Friday, May 27, 2016

የእንደራሴ ምደባ በፈጠረው መካረር ስብሰባው በድንገት ተቋረጠ፤ ፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ አዝነውበትና ጸልይውበትይወስኑበታል

his holiness abune Mathias
“ኃይል አለኝ፤ ነገር ግን መጠቀም አልፈልግም” በሚል በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ ዝተዋል
  • ምደባው፥ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግና አደራን የመጠበቅ ጉዳይ እንደኾነ ተገልጧል፤
  • የልዩ ጽ/ቤትና የአ/አበባ ሀ/ስብከት አጀንዳዎች እንዲሰረዙ በያዙት ተቃውሞ ቀጥለዋል፤
  • አንሡኝ!”ላሉበት አቋማቸው፣ “ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ እናደርገዋለን!” ተብለዋል፤
  • በጎጥና በጎሳ ለማሸማቀቅ የሞከሩ የምልዓተ ጉባኤው አባላት በከፍተኛ ደረጃ ተገሥጸዋል፤
*               *               *

Tuesday, May 10, 2016

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!

 ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!

ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር። እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ። እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረላቸው ባለጸጎች ነበሩ። ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ።
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ለመኑ ዘዘገብነ ዘንተ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ - ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም” አላት። እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳን ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት። እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በሕልሜ ርኢኩ በሕልምየ ጸዓዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርስየ - ነጭ ጥጃ ከማኅጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ ፯ት
ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው።