Friday, May 17, 2019

የዋልድባ መነኮሳት አባቶቻችን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አትገቡም ተብለው መነኮሳቱ በፌደራል ፓሊስ እየተባረሩ ነው !!

ቤተክህነት ማለት የኦርቶዶክሳውያንን አቤቱታ ተቀብሎ ቢያንስ አዳምጦ ችግሮችን በመግባባት ለመፍታት መሥራት እንጂ እንዴት ደካማ መነኮሳትን በፖሊስ ሊያስባርር ይችላል ፣ ቢያንስ ችግሮችን መፍታት ባይችል እንኳን እነኚህን ትላልቅ አባቶች አገር አቋርጠው መጥተው ችግራችሁ ምንድነው ብሎ ቡራኬያቸውን ተቀብሎ ወደቦታቸው መሸኘት ሲቻል እንዲት በፖሊስ ሊያስባርር ይችላል? እጅግ አሳፋሪ ሥራ ነው በእነኚህ ትላልቅ አባቶች ላይ የደረሰው ፤ ሲሆን እንዚህ አባቶች መኩሪያዎቻችን መሆን ሲገባቸው እንዴት እንደ ምንም በፖሊስ ተገፍተው ሊባረሩ ይችላሉ ኸረ የሰው ያለህ ኸረ የፈጣሪ ያለህ ልንል ይገባናል በእውነት እነኚህ አባቶች ቀለብ ስፈሩልን ወይ ገንዘብ ተቆራጭ አድርጉልን ሊሉ እንደማይመጡ የታወቀ ነው ፤ ታዲያ የት ይሂዱ ቤተክህነቱ እንዲህ በፖሊስ ካባረራቸው የት ይድረሱ ለማንስ አቤቱታቸውን ያቅርቡ? በእውነት እኒህ አይነት ጊዜ ላይ መድረሳችን በጣም እጅግ ያሳዝናል፤ እንዴስ እንዲህ አይነት ነግሮችን የሚያገናዝብ አባቶች ጠፉ በቤተክህነቱ ውስጥ? ሰውም እግዚአብሔርም ይታዘበናል እኮ ሰው ያያል ይታዘባል እነሱ በዚህ አይነት ሁኔታ እነዚህን አባቶች ገፍተው አብረው ነገ በእነርሱ ላይ ላለመድረሱ ምን እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር አለ? በእጅጉ ያሳዝናል ያስከፋል ያማል ልቦና ይስጥልን ቤተክርስቲያን ዛሬ ድረስ በካድሬ እየተመራች እንደሆነ የሚያመለክት ነው ልብ ያለው ልብ ይበል የሚያሰኝ ነው፤  የዋልድባ መነኮሳት አባቶቻችን
ጠቅላይ ቤተ ክህነት አትገቡም ተብለው
መነኮሳቱ በፌደራል ፓሊስ እየተባረሩ ነው !!

 አዲስአበባ ~ የዋልድባ መነኮሳት ስቃይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በተደጋጋሚ አሰልቺውን ሩቁን መንገድ ተጉዘው ቢደርሱም አትገቡም እየተባሉ ባልበላ አንጀታቸው በአዳፋ ልብሳቸው በባዶ እግራቸው አዲስ አበባ ላይ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው !!


በፌደራል ፓሊስ ጫና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በር አካባቢው ልቀቁ ዞር በሉ ቢባሉም የተወሰኑት መነኮሳት በፍፁም ንቅንቅ አንልም ቢሉም የተወሰኑት መነኮሳት የዋልድባ አምላክ ይፋረዳችሁ እያሉ እያለቀሱ ወደ መንበረ ፓትሪያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመግባት ፀሎት እያደረጉ ነው ።
ከዚህ በፊት አንድ ባስ መኪና መሉ ሴት መነኮሳት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢመጡም አትገቡም ተብለው በፓሊስ ተገፍትረው ወደ ባህታች መመለሳቸውና በየጊዜው የዋልድባ ገዳም ችግር ይፈታልን ብለው የሚመጡ መነኮሳት የሚደርስባቸው በደልና ማስፈራሪያ እጅግ የተደራረበ ነው ።
•ዛሬ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ጠቅላይ ቤተ ክህነት አትገቡም ተባሉ ።
• እሺ ቤተ ክርስቲያን ለማን ነው በሯ የሚከፈተው ?? አለም በቃኝ ብለው ሀሉን ጥለው በቅድስና ለመኖር ሲሉ ለመነኑላት መነኮሳት ለሀገር ለወገን በፀሎት ለሚተጉላት በሯን የምትዘጋ ከሆነች እሺ ለማን ነው በሩ የሚከፈተው ?
• እሺ ማነውስ ስለቤተክርስቲያን ያገባኛል ብሎ መናገር የሚችለው ?? ከመነኮሳቶች በላይ አረ አምላክ ሆይ አረ የአባቶቻችንን ሰቆቃና እንግልት እስርና አፈና የሴት መነኮሳትን መደፈር አንተ መልስ ስጥ አንተ በቃ በል የተዋህዶን ፈተና አንተ አስቁምልን !!!
• ዛሬ በቀን 07/09/2011 ዓም ከጠዋቱ 1:30 አዲስ አበባ ከሁለት ቀን አስልቺ ጉዞ በኃላ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የደረሱት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ወደ ውስጥ መግባት አትችሉም ተብለው ደጅ ጠንተው እየተሰቃዩ ነው !!!
• አዎ ዛሬ ቤተክርስቲያንክ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል ዝም ብለህ ዳር ይዘህ ተመልከት እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ የእኛ ዝምታ የጳጳሳቱ ነውር በዚህ ከቀጠለ ኦርቶዶክስ የምትባል ሃይማኖት ነበረች ብለህ የምታወራበትን ክፉ ጊዜ ለቤተክርስቲያንክ እያመጣክ ነው ለመጥፋቷም ተባባሪ እየሆንክ ነው !
• የክርስቲያኖችን ሞት እና ስቃይ ላለመስማት እንኳን ጆሮዉን በጥጥ ደፍኖ በጋቢ ተከናንቦ ወደ ዉስጡ ይሸሸጋል::
• የተዋህዶ ልጆች እባካችሁን ንቁ ተኝታቹሀል መነኮሳትን ማሰቃየት ሴት መነኮሳትን መድፈር ወንዶቹን መነኮሳት በማሰር ይሔ መንግስት
የሚቀጥለው ትውልድ ገዳም ገብቶ እንዳይሞለኩስና ቤተ ክርስቲያኗን ልጆቿ እንዲሸሿት ለማድረግ ተዋህዶን የማጥፋት የ 27 ዓመት ሴራ ነው ልታስቆሙ ይገባል !
• ገዳማቶች የሊቃውንት መፍለቂያ እንዳይሆኑና የመለመሏቸውን ሶዶማዊያኖች ወደገዳሙ በማስገባት ወንዶች መነኮሳትም እንዲደፈሩ ቅዱሱን ቦታ ለማርከስና ገዳሙ አስጠላን በነውር ተጨማለቀ ብለው እንዲሸሹና የቤተክርስቲያኗን የወደፊት ዕድገትና ለሐዋርያዊ ተልዕኮው ተተኪ ትውልድ እንዳይኖራት ከምንጩ ለማድረቅ ተዋህዶን አከርካሪዋን ለመስበር የተሰራ ስውር የፓለቲካ ሴራ ነው !!

ከአዲስ አበባ
Source: Abreham Ze Tewahido FB 
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤