Friday, October 25, 2019

ከመንግሥት ጋራ የሚደረገው ውይይት ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና የሚያረጋግጥ ሊኾን ይገባል፤ “ለቋሚ ስጋታችን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ውል ላይ መደረስ አለበት”


EOTC and PM Office
 • መግለጫውን ከውይይቱ በኋላ ለመስጠት ታስቦአል፤ ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶች ይመደባሉ
***
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከሚመራው የመንግሥት ልኡክ ጋራ የሚያደርገው ውይይት፣ የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ቋሚ የጥቃት እና የተጽዕኖ ዒላማ እየኾነች ለምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት የሚደረስበት ሊኾን እንደሚገባው ተጠቆመ፡፡

Thursday, October 24, 2019

በድንገት የተቋረጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ረፋድ መግለጫ ይሰጣል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በ6 የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ተመድበው ይሰማራሉ

73108746_732445340607253_5028854134598533120_n
 • የምልአተ ጉባኤው መግለጫ እና ለባለሥልጣናቱ የሚላኩት ደብዳቤዎች ቢዘጋጁም፣ በትክክለኛ መረጃዎች ተደግፈው እስኪጠናከሩ ድረስ ለነገ ማደሩ አስፈልጓል፤
 • የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ከትላንት ጀምሮ በ6ቱ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት የተገደሉና የተጎዱ ምእመናንን፣ በጥቃት ከበባ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያንን ሪፖርቶች እና መረጃዎች እያሰባሰቡ ነው፤
 • የባሌ፣ የአርሲ፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ሸዋ፣ የሻሸመኔ እና የድሬዳዋ አህጉረ ስብከት ሓላፊዎች፣ ዝርዝር የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችን ለየክፍላቱ ሊቃነ ጳጳሳቱ እየላኩ ናቸው
 • በባሌ ሮቤ ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ብቻ፣ ስድስት ምእመናን መገደላቸውን ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል፤ አባት እና ልጅ በአሠቃቂ ኸኔታ ተገድለዋል፤ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ቦምብ ተወርውሯል፤

ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ ዐወጀ

 • አገሪቱን ለከፍተኛ ጥፋት እና ድህነት የሚዳርግ እጅግ አሳሳቢ ግጭት እየተስፋፋ ነው፤
 • የጸጥታ ኀይሎች ቅድመ ግጭትን መሠረት ላደረገ መከላከል ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ፤
 • ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭት መንሥኤ ናቸው፤ ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል
 • ሶሻል ሚዲያውን ለሰላም፣ አንድነትና ተግባቦት በመጠቀም ኹሉም የበኩሉን ይወጣ፤
***
በአገራችን እንኳንስ ሊደረጉ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሣንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ ክልሎች እየተስፋፉ መኾኑ በእጅጉ ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ እንዲደረግ ዐዋጀ፤ ከመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች አንሥቶ ኹሉም አካላት እና ዜጎች በየድርሻቸው ለአገራዊ ሰላም፣ አንድነት እና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሰላም ጥሪ አስተላለፈ፡፡
ወቀተወ መገለጨ
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፡ የምልአተ ጉባኤውን የጸሎተ ምሕላ ዐዋጅ እና አስቸኳይ የሰላም ጥሪ መግለጫ በንባብ ሲያሰሙ

Thursday, October 17, 2019

ጾመ ጽጌ የእመቤታችን ስደቷን ልጇን እና ወዳጇን ይዛ የተቀበለችው መከራ የምናስብበት

Image result for የቅድስት ድንግል ማርያም ስደትጽጌ ጾም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያሉ አርባ ቀናት ዘመነ ጽጌ (ወርሃ ጽጌ) እንደሚባሉ ይታወቃል። የቤተክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገስት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል ። “ጾምስ በታወቀው ዕለት ፣በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው። ይህም ኃጢአቱን ለማስተስረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ህግን ለሰራለት  እየታዘዘ፤ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ፤ ሥጋም ለነባቢት ነፍሥ ትታዘዝ ዘንድ ነው” /ፍት.ነገ.ፍት.መን.አንቀጽ 15፥564/። 

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው። ለፈቃደ ሥጋም  መንፈሳዊ ልጓም ነው። ሰው ፈቃደ  ሥጋን እየገታ ነፍሱን  የሚያለመልምበት ስንቅ ነው። “ጾም ቁስለ ነፍስን የምፈውስ ፣ ኃይለ  ፍተዎትንም የምታደክም ፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፣ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣የጽሙዳን ክብራቸው ፣የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው ፣የጸሎት ምክንያት/እናት/ የእንባ መገኛ ምንጭ፣አርምሞን የምታስተምር፣ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።/ማር ይስሐቅ አንቀጽ 4 ምዕራፍ 6/

Wednesday, October 9, 2019

እነቀሲስ በላይ መኰንን “የምንጠይቀው ይቅርታ የለም” አሉ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የክሕደት ድርጊታቸውን በጽኑ አወገዘ፤ በሕግ እንዲጠየቁ ወሰነ!

69677888_1657044637765158_1035298022705070080_n
ከኦሮሞ ሕዝብ አብራክ ተገኝተው፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ ሳይኾን፤ ለሀገር አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ነፃነት ሰማዕት  የኾኑትን፤ ዛሬም ለክልሉ ሰላም እና አንድነት ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አባቶችን፣ የቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችንና መዋቅሮችን አገልግሎት ፈጽሞ የካደ አድራጎት በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ እያወገዘ፣ እየተሳተፉ ያሉት ግለሰቦች እና ቡድኖች ከዚህ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
~~~
 • ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና እና ፈቃድ ውጪ አዲስ መዋቅር ፈጥረው መግለጫ መስጠታቸው አግባብ አለመኾኑን አምነው ይቅርታ ለመጠየቅ፣ ከሌሎች የኮሚቴ አባላት ጋራ ተወያይተን እንመለስ፤ ብለው በጠየቁት መሠረት፣ ለዛሬ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 2፡30 ቢቀጠሩም፣ በዕለቱ የኮሚቴው ዋና ተጠሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን አልተገኙም
 • ኹለት የኮሚቴው አባላት ብቻ፣ ከተሰጣቸው ሰዓት አሳልፈው ከመምጣታቸውም በላይ፣ ኹለቱ ግለሰቦች በጽሑፍ በአቀረቡት ምላሽ፣ በሕገ ወጥ አቋማቸው እንደሚጸኑ ገልጸዋል፤
 • በመኾኑም፣ የግለሰቦቹ እንቅስቃሴም ኾነ “የኦሮሞ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት” ተብሎ የተጠቀሰው አደረጃጀት፣ ሕጋዊ ዕውቅና እንደሌለው መላው ካህናት እና ምእመናን አውቀው፣ የግለሰቦቹን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ በመቃወም እና በቀደመው አንድነታቸው ጸንተው፣ ቤተ ክርስቲያናቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲጠብ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል፤
 • ምንም ዓይነት ሕጋዊ ውክልናም ኾነ ከሕግ የመነጨ ሥልጣን ሳይኖራቸው፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ከሕግ የመነጨ ሥልጣን በመጋፋት፣ የቤተ ክርስቲያንን ዓርማ እና ማኅተም እንዲሁም መጠሪያ ስያሜ መጠቀም የማይችሉ በመኾናቸው፣ መንግሥት አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምት እንዲወስድባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡
***

Friday, October 4, 2019

በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” ጸሐፊ “መምህር አባ ገብረ እግዚአብሔር” ወደ ዋልድባ አበረንታንት መግባት ውዝግብ እያስነሳ ነው

 በላፈው ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ውዝግብ ከሚያስነሱ ጽሁፎች መካከል አንደኛው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” በተሰኘ ርዕስ በአባ ገብረ እግዚአብሔር ተጽፎ የተሰራጨው መጽሐፍ አንደኛው ነው “ የምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት መጽሐፍ ውግዘት” ሙሉውን ለማየት ይሄን ይጫኑ ፤ በመጽሐፉ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን አስተምህሮ የሚያፋልስ እና እጅግ ጽርፍ የተሞላበት መጽሐፍ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በታህሣስ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓም (12/11/2005) በብፁዕ አቡነ ማቲዎስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤው መጽሐፉም ጸሐፊውም ተወግዘው እንደተለዩ ይታወቃል፤

Sunday, September 22, 2019

Kesis Samuel in Afan Oromo

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

መስከረም ፰ ቀን ፳፻፲፪ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

We can't stay quite anymore!

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Saturday, September 21, 2019

Thursday, September 19, 2019

ሐሙስ መስከረም 8

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Saturday, September 7, 2019

እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እስከ ነገ ጠዋት 3:00 ይቅርታ እንዲጠይቁ ቅ/ሲኖዶስ ገደብ ሰጠ፤ ጥያቄአቸው በመሪ ዕቅዱ ትግበራ ማሕቀፍ እንደሚፈታ ገለጸ

ጋዜጣዊ መግለጫው ለረፋድ 4፡00 ተቀጥሯል
Holy Synod Pagumen 2011
የጥያቄአቸው መነሻ በኾኑት በኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት፥ የስብከተ ወንጌል፣ የዕቅበተ እምነት እና የአገልጋዮች እጥረት… ወዘተ. ችግሮች ላይ ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መግባባት ላይ ቢደረስም፣ ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ እንደኾነ እያወቁ፣ “የክልል ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናደራጃለን፤” ማለታቸውና የቋሚ ሲኖዶሱን ክልከላ ተላልፈው የሚዲያ መግለጫ መስጠታቸው ስሕተት እንደኾነ በብፁዓን አባቶች ተገልጾላቸዋል፤
የክልል ጠቅላይ ጽ/ቤትም ኾነ የክልል ሲኖዶስ የማቋቋም ዓላማ እንደሌላቸው የገለጹት እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በክልል ደረጃ የአህጉረ ስብከትን ጉዳይ የሚከታተልና የሚያስፈጽም፣ ከክልላዊ መንግሥታዊ አካላት ጋራ የሚያገናኝ፣ የሚያጋጥማቸውን መጓተትና እንግልት የሚያስወግድ ተጠሪ እንዲሠየም ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፤ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይኾን፣ በሌሎችም ክልሎች ለሚገኙ አህጉረ ስብከትም እንደኾነ ጠቅሰዋል፤ “በአንዲት ቤተ ክርስቲያንና በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ እናምናለን፤ አንከፋፍልም፤ አንገነጥልም፤” ያሉት በጉባኤው ፊት የቀረቡት አምስት የኮሚቴው አባላት፣ “በክልሉ እየተባባሰ የመጣው የምእመናን ፍልሰት እና የመናፍቃን ወረራ ያሳስበናል፤” ብለዋል፤

መንግሥት: ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መጠበቅ ድጋፉን ገለጸ፤ በባለሥልጣናቱ ለተፈጸሙት ግፎች ይቅርታ እንደማይጠይቅና ካሳም እንደማይከፍል አስታወቀ

pm with eotc synod members
 • ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራውና ትላንት በተጀመረው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙት ከ25 የማያንሱ የምልአተ ጉባኤ አባላት፣ ዛሬ ዓርብ፣ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ ባደረጉት ውይይት፣ የመንግሥታቸው ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሙትን ግፍ እና በደል በዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አማካይነት በንባብ አሰምተዋል(ሙሉ ይዘቱን ይመልከቱ)፤
 • የቀረበው ጽሑፍ፣ ክሥ መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “እኔ ካህናትንና ምእመናን አልገደልኹም፤ ቤተ ክርስቲያንን አላቃጠልኹም፤ አዝናለኹ፤ ሳላጠፋ፣ ሳልበድል እንዴት ይቅርታ ጠይቅ፤ ወርቅ ላበደረ ጠጠር እባላለኹ፤ ይቅርታ አልጠይቅም፤ ካሳም አልከፍልም፤” በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል፤ ጥያቄው የመተጋገዝ ከኾነ እንደሚቀበሉትና እንደሚረዱም ተናግረዋል፤
 • በውይይቱ ላይ የቤተ ክርስቲያንን ሐሳብ እንዲገልጹ በምልአተ ጉባኤው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ አቤቱታው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በግል እንደማይመለከትና በሥራቸው ማለትም በመንግሥታቸው መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን እንደኾነ ገልጸው ዶ/ር ዐቢይ ቅሬታቸውን እንዲያነሡ ጠይቀዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትንም በመዘርዘር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፤
 • የቀድሞዎቹን ርእሳነ መንግሥታት በመጥቀስ፣ “እስከ አሁን እንዲህ የጻፍችኹባቸው የሉም፤ ካሉ አያይዛችኹ አቅርቡ፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ የእርሳቸውም ኾነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ኹሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መኾኑን ገልጸዋል፤ የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መኾናቸውን አንሥተዋል፤ “ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው፤” ብለዋል።
 • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን በበኩላቸው፣ “ኦርቶዶክስ አንድነቷን ይዛ ትቀጥላለች፤ በምንም መልኩ አትከፈልም፤ አንድነቷን መፈታተን ለእኔ ድፍረት ነው፤ በዚህ ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም አለው፤” ብለዋል፤

Monday, July 22, 2019

አሰቦት ገዳምን እንደግፍ


የደብረ ወገግ አሰቦት ገዳምን መደገፍ እና በመራዳት የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን የጻድቁ አባታችን አቡነ ሳሙኤል ስም እንጠይቃለን።
https://www.gofundme.com/f/pdee2?teamInvite=scqWCn0FJaA9fdeFTHph6SMoQQlvKr4mLjFo0Qs8zRXSStsbtgUrINp4l7cvy9CM
 Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Friday, July 19, 2019

መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ጥቃት ጉዳይ እንዲወያይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ የሚሊዮን ወጣቶችና አገልጋዮች ማኅበራት ኅብረት አሳሰበ

Mahiberat Hibret Meglecha Ginbot2011
አእላፋት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችንና ምእመናንን ያቀፈው የማኅበራት ኅብረቱ አመራሮች፣ ትላንት ኀሙስ፣ ሰኔ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በዮድ አቢሲኒያ ሆቴል መግለጫውን በሰጡበት ወቅት
 • በቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፣መፈናቀልና ግድያ ጉዳይ እንወያይ ቢባል ዝምታን መርጧል
 • ዝምታውን እንቃወማለን፤ ለለውጥና ነፃነት ቆሜያለኹ ከሚል መንግሥት አይጠበቅም
 • ለቅ/ሲኖዶሱ፣የእንወያይ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥና እኛንም እንዲያነጋግረን እንጠይቃለን
 • 7ሚ.በላይ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የ240 ማኅበራት አእላፋት አባላት ጥያቄ ነው፤
***
 • ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ያበረከተችው አስተዋፅኦና የከፈለችው መሥዋዕት የማይካድ ነው፤
 • ውለታዋ ተዘንግቶ በሐሰተኛ ትርክት ተተክቶ በየቦታው እየተወነጀለችና እየተጠቃች ነው
 • በተደራጀ መንገድ ታቅዶ የሚፈጸምና በደለበ ሀብት ጭምር የተደገፈ ጥላቻና ጥቃት ነው
 • ከመንግሥት የፈረጠምን ነን ባይ ኀይሎች ኾነው ሳለ፣ ያለተጠያቂነት ዐደባባይ ይፏልላሉ፤
 • መንግሥት በሓላፊነት ስሜት ማስቆም ሲገባው፣ የሚያሳየውን ለዘብተኝነት እንቃወማለን
‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

Tuesday, July 16, 2019

Dalisha Kidane Meheret

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Dalshah Kidanemehret Waldba

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Thursday, July 4, 2019

ዋልድባን እንታደግ ለደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም በESFNA 36th በዓል በአትላንታ ጆርጂያ

የዋልድባን እንታደግ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን በሚያዘጋጀው ፴፮ኛው ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት በየዓመቱ በመገኘት ለኢትዮጵያውያን መረጃዎችን ያደርሳል፥ ለምዕመናን የተለያዩ ጽሁፎችን በበራሪ ጽሁፍ መልክ ያደርሳል በተጨማሪ የተለያዩ ሥራዎችን ማለትም ንዋየ ቅዱሳን የጸሎት መጻሕፍት፣ መስቀሎችን ኢትዮጵያዊነትን የሚገልጹ ቲሸርቶችን፣ የእጅ አንባሮችን እና የተለያዩ ሥራዎችን ይዞ በመቅረብ ለምዕመናን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያን መረጃዎችን ያዳርሳል በዚህ በተቀደሰ ተግባር ላይ በመገኘት ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውን እንዲሁም ገንዘባቸውን በመጠቀም ለገዳሙ ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት ድጋፍ እና እርዳታዎችን ለማድረግ የሚተባበሩትን ሁሉ በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን ሥራቸውን ሁሉ ይባርክ እያልን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም ብሎም በገዳማውያኑ ስም ምስጋናችን ለማቅረብ እንወዳለን።

Friday, June 14, 2019

መንግሥት አደራ በል ባለሥልጣናቱን አደብ እንዲያስገዛ፣ ሕዝቡም የአገርና የቤተ ክርስቲያን ጠላትና ወራሪ ከኾኑ ሰዶማውያንና ተባባሪዎቻቸው እንዲጠነቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ!

Holy Synod Ginbot2011 closing
 • በቱሪዝም ሽፋን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያስታወቀው፣ አሜሪካዊ የግብረ ሰዶማውያንአስጎብኚ ድርጅት እንዳይገባ አወገዘ!
 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ 7ቱን አጽዋማት የመጾም እና አልባሳትን የመልበስመብትና ነፃነት እንዲከበር አሳሰበ፤
 • ምእመናን በትክክል እንዲቆጠሩ፣ ቆጠራውም በሰላም እንዲከናወን፣ በየአህጉረ ስብከቱትምህርት እንደሚሰጥና የሚከታተል ኮሚቴም መሠየሙን አስታወቀ፤
 • እኒህ የምልአተ ጉባኤው ውሳኔዎች መልካም ቢኾኑም፣ በአህጉረ ስብከት ማጣራት ሪፖርቶችውሳኔና በመሪ ዕቅድ ትግበራ አጀንዳ አሳፋሪ ይዞታዎች የታዩበት መደበኛ ስብሰባ ነው!
***

Friday, May 17, 2019

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በአትላንታ ዋልድባን እንታደግ የፈቃደኞች መሙሊያ ቅጽ

እንድሚታወቀው በመጪው ሐምሌ ወር ላይ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌደሬሽን ሰሜን አሜሪካ በአትላንታ ለማዘጋጀት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል፤ እኛም ዋልድባን እንታደግ እንደተለመደው ለኢትዮጵያውያን የተለያዩ መረጃዎችን ለማዳረስ ድንኳን ተከራይተን በዚያው እንገኛለን፤ ለዚህም ዝግጅት የተለያዩ በጎ ፈቃደኞችን በሚኖረን የስድስት ቀናት ቆይታ ምዕመናን በጎ ፈቃዳኝነታቸውን እንደሁልጊዜው በማሳየት በቦታው ተገኝተው በበጎ ፈቃደኝነት የሰዓታት አገልግሎቶችን እንዲያበረክቱ ከወዲሁ በገዳማውያን አባቶቻችን ስም እየጠየቅን ፣ በቦታው ተገኝቶ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኞችን በሚከተለው ቅጽ በመሙላት የሚቻቸውን ቀንና ሰዓት በመሙላት እንድትተባበሩን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፤

ፎርሙን ለመሙላት የሚከተለውን ማጣቀሻ ይጫኑ

ዋልድባን እንታደግ   
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

የዋልድባ መነኮሳት አባቶቻችን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አትገቡም ተብለው መነኮሳቱ በፌደራል ፓሊስ እየተባረሩ ነው !!

ቤተክህነት ማለት የኦርቶዶክሳውያንን አቤቱታ ተቀብሎ ቢያንስ አዳምጦ ችግሮችን በመግባባት ለመፍታት መሥራት እንጂ እንዴት ደካማ መነኮሳትን በፖሊስ ሊያስባርር ይችላል ፣ ቢያንስ ችግሮችን መፍታት ባይችል እንኳን እነኚህን ትላልቅ አባቶች አገር አቋርጠው መጥተው ችግራችሁ ምንድነው ብሎ ቡራኬያቸውን ተቀብሎ ወደቦታቸው መሸኘት ሲቻል እንዲት በፖሊስ ሊያስባርር ይችላል? እጅግ አሳፋሪ ሥራ ነው በእነኚህ ትላልቅ አባቶች ላይ የደረሰው ፤ ሲሆን እንዚህ አባቶች መኩሪያዎቻችን መሆን ሲገባቸው እንዴት እንደ ምንም በፖሊስ ተገፍተው ሊባረሩ ይችላሉ ኸረ የሰው ያለህ ኸረ የፈጣሪ ያለህ ልንል ይገባናል በእውነት እነኚህ አባቶች ቀለብ ስፈሩልን ወይ ገንዘብ ተቆራጭ አድርጉልን ሊሉ እንደማይመጡ የታወቀ ነው ፤ ታዲያ የት ይሂዱ ቤተክህነቱ እንዲህ በፖሊስ ካባረራቸው የት ይድረሱ ለማንስ አቤቱታቸውን ያቅርቡ? በእውነት እኒህ አይነት ጊዜ ላይ መድረሳችን በጣም እጅግ ያሳዝናል፤ እንዴስ እንዲህ አይነት ነግሮችን የሚያገናዝብ አባቶች ጠፉ በቤተክህነቱ ውስጥ? ሰውም እግዚአብሔርም ይታዘበናል እኮ ሰው ያያል ይታዘባል እነሱ በዚህ አይነት ሁኔታ እነዚህን አባቶች ገፍተው አብረው ነገ በእነርሱ ላይ ላለመድረሱ ምን እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር አለ? በእጅጉ ያሳዝናል ያስከፋል ያማል ልቦና ይስጥልን ቤተክርስቲያን ዛሬ ድረስ በካድሬ እየተመራች እንደሆነ የሚያመለክት ነው ልብ ያለው ልብ ይበል የሚያሰኝ ነው፤  የዋልድባ መነኮሳት አባቶቻችን
ጠቅላይ ቤተ ክህነት አትገቡም ተብለው
መነኮሳቱ በፌደራል ፓሊስ እየተባረሩ ነው !!

 አዲስአበባ ~ የዋልድባ መነኮሳት ስቃይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በተደጋጋሚ አሰልቺውን ሩቁን መንገድ ተጉዘው ቢደርሱም አትገቡም እየተባሉ ባልበላ አንጀታቸው በአዳፋ ልብሳቸው በባዶ እግራቸው አዲስ አበባ ላይ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው !!

Friday, April 19, 2019

በቤተ ክርስቲያን ላይ የቀጠለውን ጥቃት በጥናትና በቅንጅት የሚመክት የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አደረጃጀት በየከባቢው እንዲጠናከር የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጥሪ አቀረበ

49343002_1949418621774027_5310064051697483776_n
 • ለለውጡ ጊዜ በመስጠት ትዕግሥት ብናደርግም፣ግድያና ጥፋቱ በጠራራ ፀሐይ ቀጥሏል

 • ሥልጣንን፣ ፖለቲካን፣ ቋንቋንና ወቅትን ተገን ያደረገ ትንኮሳና ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል፤

 • የጎሠኝነትና አክራሪነት ግጭቶች፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በተለየ መንገድ ጎድተዋል፤

 • ከሌሎች አብያተ እምነት ይልቅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያነጣጠሩ ናቸው፤

 • ግጭት በተነሣ ቁጥር የበቀል እና የጥላቻ መወጣጫ የምትደረገው ቤተ ክርስቲያን ናት

                                                                              ***

 • ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ክትትል ያድርግ፤ መንግሥትንም ያሳስብ

 • ለልዕልናዋ በምልዓተ ጉባኤ በአጽንዖት ይምከር፤ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ ምላሽ ይስጥ፤

 • አገር ናትና መንግሥት አደጋ ከመድረሱ በፊት ይጠብቃት፤ ስትጎዳም ፈጥኖ ይጠግናት

 • የደረሰባትን በደልና አደጋ ያጣራልን፤በሚዲያ የታገዘ የጥላቻ ዲስኩር በዐዋጅ ይከልክል፤

 • የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን አደረጃጀት በየከባቢው አጠናክረን በቅንጅት እንከላከል!
***