ባለፈው ወር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ወደ አሜሪካን በመጓዝ በውጪ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማነጋገር እና በሕዝብና በመንግሥት መካከል የተገነባውን የጥላቻ ግንብ ለማፍረስ እና መልካም ግንኙነት እንፍጠር ጥላቻን እናጥፋ፣ በምትኩ በፍቅር ተደምረን ውድ ሃገራችንን ተባብረን የቀደመ ክብሯን እናስመልስ በሚል መንፈሥ ጉብኝት ባደረጉ ጊዜ፥ ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) ጥያቄዎቻችንን እና እስከ ዛሬ ድረስ ያልተፈታውን የዋልድባን ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ብቸኛው ጊዜ እና አማራጭ ይህ እንደሆነ በመገንዘብ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ግልጽ ደብዳቤያችንን በእጅ ለመስጠት ችለናል።
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል አቅርበነዋል መልካም ምንባብ
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ በእርስዎና በሥራ ባልደረቦችዎ አማካኝነት እየተደረገ ያለውን በጎ የሆነ ሃገራዊ ለውጥ በጽኑ የምንደገፍ መሆናችንን አስቀድመን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን። በዚህም ሥራ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከልብ ተነቃቅተው እራሳቸውን ለሥራ እና ለልማት ማዘጋጀታቸውን ለመጠቆም እንወዳለን። በመቀጠልም ቀጥታ ወደ ወቅታዊውና እኛንም ሆነ ብዙዎች ኢትዮጵያውያንን በብርቱ ወደ አሳሰበን ሃገራዊ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቻችን ስናቀና ፦
ሀ/ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እርቀ ሰላም እንዲወርድ በእርስዎ መመሪያ እና ከፍተኛ ድጋፍ የተጀመረው ጉዞ በእግዚአብሄር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ አንድነትና ፍቅር በሰላም የተጠናቀቀ ቢሆንም ለወደፊቱ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ከወዲሁ እንዲቆምና ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይፈጠር ግንኙነቱ በህግ መሠረትነት እንዲገደብ እንዲደረግ ጥረት ቢደረግ፤
መ/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጥምቀትና የመስቀል ደመራ ማክበሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅ ቦታዎች ከቤተክርስቲያኗ ላይ በጉልበት እየተነጠቁ ለባለሃብቶች እና ለባለጊዜዎች የተሰጡት ይዞታዎች በሙሉ ለቤተክርስቲያኒቱ እንዲመለሱላት መንግሥትዎ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ፤
ሠ/ ቀደም ሲል መንግሥት ካሕናትን እየመለመለና የሥልጣን ማስጠበቂያ መሳሪያ እንዲሆኑ በማሠልጠን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት፥ ብሎም ክሕነት የሌላቸውን ደግሞ እየመለመለና ሥልጠና በመሥጠት ከገበያ ላይ ክቡር የሆነውን የምንኩስና ፈረጅያ (ቆብና ቀሚስ) እየገዛ በየገዳማቱና አድባራቱ በመሰግሰግ የየገዳማቱ አበመኔትና እመመኔት ያደረጋቸውን እጅግ አጸያፊ ተግባር እንዲያቆም ተያይዞም የገቡትም ማንነታቸው ስለሚታወቅ እንዲወጡ ቢደረግ፤
እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመብንን ሁሉ ከቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ እንዲያስወጣልን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአብዛኛው ጥቂት ግለሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ በታቀደ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከቤተ ክህነት እስከ ወረዳ ቤተክርስቲያን ተደራጅተው ቤተክርስቲያናችንንና አገራችንን በሙስና የሚዘርፉ ግብረ በላዎች እንዲወገዱልን፤ በአጠቃላይ መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጫነውን የብረት ቀንበር ሙሉ ለሙሉ እንዲያነሳልን።
ሐምሌ ፳፩ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ፤
በአሜሪካ ጉብኝት ወቅት የቀረበ አቤቱታ
ዋሽንግተን ዲሲበአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ በእርስዎና በሥራ ባልደረቦችዎ አማካኝነት እየተደረገ ያለውን በጎ የሆነ ሃገራዊ ለውጥ በጽኑ የምንደገፍ መሆናችንን አስቀድመን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን። በዚህም ሥራ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከልብ ተነቃቅተው እራሳቸውን ለሥራ እና ለልማት ማዘጋጀታቸውን ለመጠቆም እንወዳለን። በመቀጠልም ቀጥታ ወደ ወቅታዊውና እኛንም ሆነ ብዙዎች ኢትዮጵያውያንን በብርቱ ወደ አሳሰበን ሃገራዊ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቻችን ስናቀና ፦
ሀ/ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እርቀ ሰላም እንዲወርድ በእርስዎ መመሪያ እና ከፍተኛ ድጋፍ የተጀመረው ጉዞ በእግዚአብሄር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ አንድነትና ፍቅር በሰላም የተጠናቀቀ ቢሆንም ለወደፊቱ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ከወዲሁ እንዲቆምና ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይፈጠር ግንኙነቱ በህግ መሠረትነት እንዲገደብ እንዲደረግ ጥረት ቢደረግ፤
ለ/ በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በኩል የሚገኘው ጥንታዊው እና ታሪካዊው የማኅበረ ሥላሴ ገዳም ጉዳይ ለሱዳን ሰዎች ቦታው ተላልፎ በመሰጠቱ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ በሃገር ደረጃ ትኩረት እንዲሰጠውና ወረራውና ግድያውም በአስቸኳይ እንዲቆም እርሶዎና መንግሥትዎ ጉዳዩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ጥረት ቢደረግ፤
ሐ/ የላመና የጣመውን የሥጋ ፈቃድ ሁሉ ከመናቅ ጀምሮ እጅግ መራራ የሆነውን የቋርፍ ተክል በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለቁመተ ሥጋ እየቀመሱ ከኢትዮጵያ አልፈው ለዓለም ሁሉ የሚጸልዩ ገዳማውያን የዋልድባ አባቶች እና እናቶቻችን የሚኖሩበትን ገዳም በወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት ስም በገዳሙ ላይ የተጀመረው ጥፋት አሁንም እንደ ቀጠለ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ቢደረግ፤ እንደሚታወቀው ዋልድባ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሃገራዊ እሴቶችን ይዞ
የሚገኝ ገዳም በመሆኑ፥ እነዚህ በርካታ እጹብ ድንቅ የሆኑ ሃገራዊ ዕሴቶችን የመጠበቅ የመንከባከብ ያሃገሪቱ መንግሥት እና
ሕዝብ ሃላፊነት ቢሆንም ዛሬ ላይ ስግብግቦች እና የራሣቸውን ጥቅም ብቻ የሚያስቀድሙ ግለሰቦች እነዚህን ድንቅ እና አንጡራ
ሃገራዊ እሴቶች በአውሮፓ እና በአሜሪካ ገበያ ላይ እየተቸበቸቡ እንደሚገኙ ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ፣ ስለዚህ መንግሥት አስፈላጊ
ጥበቃ እና ክብካቤ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፤ በተጨማሪም በቅርቡ ከእሥር ቤት ከተፈቱት ከእነ አባ ገብረኢየሱስ እና አባ ገብረሥላሴ ጀምሮ ጥቃቱ በሦስቱም የዋልድባ ገዳማት በሚኖሩ ገዳማውያን ላይ እየተፈጸመ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር እስካሁን ገዳማውያውኑ ተሰደው በመከራተት ላይ
ስለሆኑ በተቻለ ፍጥነት ወደ ባዕታቸው (ገዳማቸው) እንዲመለሱልን ፤ በሌላ በኩል ለጥፋት ተልዕኮ
የተሰማሩ አበመኔት እና ዕቃ ቤት በመንግሥት ውክልና ተመልምለው ወደ ገዳማቱ
የገቡ በርካታ ሰዎች በአስቸኳይ ገዳማቱን ለቀው እንዲወጡና የገዳሙ ሥርዓት በገዳማውያኑ ብቻ እንዲፈጸም የመንግሥት ሰዎች እጆቻቸውን
እንዲያነሱ አጥብቀን እንጠይቃለን ፤መ/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጥምቀትና የመስቀል ደመራ ማክበሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅ ቦታዎች ከቤተክርስቲያኗ ላይ በጉልበት እየተነጠቁ ለባለሃብቶች እና ለባለጊዜዎች የተሰጡት ይዞታዎች በሙሉ ለቤተክርስቲያኒቱ እንዲመለሱላት መንግሥትዎ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ፤
ሠ/ ቀደም ሲል መንግሥት ካሕናትን እየመለመለና የሥልጣን ማስጠበቂያ መሳሪያ እንዲሆኑ በማሠልጠን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት፥ ብሎም ክሕነት የሌላቸውን ደግሞ እየመለመለና ሥልጠና በመሥጠት ከገበያ ላይ ክቡር የሆነውን የምንኩስና ፈረጅያ (ቆብና ቀሚስ) እየገዛ በየገዳማቱና አድባራቱ በመሰግሰግ የየገዳማቱ አበመኔትና እመመኔት ያደረጋቸውን እጅግ አጸያፊ ተግባር እንዲያቆም ተያይዞም የገቡትም ማንነታቸው ስለሚታወቅ እንዲወጡ ቢደረግ፤
እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመብንን ሁሉ ከቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ እንዲያስወጣልን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአብዛኛው ጥቂት ግለሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ በታቀደ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከቤተ ክህነት እስከ ወረዳ ቤተክርስቲያን ተደራጅተው ቤተክርስቲያናችንንና አገራችንን በሙስና የሚዘርፉ ግብረ በላዎች እንዲወገዱልን፤ በአጠቃላይ መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጫነውን የብረት ቀንበር ሙሉ ለሙሉ እንዲያነሳልን።
ረ/እግዚአብሔር በጥፋት ውሃ ዘመን ለሃገራችን ለኢትዮጵያ የሰጠንን ባንዲራችን ላይ
የሰይጣን ዓርማ የሆነውን የ ፮፮፮ (666) ዓርማና ኮከብ በባንዲራችን ላይ መደረጉ አልፎ ተርፎም በሕንጻ ቤተክርስቲያን ላይ መደረጉ በእጅጉ ሃገራችንን፣ህሊናችንን እና ሃይማኖታችንን እየጎዳው በመሆኑ ይህ የሰይጣን ዓርማ የሆነ ኮከብ ከብሄራዊ ባንዲራችን ላይ እንዲነሳ፤
ሰ/ ኢትዮጵያ ሃገራችን የተቀደሰችና ለብዙ ሺ ዓመታትም መንፈሳዊና ሌሎች ዕሴቶቿን ጠብቃ የኖረች አገር ሆና ሳለ ባለፉት የቅርብ ዓመታት ግን ግብረ_ሰዶማዊነት ወይም የተመሳሳይ ጾታ የወሲብ ግንኙነት በሃገራችን ላይ እንደ ወረርሽኝ እየተፈጸመብን መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር መሆን ከጀመረ ቆይቷል። ይህም ሕጻናት ወንዶችና ሴቶችን በተለይም ምስኪን የጎዳና ተዳዳሪ ወግኖቻችን ላይ በስፋት እየተፈጸመ የሚገኝ አስከፊና አጸያፊ ሰቆቃ ሲሆን ድህነታችንን እንደመሣሪያ በመጠቀም ይህንን እርኩሰት በሃገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድንቀበል ከሚደረግብን ተጽዕኖ ጀምሮ ሕጻናትን በመደለልና በማባበል እየሸጡ የደላላና የአመንዝራ ባለሃብቶች የወሲብ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ይገኛል። ስለዚህ ይህ አስከፊና አጸያፊ ወረርሽኝ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያስቆምና ለችግሩ ሰለባዎችም የአካልና የሥነ-ልቦና ትምህርት የሚሰጥ መንግስታዊ አካል በአስቸኳይ ተቋቁሞ ወገኖቻቸንንና ሃገራችንን እንድንታደግ የመንግስት ድጋፍ እንዲደረግ ፥ ይህንን አጸያፊ
ሥራ ለማሠራት ሕፃናት ላይ የሥነ-ልቡና ችግር የሚያደርሱትንም ግለሰቦች መንግሥትዎ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ቢደረግ፤
ሸ/ በእሥራኤል ውስጥ የሚገኙት እና ጥንታውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ያቆዩልን እንደ ዴር ሡልጣንና ሌሎችም ቅዱሳን ማካናት፥ ገዳማትና አድባራት በግብጻውያን ወረራ እየተፈጸመባቸው ከመገኘቱም ባሻገር ገዳማቱንም እንዳናሳድስና የኤሌክትሪክ መብራትና የመጸዳጃ አገልግሎት በራሳችን ይዞታ ላይ እንዳንጠቀም ለዘመናት ስለተከለከልን ይህም ታውቆ የኢትዮጵያ መንግሥት ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመነጋገር በእሥራኤል የሚገኙ ገዳማትና አድባርት ይዞታዎቻችንና መብቶቻቸውን እንዲያስከብር በመንግሥትዎ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሠራበት፤
እሥራኤል መንግሥት ለሬዲዮ ጣቢያነት የሚገለገልበትን ሕንጻችንን ግብጾች እንደለመዱት ሊቀሙን በእሥራኤል ፍርድ ቤት ቢሞግቱም በቅርቡ ፍርድ ቤቱ በቀረበለት ማስረጃ መሠረት የሕንጻውን ባለቤትነት ኢትዮጵያን እንደሆኑ ማረጋገጡ የሚያስደስት ሆኖ ሳለ፤ ከአገር ቤት ጀምሮ እስከ ውጪ አገር ድረስ እጁን የዘረጋው የሙስናና የዘረፋ ቡድን ገቢውን እየተቀራመተው ስለሚገኝም አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፧

በመጨረሻም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ቤተክርስቲያናችንን እና ሃገራችንን የሚመለከቱ ወሳኝ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ መላው ሕዝበ ክርስቲያንና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ እንድንታገል፤ ብሎም የመፍትሔው
አካል ሆነን በጋራ የጋራ የሆነችውን ውድና ቅድስት ሃገራችንን በሚቻለው እየተረዳዳን ኢትዮጵያ ሃገራችን የቀደመ ክብሯ
እስኪመለስ ድረስ መንግስትዎ ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆነ የጀመረውን የእርቅ እና የአንድነት መንፈሥ በመያዝ፥ እንደ ዜጋም አገራችን ከኛ የምትጠብቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ሆነን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ ከጀመሩት ሃገራዊ ዓላማ ጋር እኛም እንደተደመርን በታላቅ ትህትና ልናረጋግጥልዎ እንወዳለን፤ ከላይ ላቀረብናቸውም ጥያቄዎችና ጥቆማዎች አስቸኳይ እና ተገቢውን ምላሽ ውሳኔ ከእርስዎ እና ከመንግሥትዎ እንዲሰጠን ከአክብሮት ጭምር እንጠይቃለን።
የእግዚአብሔር አምላክ ሃገራችንን ኢትዮጵያን በረደኤት ይጠብቅልን አሜን
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት።
ሙሉውን ደብዳቤ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤