
✞✞✞ በስመ
አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ
፩ አምላክ
፡፡ አሜን
፡፡ ✞✞✞
✞ እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ በማለት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
እምነት ተከታዮች አንድነት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልካም ምኞቻችንን እንገልጻለን ✞
ጥር
፲፪ ቀን
የሚከበሩ ዓመታዊ
የቅዱሳን በዓላት
+ቃና ዘገሊላ+
+'ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ) የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው::
ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም::
+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት
መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::
+ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን ቻይ' እያልን የምንጠራው::
+ቃና ዘገሊላ+
+'ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ) የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው::
ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም::
+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት
መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::
+ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን ቻይ' እያልን የምንጠራው::
እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን
እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን
ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (፩ኛ ነገሥትን ተመልከት) እንደ ነበር ይታወቃል::
እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. ፲ ፥ ፰, ፲፯ ፥ ፳, ማር. ፲፮ ፥ ፲፯, ሉቃ. ፲ ፥ ፲፯, ዮሐ. ፲፬ ፥ ፲፪)
+እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. ፫፥፮ ፣ ፭፥፩ ፣ ፭፥፲፪ ፣ ፰፥፮ ፣ ፱፥፴፫ - ፵፫ ፣ ፲፬፥፰ ፣፲፱፥፲፩)
+ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ ፪ ላይ እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው:: "ወዝንቱ
ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: (ዮሐ. ፪ ፥ ፲፩) ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም:: ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም
መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: (ማቴ. ፬ ፥ ፩) አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ::
+ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት ፳፫ ነው:: ጥር ፲፩ ተጠምቆ: የካቲት ፳፩ ቀን ከጾም ተመልሷል:: ከዚያም የካቲት ፳፫ ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር ፲፪ ቀን አድርገውታል::
+በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ
ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ::
ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና) ጠሪውን ደስ ለማሰኘት
ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ::
የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው ሲቀመጡ: ሌሎች
ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ::
ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ:- በጸጋ: አንድም
'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል:: እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ
አልቦሙ-ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው::
+ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ ቃሉንና ክቡር
ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል:- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!) ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ" አላት::
ምክንያቱም ጌታ:-
*የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: (አበረከተ ይሉታልና)
*አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው:: (እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ)
አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ:: ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት:: "አባትህንና እናትህን አክብር" (ዘጸ. ፳) ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?ልቡና ይስጠን! ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን
"ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ-የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: (ዮሐ. ፪ ፥ ፭) ጌታም በ፮ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ ተአምራት ወይን አደረጋቸው::
+እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው)
ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ: ተገለጠ::
ቅዱስ ያዕቆብ ርዕሰ አበው
+የአባቶች አለቃ የተሰኘ ቅዱስ ያዕቆብ ለ፪ቱ ታላላቅ አባቶቹ እርሱ ፫ኛቸው ነው:: እነርሱን መስሎ: እነርሱንም አህሎ በጐዳናቸው ተጉዟል:: በፈቃደ እግዚአብሔር ብኩርናን ከኤሳው ተቀብሎ ወደ ሶርያ ሲሸሽ ቤቴል (ፍኖተ ሎዛ) ላይ
ድንጋይ ተንተርሶ በተኛበት ግሩም ራዕይን አይቷል::
*ይህችውም የወርቅ መሰላል የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::
"አንቲ ውዕቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ" እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም (ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ)
*ተነስቶም "ዛቲ ይእቲ ኈኅታ ለሰማይ: ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር - ይህች የሰማይ ደጅ ናት: ቤተ እግዚአብሔርም
ይታነጽባታል" ብሎ ትንቢት ተናግሯል::
+ይህ ቅዱስ አባት ለድንግል ማርያም ቅድመ አያት ከመሆኑ ባሻገር ነቢያትን: ካህናትን: ነገሥታትንና መሣፍንትን ወልዷል:: ከ፪ቱ ሚስቶቹ (ልያና ራሔል) : ከ፪ቱ ደንገጥሮች ፲፪ ልጆችን ወልዷል::
*ከአጐቱ ከላባ ዘንድ ለ፳፩ ዓመታት አገልግሎ: ሃብት ንብረቱን ጠቅልሎ ወደ ርስቱ ከነዓን ሲመለስ ለብቻው ራቅ ብሎ
ይጸልይ ገባ:: በዚያም እግዚአብሔር ሲታገለው አደረ:: (ይኸውም የፍቅርና የምሥጢር ነው) ለጊዜው ጌታ ያዕቆብን
"ልቀቀኝ" ቢለው "ካልባረከኝ አለቅህም" አለው:: ጌታም ስሙን "እሥራኤል" ብሎ ባርኮታል::
*ቅዱስ ያዕቆብ በስተእርጅና ብዙ መከራ አግኝቶታል:: ልጁን ዮሴፍን ወንድሞቹ ሽጠው "አውሬ በላው" ብለውታልና በለቅሶ ዐይኑ ጠፋ:: በረሃብ ምክንያትም በ፻፴ ዓመቱ ከ፸፭ ያህል ቤተሰቦቹ ጋር ወደ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ለ፯ ዓመታት ኑሮ በ፻፴፯ ዓመቱ ዐርፏል:: ልጆቹም ቀብረውታል::
ኃያል
ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
+በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ (በአንጾኪያ) ያበራ:
*ድንግልናውን በንጹሕ የጠበቀ:
*ቅዱሳን መላእክት የሚያነጋግሩት:
*የአንጾኪያ ሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ:
*በጦርነት ተሸንፎ የማያውቅ:
*አሕዛብ ስሙን ሲሰሙ የሚንቀጠቀጡለት:
*ከአማልክት ወን ነው እያሉ የሚፈሩት
*እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ ወጣት ክርስቲያን ነው:: ዲዮቅልጢያኖስ በካደ ጊዜም ጌታ ከባልንጀሮቹ
ለውንድዮስና ኒቆሮስ ጋር መላእክት ወደ ሰማይ አሳርገውታል:: በዚያም መድኃኒታችን ክርስቶስን ፊት ለፊት አይቶ: በእሳት ባሕርም ተጠምቁዋል:: በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና ኒቆሮስ: እንዲሁ ከ፪.፭ ሚሊየን ሰራዊቱ ጋር ለመከራ ሰጥቷል:: እርሱንም በ፻፶፫ ችንካር ወግተው ገድለውታል::
+በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ (በአንጾኪያ) ያበራ:
*ድንግልናውን በንጹሕ የጠበቀ:
*ቅዱሳን መላእክት የሚያነጋግሩት:
*የአንጾኪያ ሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ:
*በጦርነት ተሸንፎ የማያውቅ:
*አሕዛብ ስሙን ሲሰሙ የሚንቀጠቀጡለት:
*ከአማልክት ወን ነው እያሉ የሚፈሩት
*እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ ወጣት ክርስቲያን ነው:: ዲዮቅልጢያኖስ በካደ ጊዜም ጌታ ከባልንጀሮቹ
ለውንድዮስና ኒቆሮስ ጋር መላእክት ወደ ሰማይ አሳርገውታል:: በዚያም መድኃኒታችን ክርስቶስን ፊት ለፊት አይቶ: በእሳት ባሕርም ተጠምቁዋል:: በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና ኒቆሮስ: እንዲሁ ከ፪.፭ ሚሊየን ሰራዊቱ ጋር ለመከራ ሰጥቷል:: እርሱንም በ፻፶፫ ችንካር ወግተው ገድለውታል::
✞አምላከ
ቅዱሳን ወይነ
ቃና ፍቅሩን
ያሳድርብን::
ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
✞ጥር
፲፪ ቀን
የሚከበሩ ዓመታዊ
የቅዱሳን በዓላት=
፩.ቃና ዘገሊላ
፪.ቅዱስ ያዕቆብ እሥራኤል
፫.ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
፬.ቅዱሳን ለውንድዮስ እና ኒቆሮስ
፭."፪.፭ሚሊየን" ሰማዕታት (የቅዱስ ቴዎድሮስ ማሕበር)
፩.ቃና ዘገሊላ
፪.ቅዱስ ያዕቆብ እሥራኤል
፫.ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
፬.ቅዱሳን ለውንድዮስ እና ኒቆሮስ
፭."፪.፭ሚሊየን" ሰማዕታት (የቅዱስ ቴዎድሮስ ማሕበር)
"+"
አሳዳሪውም የወይን
ጠጅ የሆነውን
ውሃ በቀመሰ
ጊዜ
አደነቀ:: ከወዴት እንደ
መጣ አላወቀም::
ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን
ያውቁ ነበር::
አሳዳሪውም ሙሽራውን
ጠርቶ:- 'ሰው ሁሉ አስቀድሞ
መልካሙን የወይን
ጠጅ ያቀርባል::
ከሰከሩም በኋላ መናኛውን:: አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል' አለው:: (ዮሐ. ፪ ፥ ፱)
ከሰከሩም በኋላ መናኛውን:: አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል' አለው:: (ዮሐ. ፪ ፥ ፱)
✞✞
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞✞
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤