Saturday, October 3, 2015

በዋልድባ ዳልሻሐ የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክስቲያን ማሰሪያ እርዳታ


 







በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

በጥንታዊነቱ የሚታወቀውና ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የሚሄዱ መናንያን ተሰባስበው ለዓለም ሠላም፥ ለሰው ልጆች ደህንነት፥ ሠላምና ፍቅር አምላክን የሚማጸኑበት ከዋልድባ ዳልሻሕ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ውስጥ የሚቀኘው የሊቀሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታሪክና አመሠራረት ለግንዛቤ ያህል ከዚህ በታች ተመልክቷል።

ይህ የተጠቀሰው የፍድቃ ሊቀሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተመሠረተው በንጉሱ በሣልሳዊ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ሲሆን አባቶች የጸለዩበት እና ሰማዕትነት የተቀበሉበት እስከ 65 ዐበመኔት ወይም መምህራን በገዳሙ ሕግና ሥርዓት አበው ለብቃት የደረሱበት፤ ከብቃታቸውም የተነሳ፦

 
1/ ድንጋይ ከላይ ከተራራው ተንዶ ተንከባሎ ቤተክርስቲያኑን ሊያፈርሰው ሲል ገዝተው ያስቆሙ፤
2/ ምድር ለቀው የቀደሱ፤
3/ ገዳሙን ሊዘርፉ ሌቦች በመጡ ጊዜ ሌቦችን ከአፋቸው በወጣ ውግዘት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የዘረፉትን እቃ እንደያዙ ያቆሙ እንደነበር ለአብነት የሚጠቀስ ሲሆን፥ ከእነዚህ አባቶች ውስጥ አቡነ ተስፋ ኢየሱስ የተባሉት የፈረሰውን ቤተክርስቲያን ያሠሩት ደጃዝማች አጽሜ አምሳሉ የክርስትና ስማቸው አጽመ ክርስቶስ ከበቅሎ ወድቀው እግራቸው ሲሰበር በመስቀላቸው አሽተው ያዳኑበት።
በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጽላታቸው ተደርቦ ይሚገኘው የአቡነ ዮስጣጢዮስ የተባሉ ጻድቅ መስከረም 18 ቀን በዓለ ፍልሰታቸው ሲከበር እና ካህናት ለማዕጠንት ሲያውዱ ነጫጭ ንቦች ቤተክርስቲያኑን እይዞሩ የሚያውዱበት ሠርሖት ሕዝብ እስከሚሆን ማለትም ቅዳሴው ሲያበቃ ወደላይ የሚያርጉበት ገዳም ነው። ይህ ጥንታዊ የዋልድባ ዳልሻሐ ኪዳነምሕረት ገዳም አካል የሆነው የሊቀ ሰማዕት ይቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት የሚሠጠው አገልግሎት፦

1/ የገዳሙ ንብረት ማስቀመጫ፥ የዕንግዳ ማረፊያ/ መቀበያ
2/ በአብነት ት/ቤት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጡ ሊቃውንት ታንጸው የሚወጡበት (የሚፈልቁበት
ይህ ገዳም ከዘመን ብዛት የተነሳ ቤተክርስቲያኑ የተሠራው በጭቃ እና በድንጋይ ስለነበር ከ5 ዓመት በላይ ፈርሶ ቆይቷል።
ስለዚህ ይህንን ቤተክርስቲያን ለማሠራት በማቴሪያልም ሆነ በጥሬ ገንዘብ እርዳታ ታደርጉልን ዘንድ በእናታችን በቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና በኃያሉ በሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

እንዲህ በማድረግ ቡዙዎች አባቶች ተጠቅመዋልና መታዘዝ የሁሉ ምግባራት እናት ናት፥ መታዘዝ የቅዱሳን ሁሉ ምግባቸው ናት፥ በእርሷም ወደ ፍጹምነት ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት ይደረሱበታልና፥ እኛ የሰሜን ጎንደር እድርቃይ ወረዳ በዋልድባ ዳልሻሐ ኪዳነ ምሕረት ገዳም የምንገኝ አረጋውያን ገዳማውያን፥ መናንያን፥ መነኮሳት እናንተን ቡሩካን ውድ የክርስቶስ ወዳጆች የእናታችን የኪዳነ ምሕረት ልጆች ይህችን የአባቶችን ፈቃድ ለመፈጸምና ድካማቸውን ለማቃለል የምትደክሙ ሁሉ ድረብ ይሆነ ስውር ዋጋችሁ ይብዛላችሁ፥ ቤተሰቦቻችሁን ሁሉ ባሉበት በሰላም፥ በፍቅር፥ በጤንነት፥ በአንድነት ያኑርላችሁ፤ ለእኛም እንዳሰባችሁልን እናታችን ኪዳነ ምሕረት ታስብላችሁ፤ በጎደለው የማያልቅበት ቸሩ አባታችን መድኃኒዓለም ይተካላችሁ፥ የእኛን የገዳማውያን፥ የአረጋውያን ጸሎት፥ የእናንተን ምጽዋት በቸርነቱ ፈጣሪያችን ተቀብሎ ለገነት ለመንግሥተ ሰማያት እንዲያበቃን የዘወትር ጸሎታችን ነው።

የዋልድባ ዳልሻሐ ኪዳነምሕረት ገዳም ማኀበረ መነኮሳት እና አዲስ አበባ የተቋቋመ የቤተክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴ።

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።

የእግዚአብሔር በረከት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን አሜን!!

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤