
- ለለውጡ ጊዜ በመስጠት ትዕግሥት ብናደርግም፣ግድያና ጥፋቱ በጠራራ ፀሐይ ቀጥሏል፤
- ሥልጣንን፣ ፖለቲካን፣ ቋንቋንና ወቅትን ተገን ያደረገ ትንኮሳና ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል፤
- የጎሠኝነትና አክራሪነት ግጭቶች፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በተለየ መንገድ ጎድተዋል፤
- ከሌሎች አብያተ እምነት ይልቅ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያነጣጠሩ ናቸው፤
- ግጭት በተነሣ ቁጥር የበቀል እና የጥላቻ መወጣጫ የምትደረገው ቤተ ክርስቲያን ናት፤
***
- ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ክትትል ያድርግ፤ መንግሥትንም ያሳስብ፤
- ለልዕልናዋ በምልዓተ ጉባኤ በአጽንዖት ይምከር፤ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ ምላሽ ይስጥ፤
- አገር ናትና መንግሥት አደጋ ከመድረሱ በፊት ይጠብቃት፤ ስትጎዳም ፈጥኖ ይጠግናት፤
- የደረሰባትን በደልና አደጋ ያጣራልን፤በሚዲያ የታገዘ የጥላቻ ዲስኩር በዐዋጅ ይከልክል፤
- የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን አደረጃጀት በየከባቢው አጠናክረን በቅንጅት እንከላከል!
***