Monday, January 25, 2016

በ“ኦርጋን ብንዘምር ምን አለበት?


በ“ኦርጋን” ብንዘምር ምን አለበት? ከጥንት ጀምሮ “የምን አለበት?” መዘዙ ብዙ ነው፥የግድ የለሾች መፈክር ነው።“እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ ኃጢአት ብሠራ ምን አለበት?” እንደ ማለት ነው።ንስሐ ከመግባት ይልቅ እግዚአብሔርን መሞገት የፈለገ ሰው፡-“ኰንኖ ኃጥአን ኵሎሙ ኢይደልወከ ምንተ ፥አፍቅሩ ጸላእተ ክሙ እንዘ ትብል አንተ ፤ፈራጅ ዳኛ እግዚአብሔር፡-በጠላቶችህ ኃጥአን ላይ ልትፈርድ አይገ ባህም፥አንተ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብለሃልና፤” በማለት እንደተናገረውም ሊሆን ነው።ወይም ሲቆርብ ሲያቆርብ የኖረ በደለኛ ሰው፥ንስሐ ከመግባት ይልቅ፡-“ዘበልዐ ሥጋየ ወዘሰትየ ደምየ፥ ቦ ሕይወት ዘለዓለም የሃሉ ምስሌየ፤ብለህ ተናግረህ፥በወንጌል ተጽፎ ይገኛል ቃልህ፤ይኸንን ተላልፈህ ተኰነን ብትለኝ፥አብረን እንወርዳለን እኔ ምንቸገረኝ፤” በማለት እንዳፌ ዘው መሆኑ ነው። 

-አዳምና ሔዋን በምክረ ከይሲ ተነድተው፥በምን አለበት? የዕፀ በለስን ፍሬ መብላታቸው አልጠቀማቸውም። ዘፍ፡፪፥፲፯።ቃየል ሥርዓተ መሥዋዕትን ንቆ በምን አለበት? ያቀረበ ውን መሥዋዕት እግዚአ ብሔር አልተቀበለውም፤ወንድሙንም በምን አለበት? ገድሎታል።ዘፍ፡፬፥፫።ዔሳው በምን አለበት? ሥርዓተ ብኵርናን በማቃለሉ፥በረከተ ምርቃትን አጥቶአል።ዘፍ፡፳፭፥፴፬።ዳታን፣አቤሮንና ቆሬን በምን አለበት? ሥርዓተ ምስፍናን እና ሥርዓተ ክህነትን በመ ጋፋታቸው፡-መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው፥እሳትም ከሰማይ ወርዳ፡-አቃጥላ ገደለቻቸው እንጂ አልተጠቀሙም።ዘኁ፡፲፮፥፩-፶።አካን በምን አለበት?ከኢያሪኮ ምርኰ ወስዶ በመደበቁ፥እግዚ አብሔር ገልጦበት፥በድንጋይ ተቀጥቅጦ ሞቶአል።ኢያ፡፯፥፲፰።የአሮን ልጆች ናዳብና አሚናዳብ ፡-በምን አለበት?ከሥርዓቱ ውጭ፥እግዚአብሔር ባላዘዛቸው እሳት የዕጣን መሥዋዕት በማቅረ ባቸው፥እሳት ከሰማይ ወርዶ፥ተቃ ጥለው በእግዚአብሔር ፊት ሞተዋል።ዘሌ፡፲፥፩።የዔሊ ልጆች አፍኒን እና ፊንሐስ፡-በምን አለበት?ወደ እግዚአብ ሔር ቤት ከሚመጡ ሴቶች ጋር በማመንዘራ ቸው፡-እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያን አስነሣባቸው፥እነርሱም በጦርነቱ ላይ ሞቱ፥ታቦተ ጽዮንም ኃይሏን በእሕዛብ ምድር እስክትገልጥ ድረስ ተማረከች።ሊቀ ካህናቱ ዔሊም ከሥር ዓተ ቤተ መቅደሱ ይልቅ ለልጆቹ በማድላቱ፡-ከወንበር ወድቆ፥አንገቱ ተቆልምሞ ሞቶአል። ፩ኛ፡ሳሙ፡፬፥ ፩-፳፪።ንጉሡ ዖዝያን፡-ሥር ዓተ ክህነትን እና ሥርዓተ ቤተ መቅደስን በምን አለ በት? አቃልሎ፥ጥና ይዞ ለማ ጠን ወደ ቤተ መቅደስ በመግባቱ እግዚአብ ሔር በለምጽ ቀስፎ ታል።“እርሱ ደግሞ እግዚአብሔር ቀስፎት ነበ ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ፤”ይላል።፪ኛ፡ዜና፡፳፮፥ ፲፯።ዖዛ፡-በምን አለበት? የእግዚአብሔርን ታቦት በመያዙ፥የእግ ዚአብሔር ቍጣ እንደ እሳት ከነደደበት በኋላ በታቦቱ ፊት ሞቶአል ።፪ኛ፡ሳሙ፡፮፥፩-፲፩።የቤት ሳሚስ ሰዎች ካህናት ሳይ ሆኑ በምን አለበት? የእግዚአብሔርን ታቦት ገልጠው በማየታቸው፥ እግዚአብሔር፡-ከሕዝቡ መካ ከል ከአምስት ሺህ ሰዎች ሰበዓውን በሞት ቀጥቶአቸዋል።ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቅጣት አይተው አለቀሱ፤“ በዚህ በቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማን መቆም ይችላል?” አሉ።በዚህምበታቦት ፊት መቆም፡-በእግዚአ ብሔር ፊት መቆም፥ታቦትን መድፈር ደግሞ፡-እግ ዚአብሔርን መድፈር መሆኑን መስክረዋል።፩ኛ፡ሳሙ፡፮፥፲፱። ንጉሡ ሳኦል፡-ነቢዩ ሳሙኤል፡- “ወደ አንተ መጥቼ መሥዋዕት እስክሠዋ ድረስ ሰባት ቀን ትቆያለህ፤”ያለውን ትእ ዛዝ አቃልሎ ፥በምን አለበት ሠውቶ በመቆየቱ፡-“እግዚአብሔር ያዘዘህን አልጠበቅህምና መንግሥትህ አይጸናም ፤”ብሎታል።፩ኛ፡ሳሙ፡ ፲፥፭፤፲፫፥፰።አማሌቃውያንን እንዲወጋ በታዘዘ ጊዜ፥ምርኰ እንዳ ይሰበስብ ተነግሮት ነበር።እርሱ ግን በምን አለበት?ምርኰ ሰበሰበ፥እግዚአብሔርም ተቆጣበት። ነቢዩ ሳሙኤል ቢጠይቀው፡-“የሰባ የሰባውን ከብት ለእግአብሔር እሠዋለሁ ብዬ ነው፤ ”አለው።ነቢዩም፡-“እግዚአብሔር ናቀህ፤”አለው፥ርኵስ መን ፈስም ተቆራኝቶት ተሠቃየ።፩ኛ፡ሳሙ፡፲፭፥ ፩-፴፭።የናቡከደነጾር ልጅ ብልጣሶር፡-በምን አለበት?በቤተ መቅደሱ ንዋያተ ቅዱሳት በመመ ገቡ እግዚአብሔር ተቆጣበት፥ዕለቱኑ በጠላቶቹ ተገ ደለ።ዳን፡፭፥፩-፴፩።ሐናንያና ሰጲራ ፡-ሥር ዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ሙሉ ሀብታቸውን ማስረከብ ሲገባቸው በምን አለበት?ግማ ሹን ደብቀው አስቀሩ።ቅዱስ ጴጥሮስ በጠየቃቸውም ጊዜ በምን አለበት?በመዋሸታ ቸው በየተራ ተቀስፈው ሞቱ።የሐዋ፡፭፥፩-፲፩።የአስቄዋ ልጆች ደግሞ ጸጋውም ሥልጣኑም ሳይኖራቸው፥በምን አለበት?አጋንንት ለማስ ወጣት ተሰለፉ።“ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፡-ኢየ ሱስን አውቀዋለሁ፥ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፥እናንተስ እነማን ናችሁ?”አላቸው፥ እስኪቆስሉ ጨርቃቸውንም ጥለው እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው፥አሸነፋቸውም፤” ይላል። የሐዋ፡፲፱፥፲፬። እንግዲህ ከላይ እንዳየነው የምን አለበት? የምን ችግር አለው? መዘዙ፡-ብዙ፥የብዙ ብዙ ነው። በኦርጋኑ ብቻ የሚ ያቆም አይደለም፥ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፡-ሙሉ በሙሉ ወደ ፕሮቴስታንት ነት እስክትለወጥ ድረስ የሚቀጥል ነው።ባለፈው፡-የቀድሞው አባ ሀብተ ማርያም የአሁኑ አባ መልከ ጼዴቅ፡-በንጉሡ ዘመን ኦርጋኑን ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የማስገባታቸውን ገድል ተናግረዋልያልተናገሩት፡- ኦር ጋኑ ገብቶ ስንት ሰው ከቤተ ክርስቲያን እንዳስወጣ፥ስንት ሰው ወደ ፕሮቴስታንትነት እንደተለወጠ ነው። የሃይ ማኖት አበው ማኅበር፥ የአዲስ አበባ የልደታ ሰንበት ት/ቤት፥የባህር ዳር ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት፥የሀረር ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት አባላት የነበሩት አሁን ያሉት የት ነው?እርሳቸው ባይናገሩትም፡-የፕሮቴስታንት ፓስተ ሮች፡-በየጋዜጦቻቸውና በየመጽሔቶቻቸው ከእኛ ጋር ተቀላቅለዋል እያሉን ነው፥“ማኅበረ ቅዱ ሳን እንቅፋት ባይ ሆንብን ኖሮ እስከ ዛሬ ኦርቶዶክስን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረናት ነበር፤” እያ ሉን ነው።እነ “አባ” ዮናስ ዛሬ የፕ ሮቴስታንት መጋቢ ናቸው።እነ መልአኩም የፕሮቴስታንት ፓስተር ከሆኑ በኋላ ለምን ተመልሰው የኦርቶዶክስ ቄስ እንደሆኑ፥የሚያውቁት፡-ፕሮቴስታንቱ መልአኩና ክህነት የሰጡት አባ መልከ ጼዴቅ ብቻ ናቸው።እኛም እና ውቃለን፥ትናንት ያቆሰሏ ትን ቤተ ክርስቲያን ለመግደል ነው።ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን፡-ሞትን ድል አድርጐ የተ ነሣ አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ አካል በመሆኗ አትሞትም።ይህ አውነት ነው፥ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እግዚአብ ሔር ያስነሣው የእውነት ምስክር ነው።
ምንጭ: ከመልዓከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ የፊስ ቡክ ገጽ 

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

1 comment:

  1. lshafe kale hiwet yasamalen eragem yagaleglot gza kmwelw tanenat gare yestelen !! ewenet new lezech btchrectian yhan mheber egezabher bysnsalen newera yt neber medrsachen dgaza abatewech endh yalweeten ykert kan yorthiodox twhedow legwechen tketw yalfalew wa mchersachen yahenew abatwech are tmelesw klebach atasblewen btkula tabkewen adrachewn atersew ezgwe mharene crestos!! bent Maryam mharen crestos!! bent sadkan smaetat mharen crestos!!lgacachenne tbekeken aman!!

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤