሲሆነው ለአወቀ ሱዳን ይደውልና አንተም እድልህን ሞክር ይለዋል ። እሱም እሺ ብሎ ጉዞ ይጀምራል ። ሊብያ እንደገባ በሰዎቹ እጅ ወደቀ ። እኔን አባቱን ቀና ሊያድርግ የነበረው ልጄ በጨካኞችና በአረመኔዎች እጅ ወድቆ እጁን የፊጥኝ ታስሮ ፣ እንደ ወንጀለኛና እንደነፍሰ ገዳይም ተቆጥሮ ከሌሎች የሃገሩ ልጆች ጋር በበረሃ አናቱን በጥይት አፍርሰው ረሸኑብኝ ። ..... ቤቱ በልቅሶ ተሞላ ። በተለይ እና
እንደምንም አረጋግቼ መሞቱን እንዴት እንደሰሙ ጠየቅኳቸው ።
ያው ወንድሙ ነው አረጋግጦ የነገረን ። መጀመሪያ እሱ እንደተያዘው ተይዞ ፣ እሱ እንዳመለጠው አምልጦ ፣ እሱ የገባበት ሀገር ይገባል ተብሎ ነበር የምንጠብቀው ። በመሃል ድምፁ ጠፋ ። የልጆቹን መታረድ ስንሰማ ደግሞ የባሰ ደነገጥን ፣ ለወንድሙ እስቲ አጣራና እርማችንን እናውጣ አለነው ። እሱም አጣርቶ ጥቁር ቱታ አልብሰው አንበርክከው የገደሉበትን ፎቶ ልኮ ማረፉን አረዳን ። ይኸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መኖር አስጠላኝ ። እናቱም ሀዘን ድቅቅ አድርጓት ህመምተኛ ሆና ቀረች ። እንደገና ልቅሶ ሆነ ።
የጠየቃችሁስ አለን አልኳቸው? አይ ማንም የለም ። መንግስትም ህዝብም በቴሌቭዥን እንደ ልጄ በሊብያ የተጎዱትን ልጆች ቤተሰቦች ረዱ ሲባል ያው በራዲዮ እንሰማለን ። እኛ ድሆች ነን በዚህ ላይ ገጠር ነው ያለነው ማን ያስታውሰናል ብለህ ነው ።
በፊት ኦርቶዶክስ ነበርን አሁን ያው እዚህ አካባቢ ሙሉ ወንጌሎች መጥተው እዚያ ነው ያለነው ። ከቸርች መጥተው ዘምረው ሄደዋል ። ይረዱዋችሃል ተብለን ብንመላለስም ከአዲስ አበባ እስካሁን መልስ ስላልመጣ የምንረዳችሁ ነገር የለም በመባላችን ዝም ብለን ተቀምጠናል ።
እኔም እንደተለመደው ለሙሉ ወንጌሎች ይህችን መልእክት አስተላልፍላቸዋለሁ ። በአዲስ አበባ ለእማማ አለሚቱ እንዳደረጋችሁት ሁሉ ለእነዚህም ምስኪን ቤተሰቦች አድርጉላቸው ።እርዷቸው ፣ አጽናኑዋቸውም ።
መንግስትም በተለይ የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ምንም ቦታው ገጠር ከአስፓልትም ራቅ ያለ ቢሆንም ያው የገበሬ ነገር አይሆንልኝም እያላችሁ የምትነግሩንን እያሰብኩ ለእነዚህም አቅመ ደካሞች ድረሱላቸው የሚለው የተለመደ መልእክቴ ነው ።
አሁን አሰልቺውን እና አድካሚውን መንገድ አስበን ልንነሳ ስንል በፍጹም እዚህ ድረስ መጥታችሁማ ባዶ ሆዳችሁን አትመለሱም ብለው የግድ አሉን ። እኔ ግን ከጎጆዋ ውስጥ ይሸት የነበረውን የፍስክ ምግብ መሆኑን በመጠርጠሬና በማረጋገጤም ወቅቱ የፍልሰታ ም በመሆኑ እኔም ልጆቼም እንደማንበላ ነገሬ በምትኩ ከዶሮ ወጡ የበለጠ ምርጥ የባቄላ አሹቅ በኪሳችን ሞልተን ተሰናብተን ተመልሰናል ።
እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነኝ ። እንደአቅሚቲም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከአባቶቼ በታዘዝኩ ጊዜ አገለግላለሁ ። በእነዚህ ሰማዕታት ጉዳይ በብዙ ተባርኬአለሁ ። የሰው ልጅ ሃይማኖቱ ፣ ዘሩ ፣ ዜግነቱና መልኩ እየታየ መረዳትም የለበትም ።
" ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻውን በቂ ነው "
ለእነ ኦቦ ገመቹም ይህንኑ ነው የነገርኳቸው ። እነሱም ቢሆን ሰውን በሰውነቱ ብቻ እንዲረዱት ነው አበክሬ የነገርኳቸው ።
ወደ እዚህ ሰማዕታት ቤት የወሰደን የሟች ታላቅ ወንድም ቶሎሳ ገመቹ ነው ። ቶሎሳ ሥራ ፍለጋ ብሎ ወደ አዲስ አበባ ከመጣ ሰንበትበት ብሏል ። ከመሰደድ ይሻለኛል ብሎ መንጃፈቃድ ለማውጣት እየሞከረ ነው ያለው ። ነገር ግን እሱ የተማረው ቁቤ በመሆኑና አማርኛ ባለመቻሉ እንደተቸገረ ነው ያጫወተኝ ። እናም እንደመፍትሄ የያዘው አማርኛን እንደ አዲስ እየተማረ እስከዚያው በረዳትነት እየሠራ ህይወቱን ይገፋል ።
አባባን ወደ ዋዩ ከተማ ወስጄ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ አካውንት ከፍቼላቸዋለሁ ። የባንኩ ማናጀርም አባባ ፎቶ ሌላ ቀን እንደሚያመጡ ነግሯቸው ከማላውቃቸውም ከማውቃቸውም ሰዎች የተሰጠኝን ብር 49670/አረባ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር " በባንኩ ስራ አስኪያጅ እጅ እንዲረከቡ አድርጌ አደራዬን ተወጥቼአለሁ ።
ይህን ብር የሰጡኝ ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።
እናንተም ልክ ለሌሎቹ የሰማዕታት ቤተሰቦች እንዳደረጋችሁት ሁሉ ለእነዚህም ምስኪንና ደግ ልብ ላላቸው አረጋውያን ከያላችሁበት ሆናችሁ በተለመደው መንገድ ድጋፋችሁን እንድታደርጉላቸው በሰማዕታቱ ስም እለምናችኋለሁ ።
1ኛ፦ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት ተከታዮች አንድነት ( የዋልድባ ማህበር) www.savewaldba.org  
$ 500 ( 10,345 ብር) በአቶ ውብሸት በኩል በምስጢር ቁጥር 121-301-075-23 የተላ

2ኛ፦26790 ብር በእህቴ አያልነሽ/ አዩ / እና ጓደኞቿ በኩል ከሎስአንጀለስ አሜሪካ ። እንዲሁም በሌላ እናት በወ/ሮ ሮማን በኩልም የተላከ 8540 ብር እንዲሁም ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ጥቂት ምእመናን የሰጡኝን 3995 ብር በድምሩ 49670 ብር በስማቸው ባንክ አስገብቼላቸው ተመልሻለሁ ።

አቤት ያ ቤተሰብ ይህን ሲያይ እንዴት እንደተደሰተ ልነግራችሁ አልችልም ። አባባ ገመቹ ከምርቃቱ ሌላ በቃ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉ ልጆቼን አስተምርበታለሁ ብለው በደስታ ነበር እያለቀሱ ይመርቁን የነበረው ። ልጆቼ እንደዚያን ቀን ተደስተው አያውቁም ። የኦሮሞ የሀገር ሽማግሌዎች ተሰብስበው መረቁልኝ አይገልፀውም ልጆቼን ።
እኒህን ምስኪን ቤተሰቦች መርዳትና ከበረከቱ መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዋዩ ቅርንጫ
አቶ ገመቹ ቡ
የባንክ ሂሳብ ቁጥ
1000135040308 ሲሆ
ለማጽናናት በሰፈሩ አማርኛ በሚሞክረው በአቶ ነሜ ገመቹ ስልክ 00251987739346 ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ ። ያሉት ገጠር በመሆኑ የስልኩን ባትሪ ሲያልቅባቸው ረጅም ርቀት ተጉዘው ከተማ መጥተው ነውና ባትሪ ቻርጅ አድርገው የሚመለሱት ስልካቸው አልሰራልኝም ብላችሁ እንዳትቀየሙ። ያውም ቢሆን መብራት ካለ ነው ።
ታላቅ ወንድሙን ግን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በስልክ ቁጥር +251917669934 ደውላችሁ ልታወሩት ትችላላችሁ ።
ታዋቂዎቹ ዘሐበሻና ድሬ ትዩብ ድረ ገጾች በሰማዕታቱ ዙሪያ የጻፍኩዋቸውን ጽሑፎች በመላው ዓለም ላይ ለሚኖሩ አንባቢዎቻችሁ በማድረስ በሚልዮን የሚቆጠር ብር እኒህ የሰማዕታት ቤተሰቦች እንዲረዱ በማድረጋችሁ በሰማዕታቱ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ።
ያው ድሆችን በመርዳት የምትታወቀው አርቲስት ዮሴፍ ገብሬ / ጆሲም/ እንደተለመደው ትጠበቃለህ ። ኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ ቡድን አባላትም እንዲሁ ትጠበቃላችሁ ።
በተረፈ ለማንኛውም ማብራሪያ የእጅ ስልኬ 00251911608054 ባትሪ እስካልዘጋ ድረስ በማንኛውም ሰአት ክፍት ነው ።
ዘመድኩን በቀለ ነ
ነሐሴ 18/12/2007 ዓ
አዲስአበባ - ትዮጵ

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

1 comment:

  1. እግዚአብሔር ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጥልን። መምህር ዘነድኩንንም እግዚአብሔር ይስጠው።

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤