Wednesday, December 21, 2016

እንኳን ለታላቁ ጻድቅ "አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ" እና ለሰማዕታት "አንቂጦስ ወፎጢኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church ምስል
ታኅሣሥ 12
 እንኳን ለታላቁ ጻድቅ "አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ" እና ለሰማዕታት "አንቂጦስ ወፎጢኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
 አባ ሳሙኤል ዘዋሊ
ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን:: በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ ቦታ አላቸው:: 20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6 ሳሙኤሎች ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል : ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል::
እነዚህም:-
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው::

Sunday, November 20, 2016

እንኳን ለጾመ ነብያት መባቻ በሰላም አደረሰን


ሥጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለሥጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነዉ፡፡ሆኖም የጾም ወቅት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም ማንኛዉም ሰዉ ጾሙን ሲጀምር የሚከተሉትን ጉዳዮች በደንብ ሊያጤናቸዉ ይገባል፡፡

Sunday, November 13, 2016

የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት አመራር አባላት ከSBS አማርኛ ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት አመራር አባላት ከSBS አማርኛ ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ተከታተሉት “ዓላማችን የዋልድባ ገዳምን መታደግ ነው”

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Friday, October 7, 2016

ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች አቡነ አብርሃምን አነጋገሩ፤ “ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት”/ብፁዕነታቸው/

 • በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ፣ መንግሥት ምን ማድረግ እንደሚገባው፣አባታዊ ምክር ሰጥተዋል
 • መናገር ያለብኝን ነው የተናገርኩት፤ ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት፤” ብለዋል
  *               *               *
 • ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ሰው አላት ያሰኘና እውነትን መሠረት ያደረገ ወቅታዊ መልእክት ነው
 • ኹሉም ብፁዓን አባቶች፣ እንዲኽ፣ የኅሊናቸውን እውነት የሚናገሩበት ቀን ሩቅ አይኾንም!!
/አስተያየት የሰጡ ምእመናን/
Aba Abre
በብጹዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር፥ የም/ጎጃም፥ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

Sunday, September 18, 2016

የወቅቱ የሃገራችንን ሁኔታ በተመለከተ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ

                                         የወቅቱን የአገራችንን ሁኔታ በተመለከተ
ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የተሰጠ መግለጫ

መግለጫውን በPDF ለማንበብቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ ህዝቦቿን በፍቅርና በባህል በማስተሳሰር ነፃነቷንና አንድነቷን ጠብቃ የኖረች በየትኛውም የውጪ ወራሪ ያልተንበረከከች ለአፍሪካና ለጠቅላላ የጥቁር ዘር ፋና ወጊ የሆነ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት አገር ናት በዚህም የረጅም ዘመን ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉልህ አሻራ አላት ።ይህም  በውጪ አገር ጸሐፊዎች ሳይቀር ተመስክሮላታል።

Tuesday, August 9, 2016

ጸሎት እና ምሕላ በሃገራችን ኢትዮጵያ ለሚደርሰው መከራና ችግር ወደ ፈጣሪ ለማመልከት

"በግብጽም ሳሉ የአባቶቻችንን መከራ አየህ፤ በኤርትራ ባሕርም ሳሉ ጩኽታቸውን ሰማህ" መጽሐፈ ነህምያ ፱ ፥ ፱
ዛሬ ኢትዮጵያ ሃገራችን እየደማች እና እያነባች ትገኛለች፥ ልጆቿም በግፍና በመከራ ውስጥ እየተጓዙ ይገኛሉ። እግዚአብሔር አምላክ ይህን
የመከራ ዘመን ያሳልፍልን ዘንድ በዚህ የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ ትንሣኤዋን በሚታሰብበት የሱባኤ ወቅት መከራችንን እግዚአብሔር
አምላክ እንዲያስወግድልን ማሳሰብ የክርስቲያን ተግባር ነው። በመሆኑም
ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ)

 ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (August 7 - 19, 2016) 9:00 pm. EST Washington, DC time or 6:00 pm. PST. California time ጀምሮ በጸሎት እና በምህላ ወደ እግዚአብሔር እንድናመለክት እንድናሳስብ በመላው ዓለም ለሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ ጥሪ እናደርጋለን።

እያንዳንዳችን ለወገኖቻችን የችግር ቀን ደራሽ ሆነን መገኘታችን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ሁሉን ወደ ሚችለው የኢትዮጵያ አምላክ ወደ ልዑል 
እግዚአብሔር እጆቻችንን በጸሎት እና ምህላ እንድናነሳ መንፈሣዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" መዝሙር ፷፰ ፥ ፴፩

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Friday, August 5, 2016

ሱባኤ፣ምንነቱ፣ሥርዓቱ

እንኳን ለቅድስተ ቅዱሳን፣ ንጽህተ ንጹሃን ቅዱስት ድንግል ማርያም መታሰቢያ የፍልሰቷን ጊዜ እያሰብን በሁለት ሱባኤ ወደ አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ ስም አማላጅነቷን የምንለምንበት ልዩ እና የተመረጠች የሱባኤ ወቅት በመሁኗ ከሁሉም አጽዋማት የተለየች ያደርጋታል። በዚህም ወቅቱ የሱባኤ ጊዜ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች አሮጊት ሽማግሎ በሙሉ የሰው ልጅ በሙሉ እየጾመ የእመቤታችንን አማላጅነት እየተማጸንን ወደ ፈጣሪ የምንጮህበት ታላቅ ጊዜ ነው። ታዲያ ስለ ሱባኤ ስናወራ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ሰዎች ሱባኤ ምን እንደሆነ ለምን ሱባኤ እንዳስፈለገ ወይንም ሱባኤ እንዴት እንደተጀመረ ሲጠይቁ ይሰማል እኛም ምዕመናን ቢማሩበት ብለት ይህንን ካነበብነው ለማቅረብ ወደድን።  

                                   ሱባኤ፣ምንነቱ፣ሥርዓቱ
                                      ሥርዓተ ሱባዔ

ሱባዔ ምንድን ነው? ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ሽለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2.2 መዝ.118.164፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም «አንድ ሱባዔ ጾመ» ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም «ሁለት ሱባዔ ጾመ» እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

መቼ ተጀመረ?

Friday, July 29, 2016

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዓል ወርሃዊ መታሰቢያ አደረሳችሁ

ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም

የድንግል ማርያም ስሞች
ስም ለፈጣሪም ሆነ ለፍጡራን ለመጠሪያነት ያገለግላል፡፡ ይህም ስም አንዱን ከሌላው ለይቶ የሚያሳውቅ የፍቅር
መግለጫ ነው፡፡ በጽሑፍም ሆነ በቃል ማስተላለፍ የሚቻለው በስም አማካኝነት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ለሚወዳቸውና ለመረጣቸው ሰዎች ስም ያወጣ እንደ ነበር ሁሉ፤ ሰዎችም ያወጡ መጠሪያ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህም ስም የሚሰየመው ወይም መጠሪያ ሆኖ የሚሰጠው እንዲሁ በዘፈቀደ ሳይሆን መሠረታዊ ምሥጢርና ትርጉም አለው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን «እስመ ስሙ ይመርህ ኀበ ግብሩ» በማለት ስም ግብርን ሁኔታን እንደሚገልጽ መሥክረዋል፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ምስክርነት ከስም አጠራሯ በመጀመር ለስመ ድንግል ማርያም ዘርፍ /ቅጽል/ አልያም ምትክ አድርገን የምንጠቀምባቸው ምሥጢራዊና ትርጉም ያላቸው ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ድንግልናዋን፣ ወዘተ የሚመሰክሩ በርካታ ስሞች አሏት፡፡ ስለ እመቤታችን ስሞች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካላቸው ፍቅር የተነሣ አብዝተው፣ አምልተው፣ አስፍተው፣ አመስጥረው ከተረጐሙት ጥቂቱን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

Thursday, June 16, 2016

በጅማ ሃገረ ስብከት በሰኮሩ ወረዳ ቁንቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ላይ በአክራሪ እስልምና አራማጆች የደረሰው ሰቆቃ

" አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ"
(ሰቆቃው ኤርምያስ 5:1)
በጅማ ሃገረ ስብከት ሰኮሩ ወረዳ ቁንቢ ቀበሌ ውስጥ በሚገኘው ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ–ክርስቲያን በ08/10/2008 ዓ·ም ንጋት ላይ ኪዳን ለማድረስ ከሄዱት ምዕመናን መካከል ወሰንየለሽ ፍቃዱ እና ወለላ ፍቃዱ የተባሉ እህትማማቾች ላይ "ጀሀድ" በሚል አላማ አራት ግለሰቦች መላ ሰውነታቸውን በጥቁር ልብስ በመሸፈን ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል።ይህ የግድያ ሙከራ የተደረገው ከ20 የማይበልጡ ክርስቲያን አባውራ በሚኖሩባት የቁንቢ ቅ/ሚካኤል ቤተ–ክርስቲያን የተፈፀመ አስከፊ ጥቃት ሲሆን ከአራቱ ጥቃት አድራሾች ሦስቱ ባዘጋጁት መኪና ወደ ጅማ መስመር ያመለጡ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁልን "መሐመድ ሰኒ" የተባለው አክራሪ በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል።አክራሪዎቹ ጥቃት ያደረሱበት የስለት መሳሪያ በአብዛኛው የአረብ አገራት ላይ በስፋት የሚታይ ሲሆን መርዛማ መሳርያ መሆኑም ታውቋል።ክርስቲያኖችን ማጥፋት አላማቸው አድርገው የመጡት አክራሪ ቡድኖች ክርስቲያኖችን በሰይፍ ሲያርዱ በዝምታ መመልከት ያላስቻላቸው የአካባቢው ሙስሊም ወንድሞች በመሀል በመግባት በሚያገላግሉበት ወቅት ሁለቱ ሊጎዱ ችለዋል።ጉዳቱ ከደረሰባቸው ከሁለቱ እህትማማቾች አንዷ የሆነችው ወሰንየለሽ ፍቃዱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በአሁኑ ሰአት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ ትገኛለች።የኢ/ኦ/ተ/ቤተ–ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስን ጨምሮ የተለያዩ ብፁአን አባቶች እንዲሁም ብዛት ያላቸው ምዕመናን በጥቁር አንበሳ በመገኘት እህታችንን በመጠየቅ እና በአደጋው የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን እየገለፁ ይገኛሉ። 
በዚህ መጠነ ሰፊ በሆነው ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦች፣ ምዕመናን እና ምዕመናት ብሎም በጅማ ሃገረ ስብከት በተፈፀመው የፅንፈኛ አክራሪ ቡድን የመግደል ሙከራ ዋልድባን እንታደግ (ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት)ልባዊ ሀዘናችንን እየገለፅን አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ለተጎዱት እህትና ወንድሞች ፍፁም ምህረትን እንዲሁም ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንዲሰጥልን እናመኛለን!!!

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Thursday, June 9, 2016

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ እስከ ሰኔ 30 የዕጩዎችን ዝርዝር ያቀርባል፤ የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል

Holy Synod00
ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት፣ ላለፉት 16 ቀናት ሲያካሒደው የቆየውን የ2008 ዓ.ም. የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡
ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው ጉባኤው፣ ዛሬ፣ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የተጠናቀቀው፣ ባለ17 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ነው፡፡
በቅዱስ ሲኖዶሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መግለጫውን በንባብ ያሰሙት ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቀሜታ ባላቸው አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቀዋል፡፡
ከውሳኔዎቹ ዓበይት ነጥቦች መካከል፣ የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በምልአተ ጉባኤው የታመነበት ሲኾን፤ በዕቅዱ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በአስረጅነት የሚገኙበትና ሰባት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉ ተገልጧል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው፣ ዕጩ መነኰሳቱን፥ መርምሮ፣ አጥንቶና አጣርቶ ውጤቱን እስከ ሰኔ 30 ቀን እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡ በዕጩነት የሚቀርቡት ቆሞሳትና መነኰሳትም፡-
 • ፈተናውንና መሰናክሉን ኹሉ አልፈው ዕውቅና ያገኙትን፤
 • በብሔር አቀፍና በዓለም አቀፍ ትምህርት የበሰሉትን፤
 • የወቅቱንም ችግር ይፈታሉ ተብለው እምነት የተጣለባቸውንና የሚጣልባቸው መኾን እንደሚገባቸውም በመግለጫው ተዘርዝሯል፡፡


Friday, May 27, 2016

የእንደራሴ ምደባ በፈጠረው መካረር ስብሰባው በድንገት ተቋረጠ፤ ፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ አዝነውበትና ጸልይውበትይወስኑበታል

his holiness abune Mathias
“ኃይል አለኝ፤ ነገር ግን መጠቀም አልፈልግም” በሚል በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ ዝተዋል
 • ምደባው፥ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግና አደራን የመጠበቅ ጉዳይ እንደኾነ ተገልጧል፤
 • የልዩ ጽ/ቤትና የአ/አበባ ሀ/ስብከት አጀንዳዎች እንዲሰረዙ በያዙት ተቃውሞ ቀጥለዋል፤
 • አንሡኝ!”ላሉበት አቋማቸው፣ “ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ እናደርገዋለን!” ተብለዋል፤
 • በጎጥና በጎሳ ለማሸማቀቅ የሞከሩ የምልዓተ ጉባኤው አባላት በከፍተኛ ደረጃ ተገሥጸዋል፤
*               *               *

Tuesday, May 10, 2016

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!

 ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!

ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር። እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ። እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረላቸው ባለጸጎች ነበሩ። ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ።
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ለመኑ ዘዘገብነ ዘንተ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ - ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም” አላት። እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳን ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት። እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በሕልሜ ርኢኩ በሕልምየ ጸዓዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርስየ - ነጭ ጥጃ ከማኅጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ ፯ት
ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው።

Saturday, April 16, 2016

፯ኛው የዓብይ ጾም ሳምንት “ኒቆዲሞስ”

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡ ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች ፡፡ ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡
ኒቆዲሞስ ማነው?
፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው ዮሐ 3-1

በአብረንታንት ዋልድባ የመጋቢት መድኃኒዓለም ተሳላሚዎች በታጣቂዎች ተዘረፉ

መቆየት ጉድ ያሰማል
·         ለመጋቢት መድኅኒዓለም ክብረ በዓል የመጡ ምዕመናን በመንግሥት ታጣቂዎች ንብረታቸው ተዘርፏል
·         ዓመታዊው የአበረንታንት መድኅኒዓለም ክብር እጅግ በጣም የሚታወቅ እና በርካታ ምዕመናን በሚመጡበት ጊዜ ትግርኛ ተናጋሪ ታጣቂዎች የመልቃይት ታጣቂዎችን እንፈልጋለን በማለት ቀን በቀን ምዕመናን ሲንገላቱ፣ ሲዘረፉ፣አድዳንዱም ሲደበደቡ ነበር
ባለፈው የመድኅኒዓለም ክብረ ለማክበር ወደ ዋልድባ አበረንታንት ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ምዕመናን እናቶች፣ አባቶች፣ ወንድሞች እና እህቶች ትግሪኛ ተናጋሪ በሆኑ የመንግሥት ታጣቂዎች በሆኑ ሰዎች መንገድ በመጠበቅ በርካታ ምዕመናን ሲያንገላቱ እና ሲያስጨንቁ እንደነበር የዓይን እማኞች ገልጸዋል፣ እነዚህ ሰዎች የመንግሥት ተወካዮች ነን፣ የምንፈልገውም የወልቃይት ታጣቂዎችን ነው በማለት የሚመጣውን ምዕመን በሙሉ ከላይ እስከ ታች በመፈተሽ በእጃቸው የገባውን ገንዘብ፣ ካሜራ፣ የእጅ ስልኮችን ጨምሮ ከምዕመናን ላይ በመንጠቅ ሲወስዱ እና ምዕመናን ሲያንገላቱ እንደነበሩ በወቅቱ በስፍራው ከነበሩ እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸውልናል።
ዛሬ ዛሬ የታላቁን የወልድባን ገዳም እናንተ የትግራይ ተወላጆች አይደላችሁም፣ ይሄ የትግራይ መሬት ነው በማለት በበርካታ ገዳማውያን ላይ እና ምዕመናን ላይ በሙሉ ብዙ መከራ ሲያደርሱ እና ሲያሰድዱ እንደነበር ለበርካታ ጊዚያት እኛም በድኅረገጻችን ለምዕመናን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል፥ የእስከ ዛሬውም በግልጽ ባልሆነ ጉሰማ እና በተለያዩ ዘደዎች በመጠቀም በተለይ ገዳማውያን አባቶችን እናንተ ወደ ክልላችሁ ተመለሱ በማለት ብዙዎችን ሲያሰድዱ እና ሲያስሩ ሲገርፉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። እነዚህ እምነት የሌላቸው አሪዎሳውያን እስከ ዛሬ ባለው በተለያዩ የገዳሙ አባቶች እና መነኩሳይት ላይ ሲያደርሱት የነበረው ይህ ነው የማይባል ግፍ እና በደል ሲፈጽሙ መቆየታቸው ሳያንሳቸው ዛሬ ደግሞ እምነቱን፣ እና በረከት ፍለጋ የመጣውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት አማኞችን በእንዲህ አይነት መልክ ቀን በቀን፥ በጠራራ ጸሐይ መዝረፍ እና ማንገላታት ይቅርታ የማያሰጠው በደል እንደሆነ ማናቸውም በወቅቱ በደል ከደረሰባቸው በአጠቃላይ መላው ምዕመናን በመላው ዓለም የሚገኝ ሁሉ የሚስማማት ጉዳይ ይመስለናል።