Monday, January 25, 2016

አምስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት

http://orientalorthodox.blogspot.com/p/blog-page.html 

አምስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ አሁን ስድስት ሆነዋል፥የኢትዮጵያ፣የኤርትራ፣የግብፅ፣የሕንድ፣የሶርያ እና የአርመን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በእምነት እና በሥርዓት አንድ መሆናቸው የታወቀ የተረዳ ነገር ነው።እንዲህም ሲባል በሌሎች ዘንድ የሌለ፥ እኛ ብቻ ያለን ብዙ ነገር መኖሩን ከማስተዋል ጋር መሆን አለበት።ምክንያቱም እግዚአብሔር፡-ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሰጣት ጸጋ ብዙ ነው ።የቅዱስ ያሬድ ዜማ የተሰጠው ለእኛ ነው፥ለሌሎቹ ስላልተሰጠ ወይም በእነርሱ ቤተ ክርስቲ ያን ውስጥ ስለሌለ እንጣለው?በአጠ ቃላይ ሥርዓተ ማኅሌቱና ሰዓታቱ በእነርሱ ዘንድ ስለሌለ የእኛን እንተወው?ታቦትም የተ ሰጠው ለእኛ ብቻ ነው።ከእኛ የሚጠበቀው እግዚአብሔር በሰ ጠን ጸጋ መጽናት፥የተሰጠንን አደራ መጠበቅ ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡-ጢሞቴዎስን -“ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤ ይህ እውቀት አለን ብለው፥አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና።ያለው ለዚህ ነው።፩ኛ፡ጢሞ፡፮፥፳።ዳግመኛም፡-“መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ፤ብሎታል።፪ኛ፡ጢሞ፡፩፥ ፲፬።እግዚአብሔር የሚጠይቀን በሰጠን እንጂ ባልሰጠን አይደለም።አንድ የተሰጠው፥ ሁለት የተሰጠው፥አምስት የተሰጠው አለ።ማቴ፡፳፭፥፲፭።ኢትዮጵያ፡-ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት፥ከሕገ ኦሪት ደግሞ ወደ ሕገ ወንጌል የተሸጋ ገረች ሀገር ናት።በመሆኑም በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላታል።እኛ ሁላችን ከሙ ላቱ ተቀበልን፥ በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና፤ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ፤ይላል።ዮሐ፡፩፥፲፮።ስለሆነም ንባቡን ይዛ ኑራ ከትርጓሜው የደረሰች ቤተ ክርስቲያን በሁሉ ባዕለ ጸጋ ናት ።የሐዋ፡፰፥፳፮።ከዚህም የተነሣ ከጥንት ጀምሮ የተከፈተባትን የመናፍቃ ንን እና የአሕዛብን ውጊያ ተቋቁማ ጸንታ ኖራለች ትኖራለችም።ጠላቶቿን ስትከላከል የኖረችው ደግሞ በትምህርተ ሃይማኖቷ እና በሥርዓቷ፥ በታ ሪኳ እና በትውፊቷ ነው።የራሷ የሆነ ጸጋ ስላ ላት፥ተመሳስለው መንጋዋን ለመቀላቀል ለሚፈልጉ ተኵላት አትመ ችም፥ ለዚህ ነው አገኝ አጣ ውን እየወረወሩ፥ዙሪያውን የሚንጫጩት።መናፍቃኑ ወደ ሌሎቹ አብያተ ክርስቲያ ናት ተመሳስ ለው ለመግባት ብዙ አልተቸገሩም።ለምሳሌ፡-የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ብንመለከት፥ መናፍቃኑ በተሀድሶ ስም ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋት ስለ ነበር፥ሕዝቡ፡-በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት መካከል ያለው የሃይማኖትና የሥርዓት ልዩነት ጠፍ ቶባቸው፥የጸኑትና ያልጸኑት ለሁ ለት ተከፍለው ነበር።በመጨረሻም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ፥ተሀድሶዎቹና ኦርቶዶክሶች፥የአ ንዲቷን ቤተ ክርስቲያን፡-ሕንፃና ንብረት ለሁለት ተካ ፍለዋል።የተቀሩትም አኃት አብያተ ክርስ ቲያናት በተለያየ ጊዜ በተሀድሶ እንቅስቃሴ በጣም ተጐድተዋል። ለም ሳሌ፡-በአስመራ ቅዳሴ የአ ረጋውያን ነው ተብሎ ወጣቶች አያስቀድሱም ነበር። ቅዳሴው ካለፈ በኋላ ግን ተሰብ ስበው የፕ ሮቴስታንቱን መዝሙር ያቀልጡት ነበር፥በመጨረሻም ጌታን የተቀበላችሁ እጅ አውጡ ይባል ነበር። በየክፍለ ሀገሩ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት፡-የመምህር ጥያቄ ሲያነሡ፥ቄስ እገሌ፣ዲያቆን እገሌ እየተባሉ የሚላኩላ ቸው፥የሙሉ ወንጌል ፓስተሮች ነበሩ። እነዚህ ነገረ ኦርጋን ያንገበገባቸው ሰዎች፡-ለነገረ ክርስቶስ፥ለነገረ ማር ያም እና ለነገረ ቅዱሳን ግድ የላቸውም።ኦር ጋንን የምትጠቀመው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብትሆን ኖሮ፥ዓይ ናቸውን አፍጥጠው፡-“መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የለም፤ብለው ከመከራከር ወደ ኋላ አይሉም ነበር። ለመሆኑ ተሀድ ሶዎቹ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን እንደ አብነት ለመጥቀስ ሞራሉን ከየት አመጡት፥አለማፈራቸው ይገር መኛል።ምክንያቱም፡-የኦርቶዶክስን መለያ ለብሰው ለፕሮቴስታ ንት የሚጫወቱ ናቸውና ነው።ከጥንት ጀምሮኦርጋን፥ኦርጋንያሉ ሰዎች፡-አሁን ያሉት የፕሮ ቴስታን አዳራሽ እንደሆነ ባለፈው ጽሑፌ ላይ ጠቅሻለሁ።የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደ ርቅ፤እንደተባለው ሆኖ ነው እንጂ፥እነርሱም ያውቁታል።ልብ ካላቸው ዋናውን ክህደታቸው ንም በየድረ ገጹ በብዕር ስም ከመጻፍ በትክክለኛው ስምና አድራሻ ይጻፉት።የፕሮቴስታንቱን መቀ በላቸውን በግልጽ ያውጁ።ታቦታቸውን፡-ጊታርን ከሚያደክሙት እነርሱ ጓዛቸውን ጠቅል ለው እርሱ ወደ አለ በት ይሂዱ።ከእኛ የሚጠበቀው የአባቶቻችንን እምነት እና ሥርዓት ሳይከ ለስ እና ሳይበረዝ መረከብ ነው።ዛሬ እንደ አዲስ የምንጀምረው ምንም ነገር የለም።የተቀደሱት አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ሁሉን ነገር አስተ ካክለውልን ሄደዋል፥ያንን መከተል ነው። የቀደሙት አባቶቻችን እና እኛ፥እንዲሁም እሰከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚነሡ አባቶታችን አንድ አይነት እም ነት እና ሥርዓት እንጂ የተዘበራረቀ ነገር አይኖረንም።የተቀበልነው ሥር ዓተ መላእክትን ስለሆነ፥ተጠርተን ወደ ሰማይ ስንሄድም ከቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ ሆነን፥በአንድ አይነት ሥርዓት አናመሰግናለን።በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእ ክት ይሆናሉ፤የሚለው ይኸንን ሁሉ የሚያጠቃ ልል ነው።ማቴ፡፳፪፥፴።ስለ ነገረ ኦርጋን፡-የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስ ቲያንን እንደ አብነት ለመጥቀስ የሚሞ ክሩ አሉ።አባቶቻችን እኮ ከቅዱሳን ነገሥታት ከአብርሃ ወአጽብሐ ጀምሮ፡-ለአንድ ስድስት መቶ ዓመታት ጳጳሳትን እንጂ ኦርጋንን አላስመጡም። ግብፃውያን ጳጳሳትም፡-ቅዱሳት መጻሕፍትን እና መስቀላቸውን ይዘው መጡ እንጂ ኦርጋን ተሸክመው አልመጡም።አንዳንዶች ደግሞ፡-“ጥንት ስላልነበረ ነው፥አሁን ግን ዘመኑ ኦርጋንን ስላመጣልን ከዘመኑ ጋር መዘመን አለብን፤ይላሉ እንጂ ምክንያታቸው አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም፡-እግ ዚአብሔር፡-ዘመን በሚያመጣው ኦርጋን መመስገን ፈቃዱ ቢሆን ኖሮ አን ዱን ነቢይ ትንቢት ማናገር ይችል ነበር። ቴክኖሎጂን በተመለከተ፡-ማኅበር ቅዱሳን የዛሬ ዓመት በ፲፱፻፹፰ .. ባሳተመው፡-“ቤተ ክርስቲ ያንህን እወቅ በሚለው መጽሐፍ መግቢያ ላይ፡-“የትውልድ ዕድገት አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ እስካ ልሆነ ድረስ ትውፊት(Tradition) ከቴክኖሎጂ ጋር አይጋጭም። ቴክኖሎጂ ባስገኘው ቴፕ ቅዳሴያችንን በድ ምፅ ቀርፀን ለተተኪው ትውልድ እናስቀምጥበታ ለን እንጂ፡-“የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፥የሰው ኃይልና ጊዜ ይቆ ጥባል፤ብለን በካህናቱ ምትክ የቅዳሴ ካሴት ቴፕ ውስጥ አስገብተን በሰንበት ጠዋት አናስቀድስም።ትክኖሎ ጂን ተጠቅመን በቀላሉ ጧፍ ለመሥራትና ለአብያተ ክርስቲያናትም በቶሎ ለማዳረስ የሚያስችለንን መንገድ እንቀይሳለን እንጂ ጧፍን በእጅ ባትሪ እንቀይርም።ይላል።
Top of Form

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

1 comment:

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤