Wednesday, December 6, 2017

የዋልድባ አባቶች በቅሊንጦ ስቃይ በVOA እና በESAT ተዘገበ

ESAT Radio on November 29, 2017

VOA News on December 1, 2017

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, November 26, 2017

የዋልድባ አባቶች የችሎት ውሎ ከቅሊንጦ መልስ

 •   በችሎት እለት ከፍተኛ መታወክ በፍርድ ቤት ተከስቷል
 •     በኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ታሪክ እንዲህ አይነት ረብሻ አይተን አናውቅም ብለዋል የዓይን ምስክሮች
 •     አባ ገብረ ኢየሱስ እና አባ ገብረ ሥላሴ ዘዋልድባ ወደ ዞን ፭ (የጨለማ ማሰቃያ) ተዛውረዋል
 •     አባቶች አሰቃዮቻቸውን (ደብዳቢዎቻቸውን) ኦፊሰር ካሱን ዘራችሁ አይባረክ ጥቁር ውሻ ውለዱ በማለት     ተራግመዋል ገዝተዋል
 •  ስቃያቸው እስከ መቼ ይቀጥል ይሆን 

 • አባ ገብረ ኢየሱስ


የጠዋቱ ቀዝቀዝ ያለ አየር ይነፍስ ነበር እለቱ ሐሙስ ኅዳር ፲፬ ቀን በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፪ኛ ምድብ ችሎት እንደተለመደው የተለያዩ ክስ የተመሠረተባቸው የክስ ሂደታቸው የሚታይበት ቦታ ነው፥ በዚህ ቀን ግን ከእለቱ ለየት ባለ ሁኔታ ከቅሊንጦ  በመጡ ታራሚዎች የክስ ሂደታቸው የሚታይበት ቀን በመሆኑ ሊሆን ይችላል ወይም ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መነኮሳት የክስ ሂደታቸው የሚታይበት ቀን በመሆኑ ሊሆን ይችላል፥ ከሌሎች ቀናት ለየት ባለ ሁኔታ ችሎት ከአፍ እስከ ገደፉ የክሱን ሂደት የሚከታተሉ ተከታታዮች፣ የተከሳሾች ዘመድ አዝማድ እንዲሁም የፍርድ ቤቱ የህግ ሂደቱን የሚቆጣጠሩ የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች የሚገኝበት ፪ኛ ምድብ ችሎት የፍርድ ሂደት ሊከታተሉ የተመደቡ ሦስት የፍርድ ቤቱ ዳኞች ቦታቸውን ይዘዋል። የመሃል ዳኛው “ጸጥታ ይከበር” በማለት የችሎቱን የፍርድ ሂደት ለመጀመር ደጋግመው  በያዙትን የዳኞች መዶሻ መሰል በጠረጴዛው ላይ ያንኳኳሉ፣ የመጀመሪያዎችን ታራሚዎችን የጸጥታ ሃይሎች ወደ ችሎት እንዲያስገቡም ሊሆን ይችላል ሂደቱ በእንዲህ ያለ ቀጥሎ።

Monday, October 30, 2017

የቤተክርስቲያን አባቶች በፍርድ ማጣት ሲሰቃዩ፥ ቅዱስ ሲኖዶስ ለምን ዝም አለ?

የቤተክርስቲያን አባቶች በፍርድ ማጣት ሲሰቃዩ፥ ቅዱስ ሲኖዶስ ለምን ዝም አለ?
     የጥቅምት ፲፬ የፍርድ ቤት ይህን ይመስል ነበር

§      የዋልድባ አባቶች በፍርድ እጦት እየተሰቃዩ ነው
§      የመነኮሳቱ ጉዳይ እንግዳ በሆኑ ሁኔታዎች የተሞላ ሆኗል
§      የጥቅምት ፲፬ የፍርድ ቤት ውሎ እንዴት ነበር
§      የመነኮሳቱን መጎሳቆል ሃላፊነት ማነው የሚወስደው
ዋልድባ ገዳም ላይ መንግሥት በዕቅድ ላይ የነበሩትን ሰባት ትላልቅ የስኳር ፋብሪካዎች ለማቋቋም በሚል ሰበብ በዋልድባ ገዳም ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት፣ በመነኮሳት ላይ እንግልት እንዲሁም ግድያ ሲፈጽም የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት በአካባቢው ባሉ ባለሟሎቹ ለበርካታ መነኮሳት መደብደብ፣ መሰቃየት፣ ብሎም ለህልፈት መብቃት ብቸኛ ተጠያቂው መንግሥት እና በአባቢው ያሉ ተላላኪዎች እንደ እነ አማናይ እና ሲሳይ መሬሳ የመሳሰሉት ብዙ ግፍ እና እንግልት በመነኮሳቱ ላይ ሲፈጽሙ እንዲሁም ግብረ በላ በመላክ ግፍ ሲያስፈጽሞ፥ ዛሬ ድረስ ለበርካታ መነኮሳይት መደፈር፣ መደብደብ እና እንግልት የደረጉ እነዚህ ሰዎች ከታሪክ ተጠያቂነት አያመልጡም የሚል እምነት አለን። ያኔ ነበር እንግልቱ በመነኮሳት ላይ ሲጨምር፣ የአበው አጽም ሲፈልስ፣ እንዲሁም የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አማናዊ ሥጋው እና ደሙ የሚፈተትባቸው ቤተክርስቲያናት ለመፍረስ ሲታቀዱ በዋልድባ ሦስቱም ማኅበራት ማለትም

Wednesday, October 25, 2017

! ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ: የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪውን በጋሻው ደሳለኝን አውግዞ ለየ !

 • በደሉ፥ በበርካታ የምስል፣ የድምፅና የሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል
 • በደርዘን ለሚቆጠሩ ዓመታት በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲላገድ ቆይቷል
 • ከሐዋሳ የመጡ ልኡካን፣ በደሉንና ድፍረቱን በማስረጃ አብራርተዋል
 • የይቅርታ ዕድሎች በቂ በመኾናቸው፣ ጠርቶ መጠየቁ አላስፈለገም
 • ውግዘቱ የተላለፈው ልዩነት በሌለበት የምልአተ ጉባኤ ድምፅ ነው፤
†††

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ የሰጠችውን የንስሐና የይቅርታ ዕድል ተጠቅሞ ከመታረም ይልቅ፣ ለማንነቷና ማዕከላዊ አንድነቷ ስጋት የኾነውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ማስተጋባት የመረጠውና በቅርቡም ክብሯን እያንኳሰሰ ለመገዳደር የዛተው በጋሻው ደሳለኝ፤ የማይታረም የጥፋት መሣሪያ እንደኾነ ያረጋገጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አውግዞ ለየው፡፡
ውግዘቱ የተላለፈው፣ የበጋሻው በደሎች በስፋትና በተደጋጋሚ በተፈጸሙበት የሲዳማ፣ ጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቀደም ሲል ለቋሚ ሲኖዶስ በደብዳቤ ባስታወቁት መሠረት፣ በምልአተ ጉባኤ ተ.ቁ(10) የተያዘው አጀንዳ፣ በዛሬው፣ ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ የቀትር በኋላ ውሎ በታየበት ወቅት ነው፡፡
ከ1997 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ፣ ላለፉት ከደርዘን በላይ ዓመታት በጋሻው በንግግርም በድርጊትም በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸማቸውን በደሎች የሚያስረዱ በርካታ የድምፅ፣ የምስልና የሰነድ ማስረጃዎች እየቀረቡ ተነጻጻሪ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ከሐዋሳ የመጡ ዐሥር ያህል ልኡካን በአስረጅነት ያቀረቡና ያብራሩ ሲኾን፤ ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ሥርዓተ እምነትን፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትንና ታሪክ በንግግርም በድርጊትም በመናቅና በማቃለል የፈጸማቸውን በደሎች የሚያስረዱ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን፣ በዘመናት ብሔራዊ አስተዋፅኦዋ የገነባችውን መልካም ስም በዐደባባይ እያንኳሰሰ “ትከሻ ለመለካካት” የዛተባቸውና የተገዳደረባቸውም ናቸው፡፡
ከተጠቀሱት ውስጥ፡- “ጋለሞታዪቱ ቤተ ክርስቲያን”፣ “ክርስቶስን ሰብካ የማታውቅ ቤተ ክርስቲያን”፣ “ከፖሊቲካ ጋራ የተጋባች ቤተ ክርስቲያን”፣ “ውሸት ሰብስባ ውሸት ስታስተምር የኖረች ቤተ ክርስቲያን”፣ “ምእመናኗን በትና ገንዘብ የምትሰበስብ ቤተ ክርስቲያን”፣… ወዘተ የሚሉት እንደሚገኙበትና እነኚህን የመሳሰሉ ሌሎችም በርካታ ነገሮች ከነማብራሪያቸው መቅረባቸው ተገልጿል፡፡

ቅ/ሲኖዶስ: በእነዶ/ር ንጉሡ ለገሰ ለሚመራው የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዓለም አቀፍ የዕርቀ ሰላም ኮሚቴ ጥረት ይኹንታ ሰጠ

 • በውጭ ካሉ አባቶች ጋራ ለተጀመረው ዕርቀ ሰላም ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ተቋቋመ
 • ምሥረታውን አስተዋውቋል፤ ዓላማውንና ዕቅዱን ለምልአተ ጉባኤው አብራርቷል
 • ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ተነጋጋሪ ልኡካን መመደብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል
 • በጥቅምት መጨረሻ በኮለምበስ ኦሃዮ ከሚደረገው የውጩ ሲኖዶስ ጋራ ይወያያል
 • ልዩነቱ ወደ ቀኖናዊነት ሳይከፋ፣ ጥረቱን በቅንነት እንደግፍ፤ ዕድሉን እንጠቀም
†††
በውጭ ከሚገኙ አባቶች ጋራ ተጀምሮ የተስተጓጎለውን የዕርቀ ሰላም ሒደት በተሻለ አያያዝ ለማስቀጠል ዓለም አቀፍ አስታራቂ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲኾን፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዓላማውንና ዕቅዱን አቅርቦ ይኹንታ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡
በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ አገልጋዮችና ታዋቂ ምእመናን በበጎ ፈቃድ የተሰባሰቡበት ዓለም አቀፍ አስታራቂ ኮሚቴው፣ ዐሥር አባላትን የያዘ ሲኾን፤ ወደ ኢትዮጵያ በመጡት ሦስት ልኡካኑ አማካይነት ዓላማውንና ዕቅዱን ለምልአተ ጉባኤው በማስረዳት ለወጠነው የዕርቀ ሰላም ጥረት ይኹንታ እንዳገኘ ተገልጿል፡፡

Monday, October 23, 2017

ፓትርያርኩ: በመክፈቻ ቃለ ምዕዳናቸው የተነሣሒነት ጥሪ ቢያቀርቡም፣ በግትርነትና ቡድንተኝነት አፈረሱት፤ ትውልዱን በጅምላ ነቀፉ

 • የምልአተ ጉባኤውን የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አሠያየም፣ በግትርነትና ቡድንተኝነት አወኩ
 • “ስለማኅበረ ቅዱሳን አታንሡብኝ፤ በአባ ማርቆስ ጉዳይ የሚቀርብ አጀንዳ አልቀበልም፤” አሉ
 • ብፁዕ አባ ማርቆስን በኮሚቴነት ለማስመረጥ ሲሟገቱ የተመረጡት አባቶች ራሳቸውን አገለሉ
 • ከምሥራቅ ጎጃም እንዲነሡ የተጠየቀውን በመቃወም የመጡ ደጋፊዎችን ተቀብለው አነጋገሩ
 • ኮሚቴው ሊሠየም ባለመቻሉ፣ ቋሚ ሲኖዶሱ ባቀረባቸው 16 አጀንዳዎች ውይይቱ ይቀጥላል፤
†††
 • በበጋሻው ደሳለኝ፣በ“ወልደ አብ መጽሐፍ” እና በአባ መዓዛ በየነ ላይ የቀረቡ ጉዳዮች ተካተዋል፤
 • የጅቡቲ ሀገረ ስብከት፣ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥር እንዲተዳደር ጥያቄ መቅረቡ ተገልጿል፤
 • ከግንቦት በኋላ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ያልተመለሱት ብፁዕ አቡነ ሙሴ ጉዳይም ይታያል፤
 • ወደ ሀገር እንዲመለሱ የመጨረሻ ጥሪ የተላለፈላቸው ብፁዕ አባ ኤዎስጣቴዎስም አሉበት፤
 • በሶማሌና በኦሮሚያ ድንበር በተፈጠረው ግጭት ስለሞቱና ስለተፈናቀሉ ዜጎችም ይወያያል፤
†††
 • የ36ኛውን አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ የጋራ መግለጫ እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል፤
 • የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ስለ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ይመለከታል፤
 • በገዳማት መተዳደርያ ደንብ ረቂቅ በግንቦት የሰጠውን ማሻሻያ ተመልክቶ ደንቡን ያጸድቃል፤
 • በውጭ በስደት ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋራ ተጀምሮ ስለተቋረጠው ዕርቀ ሰላም ይነጋገራል፤
 • ለ2010 ዓ.ም. የቀረበውን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጀት ረቂቅ ያጸድቃል፤
†††

ቅ/ሲኖዶስ በአንድነት በመሥራት ለምእመናን አቤቱታ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ፤ “የተሐድሶ ኑፋቄ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ሊመክት ይገባል፤” /ብፁዕ አቡነ እንጦንስ/

በ7 አውቶብሶች ተጓጉዘው የደረሱ የምሥራቅ ጎጃም ግፉዓን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በምልአተ ጉባኤው የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር ላይ የአቤቱታ ድምፃቸውን ሲያሰሙ፤
 • የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ጸሎት ተካሔደ፤
 • የተሐድሶ ኑፋቄ፣ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ካልተመከተ፤ ከዮዲት ጉዲት ጥፋትና ከግራኝ ወረራ ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና እንደሚያናጋ ብፁዕነታቸው አሳሰቡ
 • የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን፣ በሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደሎች ያስቸገሩት ብፁዕ አባ ማርቆስ እንዲነሡ፥ ግፉዓን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ጠየቁ፤
 • ችግሮቹ መፍትሔ ሳይበጅላቸው ከቀጠሉ፣ ለሀገረ ስብከቱና ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች እንደሚያስከትሉ አሳስበዋል፤
 • “ምክር ዝክር የሌላቸው ግራ አጋቢ” ያሏቸውን ብፁዕ አባ ቶማስን አስጠነቀቁ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስን እየደገፉ በሚከተሉት፣ ወጣቱን ትውልድ ከቤተ ክርስቲያን የሚያርቅ አካሔዳቸው ወቀሷቸው፤
 • ከደብረ ማርቆስ፣ ብቸና እና ደጀን የተውጣጡትና በ7 አውቶቡሶች ተጓጉዘው የደረሱት ከ500 በላይ ካህናትና ምእመናን፣ የአቤቱታ ድምፃቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰምተዋል፤
 • የምልአተ ጉባኤው መክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በተደረገበት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ አቤቱታቸውን ያሰሙ በርካታ ምእመናን፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እና ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መከበር ጥብዓት ላሳዩት፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል፤

ፓትርያርኩ የጠሩት የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ሳይካሔድ ቀረ

 • በቦታው የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ብቻ ናቸው
 • ብዙዎቹ ዕለቱኑ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ እያሉም ያልተገኙ አሉ
 • እንዳይገኙ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጥብቅ አዘዋል፤እስከ አየር ማረፊያ የሸኙም አሉ
 • “ፓትርያርኩ ከቤተ ክህነቱ መዋቅር ላጡት ተቀባይነት ማሳያ ነው፤” 
†††
ትላንት በተጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ፍጻሜ ማግሥት፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል በድብቅ ጠርተውታል የተባለው የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ሳይካሔድ መቅረቱ ተገለጸ፡፡
ስብሰባው፣ ለዛሬ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ ጠዋት 3፡00 ላይ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተጠርቶ የነበረ ቢኾንም፣ ከአንድ ሀገረ ስብከት በቀር ብዙዎቹ ሥራ አስኪያጆች ወደ የአህጉረ ስብከታቸው በመመለሳቸው፣ አንዳንዶቹም በከተማው እያሉ ባለመገኘታቸው ሳይካሔድ እንቀደረ ተገልጿል፡፡
የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች በበኩላቸው፣ አጠቃላይ ጉባኤው የተጠናቀቀበትን መንፈስ ይዞ ስብሰባውን ማካሔዱ ፋይዳ እንደሌለው በመታመኑ፣ ትላንት ማምሻውን በተካሔደ ምክር እንዲሰረዝ መወሰኑን ነው የተናገሩት፡፡
በሥፍራው ተገኝተዋል የተባሉት፣ በብፁዕ አባ ማርቆስ የሚመራው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ዕንባቆም ጫኔ ሲኾኑ፤ ስለሚናገሩበት ጉዳይ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ መክረው በስፋት ተዘጋጅተውበት እንደነበር ተነግሯል፡፡
ከእርሳቸው በቀር ሌሎች ተሰብሳቢዎች ባልተገኙበት ጧት፣ በመንበረ ፕትርክናው አካባቢ ለብቻቸው ሲዟዟሩ ታይተዋል፡፡ ምን እንደሚፈልጉና ምን ሊሠሩ እንደመጡ የፓትርያርኩ ረድእ መላልሰው ሲጠይቋቸውም ነበር፣ ተብሏል፡፡

Saturday, October 14, 2017

“ወልደ አብ” በተባለ የኑፋቄ መጽሐፍ ጉዳይ: ለብፁዕ አባ ማርቆስ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፤“ሊያስወግዝዎና ከአባልነት ሊያሰርዝዎ ይችላል”/ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

 • ወልደ አብ” የክሕደት መጽሐፍ እንዲታገድና ምላሽ እንዲሰጥበት፣ አሳታሚዎቹም በሕግ እንዲጠየቁ የሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምእመናን ቀደም ሲል ያቀረቡትን አቤቱታ በዚህ ፒዲኤፍ ፋይል ይመልከቱ፡፡
†††
 • በምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ገዳማት፣ በድብቅና በስፋት እየተሠራጨ ነው
 • የሊቃውንት ጉባኤ ክሕደቱን መርምሮ እንዲያቀርብ በቋሚ ሲኖዶሱ ታዟል
 • ሊቀ ጳጳሱ፥በማውገዝ ፈንታ በዝምታ መደገፋቸው፣ ምእመናንን አስቆጥቷል
 • በንቀትና ትችት በፈጸሙት የቀኖናና የሕግ ጥሰትም፣አቤቱታው ተጠናክሯል
†††
 • በደላቸውን የሚያጣራ ልኡክ ቢመደብም፣ በፓትርያርኩ እንዲዘገይ ተደርጓል
 • ፓትርያርኩ ይኹንታ በሰጡት፣ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን አድማቸው ቀጥለውበታል
 • ማኅበሩ፣ ከፍተኛ ድጋፍ የሰጠበትን ኹለገብ ሕንፃ፣በፓትርያርኩ ያስመርቃሉi
 • ለ5 ጊዜ አቤቱታ ቢያቀርብም፣ያልተደመጠው ምእመን፣እንዲያናግሩት ይሻል!
†††
ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የ“ወልደ አብ” መጽሐፍን ክሕደት ገልጸው ምእመናን እንይቀበሉት ቃለ ውግዘት ያስተላለፉበት ደብዳቤ

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ: በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተላለፈውን የፓትርያርኩን ኢ-ሲኖዶሳዊ እገዳ ውድቅ አደረጉ፤ስለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት አሳሰቧቸው


ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፓትርያርኩን ያሳሰቡበት የደብዳቤ ክፍል፤
ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና መከበር የቆሙት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፡-
 • የፓትርያርኩ የእግድ መመሪያ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያልወሰነበት ኢ- ሕጋዊ መኾኑን ገለጹ
 • በ36ው አጠቃላይ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርታቸው፣ የማኅበሩንም ማካተቱን አስታወቁ
 • የ“ዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔትም፣ የአህጉረ ስብከቱን የማኅበር ዘገባ ጭምር ይዞ ተዘጋጅቷል
 • ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት፣ ፓትርያርኩ ለቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲገዙ መከሩ
 • ብፁዓን አባቶች፣ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሓርበኝነት ድጋፋቸውን እየገለጹላቸው ነው
†††

Thursday, April 20, 2017

በዋልድባ ገዳም ላይ ህወሓት ያደረገው ምስጢራዊ ስብሰባ እና ገዳሙን ለማፍረስ ያደረጋቸው እኩይ ተግባራት


አቶ ገብረመድህን አርአያ


ከአቶ ገብረመድህን አርአያ
የህወሓት መስራች፣ የፖሊት ቢሮ አባል እና የፋይናንስ ኃላፊ የነበሩ
አሁን በስደት በአውስትራሊያ ነዋሪ

የዋልድባ ገዳም በህዋሓት መሪዎች በዓይነ ቁራኛ የወደቀው ገና ትገሉ እንደተጀመረ ነው። የዋልድባ ገዳም የህወሓት መሪዎች እንዲወድም ሃሳብ ያቀረቡት ፲፱፸፫ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ አቅማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በውቅቱ የህወሓት መናኸሪያ ነበር። በተመቤን ውስጥ የሚገኘው ቦታ በፕሮፓጋንዳ /ቤት ተሰብስበው ወሰኑ፤ በስብሰባ የነበሩት አመራር ፖሊት ቢሮው በሙሉ ነበር። እነሱም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፈን እና መለስ ዜናዊ ነበር። በወቅቱ /ኮሚቴ የነበሩ ናቸው።  Ato Gebremedhin Araya former TPLF leadership member

Thursday, April 6, 2017

በፈረሰችው የቅ/አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ: ፓትርያርኩ፥ የአ/አበባ ከተማ ከንቲባን አሳሰቡ፤ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንም ፈረሰ

 • የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ፥ቀኖናን ጥሷል፤ ምስጢራትን ደፍሯል፤ ንዋያተ ቅድሳትን መዝብሯል
 • ደብሩ፣ በወረዳው ሥራ አስፈጻሚ እና በደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ ሓላፊዎች ላይ ክሥ መሠረተ
 • ተመሳጥሮ በማፍረሱ፥ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው የተባለው፣ ‘አባ’ ኃይለ ሚካኤል ካሳ ታገደ
 • ጸሎቱ እና ትምህርቱ አልተቋረጠም፤ ኹሉም እንደ ልቅሶ ደራሽ እንባውን አፍስሶ ይሔዳል
***
 • ሮሮው ተባብሶ አቅጣጫ ሳይለውጥ ፍትሕ ርትዕ የተሞላበት ዳኝነት ይታይ”/ፓትርያርኩ/
 • ይዞታ፣ በስጦታ ተገኘ፤ በሚል ብቻ ቤተ ክርስቲያን ሊሠራ አይችልም”/የከንቲባው /ቤት/
 • “የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱን የእግድ ትእዛዝ እያሳየናቸው ማፍረሳቸው ሕጉን መናቅ ነው”/ደብሩ/
 • ታቦቱ ባለበት በንብረቱ ላይ ተራምደው ከነጫማቸው ገቡ፤ መንበሩንም ጭነው ወሰዱ/ምእመኑ/
***
(ሰንደቅ፤ ፲፪ኛ ዓመት ቁጥር ፮፻፬፤ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)

በአዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12፣ አባዶ ቁጥር 1 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተሠራችው፣ የደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን፥ ድፍረት በተመላበት ኃይልና ሥልጣን፣ በወረዳው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እንደፈረሰች ፓትርያርኩ የጠቀሱ ሲኾን፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚያሰማው ሮሮ ተባብሶ አቅጣጫውን ከመለወጡ በፊት፦ ፍትሕ ርትዕ የተሞላበት ዳኝነት ታይቶ፣ የፈረሰው ተጠግኖ፣ የጎደለው ተሟልቶ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል አመራር ለሚመለከተው ክፍል እንዲተላለፍ ከንቲባ ድሪባ ኩማን አሳሰቡ፡፡
የደብሩ ይዞታና ግንባታ፣ ሕገ ወጥ ነው፤ በሚል ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትፈርስ በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ፣ የይግባኝ ቅሬታ ቀርቦበት እንዳይፈጸም ታግዶና በቀጠሮ ላይ እያለ፣ መጋቢት 18 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ በሚያሳዝን ኹኔታ፣ ታቦተ ሕጉ ያለበት መቃኞ ቤተ ክርስቲያን በመፍረሱ፥ ንዋያተ ቅድሳቱ ተመዝብሯል፤ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንም የድፍረት ሥራ ተፈጽሞባቸዋል፤” ብለዋል ፓትርያርኩ፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ ለከንቲባው በጻፉት ደብዳቤ፡፡
 • ክፉኛ የተጎዱት ሥራ አስኪያጁ፣ በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው
 • በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን የደበደቧቸው 2 የኑፋቄው ቅጥረኞች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል
 • በጥቃቱ እና ጉዳያቸው እየታየ በሚገኙ ከ23 በላይ የኑፋቄው ተጠርጣሪዎች ውሳኔ ይሰጣል
 • ጥቃቱ፣ የወረዳውን አድባራት፣ የፀረ ተሐድሶ ኮሚቴ ጥረትና ውጤታማነት አመላካች ነው
 • በፀረ ተሐድሶ ተጋድሎው፣ ወላጆችና ሰንበት ት/ቤቶች ወሳኝ ሱታፌና ትብብር አሳይተዋል
                                           * * *