Tuesday, July 10, 2018

ዋልድባን እንታደግ በ35ኛው የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት ዝግጅቶችን አቀረበየዋልድባን እንታደግ ማኅበር በ35ኛው የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የስፖርትና የባሕል ፌደሬሽን ላይ በመገኘት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ግንዛቤ እያስጨበጠ፥መረጃዎችን እይሰጠ፥ በተያያዥም ከማኅበሩ በጎ አድራጊዎች ጋር ለበጎ ሥራ ሊጠቅሙ ይሚችሉ የተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቲሸርቶችን፥ መስቀሎችን፥ ማኅተቦችን፥ የጸሎት መፅሐፍትን እንዲሁም እራሥን ዝቅ በማድረግ ጫማ በመጥረግ እግረመንገዳችንንም እራሥን ዝቅ አድርጎ ሥራዎችን የሚሠራ ትውልድ ለምፍጠር ወይም አረያነትን ለማሥተማር መሰል ሥራዎችን በምሥራት ገዳማውያኑን በሚያሰፈልጋቸው ለምርዳት ቁርጠኝነትን፥ አጋርነትን፥ አልኝተኛነትን፥ ለማሳየት እና ለመራዳት በርካታ ሥራዎችን እይሠራ እንደሚገኝ ከሥፍራው ተግልጾልናል።
ዋልድባን እንታደግ ወይም ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች እይተዘዋወረ ዝግጅቶችን ድንኳን በመከራየት ለምዕመናን ግንዛቤን በማስጨበጥ መረጃዎችን በመስጠት፥ ብሎም ከበጎ አድራጊዎች ጋር በመሆን የተለያዩ የገዳሙን እና የገዳማውያኑን ችግሮች ለምቅረፍ በሚገኙት ገንዘቦች የተልያዩ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል፥ በተለይ በቅርቡ በዋልድባ ዳልሻህ አካባቢ በደረሰ የምግብ እጥረት የተነሳ በርካታ ደካማ እናቶች በምግብ እጥረት፥ በእርዛት እና በብዙ ችግር ላይ እንደነበሩ በደረሰን መረጃ መሠረት ማኅበሩ የተለያዩ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር ለዚህ ለተፈጠረው ችግር ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠት ግድ ስለነበር ተመጣጣኝ እርዳታን በማድረግ ለገዳምውያኑ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል፤ በዚህም መሠረት ከተላከው አጠቃላይ $2000 00 ወይም ወደ 70000 00 ብር ግምት በገዳሙ ደርሶ በዚህም ከ32 ኩንታል በላይ ማሽላ፥ 2 ኩንታል ኑግ እና 1 ኩንታል ጨው ተገዝቶ ለገዳሙ ገቢ ሆኗል፤በቅርቡም የምሥጋና ደብዳቤ እንደሚደርሰን ነግረውናል።


ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዋልድባ ገዳም ይልቁንም በዋናው እና ትልቁ ገዳም ማለትም የአበረንታንት መድኅኒዓለም ገዳም እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት በገዳማውያን ላይ፥ እንግልት፥እሥራት፥ ግርፋት፥ ሌላም ሌላም ደርሶባቸዋል በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያን ተገፋች ተመዘበረች ብለው ድምፃቸውን ያሰሙትን ብዙ እንግልት ግርፋት እንዲሁም እሥራት ደርሶባቸዋል። ዛሬም ድረስ ከባዕታቸው ተገፍተው የተባረሩ ገዳማውያን በተለያዩ የሐገራችን ክፍል በሚገኙ ገዳማት ውስጥ እለት በዕለት ስብሃተ እግዚአብሔር እያደረሱ ለሃገር ለወገን ለቤተክርስቲያን እንዲሁም የለውጥ መንፈሥን በሃገራችን ያመጡ መሪዎቻችን ጭምር እየጸልዩ የሚገኙ አባቶች እንዲሁም እናቶች በእነዚህ በርካታ ገዳማት ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል፥ የማኅብራችን ዋናው ዓላማ እነዚህ በግፍ፥ በዘረኝነት ተገፍተው ከባዕታቸው የተባረሩ፥ ተደብድበው በእሥር ቤት ተወርውረው (ዛሬ ድረስ በተለያየ የእሥር ላይ የሚገኙ እንዳሉ ይታወቃል፥) እነዚህን በግፍ የተባረሩትን ገዳማውያን ወደየ ባዕታቸው በሰላም ተመልሰው ከገዳምውያን ወንድሞቻቸው ጋር እንደ ጥንቱ በጋር ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን እየለመኑ ከፈጣሪያቸው ለሕዝባችን፥ ለሃገራችን፥ እንዲሁም ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን አንድነትን፥ ፍቅርን፥ መተሳሰብን እንዲሰጥልን በየዕለቱ ፈጣሪያቸው በምሕረት እንዲጎበኘን ለእኛም የአባቶቻችን በረከት፥ የእነርሱ ረደኤት እና በረከት ለሕዝብ ክርስቲያኑ ሁሉ እንዲደርስልን በዚህም ምክንያት ማኅብራችን የገዳማውያኑን መብት ለማስጠበቅ፥ ወደ ባዕታቸው ተመልሰው ፈጣሪቸውን እያመሰገኑ በሰላም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሊኖሩ እንዲችሉ መብታቸውም እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል።
በዚህ መሠረት ዋልድባን እንታደግ ላለፉት ስምንት ዓመታት በየሣምንቱ ሐሙስ የሥልክ ጉባኤ በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመሰብሰብ መምሕራኑን በመጋበዝ ቃለ እግዚአብሔርን በማዳረስ፥በመዝሙር አገልግሎት በመስጠት፥ ታዳጊ ወጣቶችን በጉባኤው ላይ ተገኝተው በተለያየ የአገልግሎት ዘርፍ በመሠማራት በምስባክ፥ በመዝሙር፥ እንዲሁም በማስተማር የተለያዩ አገልግሎቶችን እይሰጠ ይገኛል፥ እግረመንገዳችንን በሃገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ገዳማት ላይ እይደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን፥ የሚደርሱ እንግልት እና ማዋከቦችን ለተሰብሳቢው እያሳወቅን ተሳታፊው በሚችለው አቅም ሁሉ እንዚህ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆኑ ሃገራዊ እሴቶችን የመጠብቅ፥ የመንከባከብ ሃላፊነት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት እንደሆነ በማመን ጥበቃውን እንዲያደርግ እንዲሁም የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ጥያቄዎችን በመጠየቅ እና ጉዳዩን ስለምን እስከአሁን እንደተዘነጋ እና አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥበት ጥያቄ ማቅረብ እንዲቻል አደራ ለማለት እንወዳለን።

በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት ዕለት በዕለት ስብሃተ እግዚአብሔር እያደረሱ ለሃገር ለወገን፥ ለመሪዎችም ጭምር እንዲሁም ለዓለም ሕዝብ በሙሉ በጸሎታቸው፥ በምልጃቸው እንዲራዱን እና በረከታቸው እንዲደርሰን አምላከ አበው ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን። 

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤