Monday, January 23, 2017

የዋልድባ ቅን አምባ ኪዳነ ምሕረት የደናግላን ገዳም በፌደራል ወታደሮች ቤተመቅደሱ ተመዘበረ

Related image


በሰሜን ጎንደር ዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገኘው የዋልድባ ቅን አምባ ኪዳነ ምሕረት የደናግላን ገዳም ትላንት ረፋዱ ላይ በፌደራል ወታደሮች መወረሩን የአካባቢው የዓይም ምሥክሮች የደረሰውን ውዝግብ እና የመንግሥት ወታደሮች በሃይማኖታችን ላይ እያደረሱት ያሉትን መጠነ ሰፊ የሆነ ምዝበራ እና ቤተመቅደስ የማዋረድ ሥራቸውን እግዚአብሔር እንዲያስታግስልን ምዕመናን በጸሎት እንዲያግዙን ብለው መልዕክታቸውን አስተላልፈውልናል።

Thursday, January 19, 2017

እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
 እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ በማለት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልካም ምኞቻችንን እንገልጻለን  
ጥር ፲፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+
ቃና ዘገሊላ+
+'
ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ) የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው::
ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም::
+
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት
መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::
+
ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን ቻይ' እያልን የምንጠራው::

የአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ: ለስምሪት ሲዘጋጁ እጅ ከፍንጅ የተያዙ 9 የተሐድሶ ኑፋቄ ምልምሎችን አባረረ፤“ሃይማኖታቸውን የካዱ የእናት ጡት ነካሾች ናቸው!”/ኮሌጁ/

 • በኑፋቄው ዓላማና እንቅስቃሴ ሠልጥነው በፓስተሮቻቸው ‘ሲመረቁ’ በቪዲዮ ተቀርፀዋል
 • በሐቀኛ ደቀ መዛሙርትና በሰንበት ት/ቤቱ የነቃና የተቀናጀ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቷል
 • በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘው ማሕበር ሰላማ፣ የታገዱትን ለማስመለስ በድብቅ እየሠራ ነው
 • በኅቡእ በሚሠለጥኑ ሌሎች ስመ ደቀ መዛሙርት ላይም ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው
*                    *                    *
 • በደብረዘይት፣ ኅቡእ ሥልጠናዎችን የተሳተፉ የኮሌጁ ምልምሎች ተለይተው ታውቀዋል
 • በጠቅላይ ጽ/ቤት እና በየአድባራቱ የተሰገሰጉ ሰርጎ ገቦች፥ ያስተባብራሉ፤ ያሠለጥናሉም
 • ዋነኞቹ አስተባባሪዎች፦ ከኮሌጁ ተመርቀው የወጡና በድኅረ ምረቃ እየተማሩ ያሉ ናቸው
 • ከአ/አበባ መኳንንት ተገኝ፣ ከሰበታ ገበየሁ ይስማው፣ ከአዳማ አዲስ ይርጋለም ይጠቀሳሉ
*                    *                    *
 • በጠ/ጽ/ቤቱ የሊቃውንት ጉባኤ የሚሠራው አእመረ አሸብር በተደጋጋሚ በማሠልጠን ተሳትፏል
 • መኳንንት ተገኝ፥ አማሳኙ ጎይትኦም ያይኑ በአ/አበባ አድባራት በቅጥር ከሰገሰጋቸው አንዱ ነው
 • “የነገረ መለኰታውያን ማኅበር” በሚል በኮሌጆች የኑፋቄው ፈጻሚ ቡድን ለማቋቋም መክረዋል
 • ‘ማኅበረ አኃው’ በሚል ፈቃድ ያወጣው የኑፋቄ አራማጅ፣ በሤራው አብሯል፤ በፈንድ ይደግፋል
*                    *                    *kesate-birhan-college

Thursday, January 5, 2017

ታሕሳስ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ቅዱስ አማኑኤል

እንን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ በማለት፣ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ከተታዮች አድንድነት መልካም ምኞታችንን እየገለጽን፥ በዓሉም የደስታ የፍስሃ የምሕረት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።
Related image
 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ 
ታሕሳስ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
"
ቅዱስ አማኑኤል "+
+
የክርስትና ሃይማኖት እጅግ ብዙ ምሥጢራትን ያካትታል:: ታላቅ መዝገብ ነውና:: ሰዎች እናልፋለን:: ዓለምም ታረጃለች እንጂ ምሥጢረ ክርስትና አያረጅም:: እዚህ ቦታ ላይ ይጠናቀቃልም አይባልም::

+'
አማኑኤል' የሚለውን ስም መረዳት የሚቻለው በአንድ መንገድ: እርሱም ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን ጠንቅቆ በመማር ነው:: ምሥጢራት ደግሞ በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

Wednesday, January 4, 2017

መጤው የገና ዛፍ ሻጮችና ሸማቾች እየበዙ ነው – የሉላዊነት ተጽዕኖ ማሳያ? “ሃይማኖታዊውና ባህላዊው ሥርዓት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል”/ባለሞያዎች/


 • በየሱቁ የሚታዩ፡- የገና ዛፎች፣ ማስጌጫ መብራቶችና ኳሶች የከተማዋ ገጽታ ኾነዋል
 • የገና ዛፍንና ተያያዥ ቁሳቁሶችን ከውጭ ለማስመጣት እስከ 930ሺሕ ዶላር ወጥቷል
 • ወጪው በየዓመቱ እየናረ በመምጣቱ ኹኔታው እንዲቀየር ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል
 • እንደ በዓላት አከባበር ያሉ ግዙፍነት የሌላቸው ባህላዊ ቅርሶች ሲጠፉ ቀስ በቀስ ነው
*                   *                    *
 • የገና ዛፍ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ትርጉም ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ያሻል
 • ስለአከባበሩ የውይይት መድረክ በመፍጠር እንደ ገና ጨዋታ ላሉ ባህሎች ቦታ ይሰጥ
 • ትውፊታዊ አከባበሩን በማንፀባረቅ ረገድ የብዙኃን መገናኛዎች ትልቁን ድርሻ ይውሰዱ
 • ለገና ጨዋታ፣ ሩር እና ኳስ በመሥራት በአገር ውስጥ የሚዘጋጁ ምርቶች ይበረታቱ
 • የገና ዛፍ በከብቶች ግርግም ቅርፅ ቢተካስ? በጭድ የተሠራ ግርግም ለሽያጭ ቀርቧል!
*                   *                    *
 • በሉላዊነት፣ ፈጣን የመረጃ ልውውጥና የሰዎች ፍልሰት የባህል መዳቀል ይፈጠራል
 • አዎንታዊ ጎኖቹን ከአሉታዊዎቹ በመለየት፣ በበጎው ላይ ብቻ ማተኮር ተመራጭ ነው
 • የኮንዶሚኒየም ግላዊ ኑሮ የበዓላት አከባበርን በማቀዛቀዝ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ነው
 • ከ‘90ዎቹ ወዲህ የሚዲያዎቹ አካሔድ መለወጡ በበዓላት አከባበር ተጽዕኖ አድርጓል
 • ኢትዮጵያ የራሷን መገለጫዎች ይዛ እንጂ የራሷን ጥላ ሉላዊነትን መቀላቀል የለባትም!
*                   *                    *
/ሪፖርተር፤ ምሕረተ ሥላሴ መኰንን፤ ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 26 ቀን 2009 ዓ.ም./
genna-_0