Thursday, July 4, 2019

ዋልድባን እንታደግ ለደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም በESFNA 36th በዓል በአትላንታ ጆርጂያ

የዋልድባን እንታደግ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን በሚያዘጋጀው ፴፮ኛው ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት በየዓመቱ በመገኘት ለኢትዮጵያውያን መረጃዎችን ያደርሳል፥ ለምዕመናን የተለያዩ ጽሁፎችን በበራሪ ጽሁፍ መልክ ያደርሳል በተጨማሪ የተለያዩ ሥራዎችን ማለትም ንዋየ ቅዱሳን የጸሎት መጻሕፍት፣ መስቀሎችን ኢትዮጵያዊነትን የሚገልጹ ቲሸርቶችን፣ የእጅ አንባሮችን እና የተለያዩ ሥራዎችን ይዞ በመቅረብ ለምዕመናን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያን መረጃዎችን ያዳርሳል በዚህ በተቀደሰ ተግባር ላይ በመገኘት ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውን እንዲሁም ገንዘባቸውን በመጠቀም ለገዳሙ ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት ድጋፍ እና እርዳታዎችን ለማድረግ የሚተባበሩትን ሁሉ በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን ሥራቸውን ሁሉ ይባርክ እያልን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም ብሎም በገዳማውያኑ ስም ምስጋናችን ለማቅረብ እንወዳለን።


በተለይ ዘንድሮ በዚህ ፴፮ኛው በዓል ላይ ልንሠራ ያሰብነው ትልቅ ፕሮጀክት አለ እሱም የአሰቦት ገዳም እንደሚታወቀው በብዙ ፈተና እና ችግር ላይ እንዳለ ይታወቃል ይሄንን ታሪካዊ እና ቅዱስ ገዳም የዋልድባን እንታደግ ገዳም በበለጠ ለመርዳት እና ገዳማውያኑ በተለይ የገዳሙ አበሜኔት አባ ተክለሃይማኖት በጠየቁት እና የገዳማውያኑም እራስን የመቻል ሥራ ብንሠራ እናንተም ብታግዙን በማለት ጥያቄውን አቅርበዋል የገዳማውያኑም ጥያቄ ይልቁንም የአበሜኔቱ ምኞት ይሄ ማኅበር ቢደረግልን ብለው ያሳሰቡንን ለመሥራት የገዳማውያኑን አምላክ አጋዥ በማድረግ ለመሥራት በፈቃደ እግዚአብሔር የምዕመናንም እገዛ ተጨምሮበት ሥራውን ለመጀመር ገንዘቡን ለማሰባሰብ አንድ ብለን ጀምረናል እና በመላው ዓለም የሚገኙ ምዕመናን ይሄንን በጎ ጥሪ የሰማ በሙሉ በመላው ዓለም ያለ ምዕመናን PAYPAL በመግባት በማኅበሩ ዌብ ሳይት ማለትም www.savewaldba.org በመግባት በስተግራ በኩል በሚገኘው የፔይፓል ማጠቀሻ በመጠቀም መርዳት መደገፍ የምትችሉ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
እንደሚታወቀው የአሰቦት ገዳም ከተመሠረትበት 13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ገዳሙ ያለበት የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እጅግ ማራኪ በመሆኑ፣ ይበልጥ ደግሞ ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ከመሠረቱት ጊዜ ጀምሮ የገዳሙ ዙሪያ እና አጸዱ በሙሉ እጅግ ማራኪ እና ውብ በመሆኑ፣ ገዳማውያኑ እራሳቸውን ለመቻል ከጸሎት ባሻገር እራሳቸው የሚያበርቱበት የጓሮ አታክልት በሴቶች ገዳም በወንዶች ገዳም ደግሞ በቆሎ፣ ማሽላ እና ዘንጋዳ በማምረት ለዳቤ እና ለገዳሙ ፍጆታ የሚሆነውን የሚያመርቱበት የእርሻ ቦታ በመኖሩ፣ አካባቢው በሙሉ የሚኖሩት ኢአማናውያን በመሆናቸው የችግሮቹ መጠን እጅግ ውስብስብ ያለ ነው፥ ገዳማውያኑ በተለያየ ጊዜ ለክልሉ መንግሥት ተደጋጋሚ እርዳታ ደህንነታችው እጅግ አስጊ እየሆነ በመምጣቱ ተደጋጋሚ ሙከራም ቢያደርጉ አጥጋቢ ውጤት ወይም መልስ ለማግኘት አልተቻለም፥ ገዳማውያኑ የአምልኮ ቦታቸውን ጠብቀው ስብሃተ እግዚአብሔር የሚያደርሱበት ቦታ ተከብሮ እንዲኖር ፍላጎታቸው ነው፥ 1984 .. የደረሰው ዓይነት እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት እንዳይፈጸምባቸው በእጅጉ ይሰጋሉ ሥጋታቸው ግን ከአምልኮተ እግዚአብሔር አልገታቸውም፣ ለመኖር ደግሞ ከጸሎት እና ከስግደት በሚተርፋቸው ጊዜ እርሻ እያረሱ እራሳቸውን እየደገፉ ገዳማውያኑን በምግብ እራሳቸውን ማስቻል ትልቅ ሥራ በመሆኑ እኛም ይበል ብለናል።
እንግዲህ የደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እና እንደ እኛ ምኞት ብሎም እንደ ገዳማውያኑ ፍላጎት በዚህ በያዝነው ዓመት ለገዳማውያኑ የሚጠቀሙበት አንድ ፕሮጀክት ታስቧል፥ ፕሮጀክቱም በፈቃደ እግዚአብሔር ገዳማውያኑ የሚያመርቱትን የዘንጋዳ፣ የማሽላ እና የበቆሎ ምርት ምርቱን ከገለባው ከለዩ በኃላ የበቆሎውን ቆረቆንዳ እንዲሁም የበቆሎውን፣ የማሽላውን እና የዘንጋዳውን አገዳ ወይም ተረፈ ምርት ወደ ከብቶች መኖ ምግብ የሚቀይር (processing machine) በዚህም ከብቶችን በማርባት እና በማደለብ ለተጠቃሚዎች በመሸጥ እና ብሎም ለገዳሙ ለበዓል የሚሆኑ የእርድ ከብቶችን ለመሥራት ፍላጎት ስላላቸው እኛም ይሄንን በጎ ምኞታቸውን እውን ለማድረግ በፈቃደ እግዚአብሔር ሥራውን ለመጀመር ከደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም አሰሮተ ምንኩስናን ተቀብለው በዚያ ገዳም ያደጉ፥ ከዚያም በተለያዩ የሃገራችን ክፍል በስብከተ ወንጌል፣ በደብር አስተዳዳሪነት፣ በሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነት እና በተለያዩ ቤተክርስቲያን ባዘዘቻቸው ቦታዎች በመዘዋወር ያገለገሉ በአሁን ሰዓት በቦስተን ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል በስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ አባታችን በአትላንታ በመገኘት ለገዳሙ የሚሠራውን በመከታተል ላይ ከእኛ ጋር ናቸው እግዚአብሔር በፈቀደ ምዕመናን በዚህ ቦታ መገኘት ያልቻላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ምዕመናን የዚህ በረከት ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉ በሙሉ በድኅረ ገጽ በመግባት PayPal መክፈል ይቻላል በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥም Go Fund Me ከፍተን ለዚህ ሥራ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለገዳማውያኑ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ተባበሩን በማለት በዋልድባን እንታደግ ማኅበር እና በአባላቱ ብሎም በአሰቦት ገዳም አስተዳደር እና በገዳማውያኑ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በኳስ ሜዳም የዚህን ሥራ ለመደገፍ የሚሠሩትን ሥራዎች በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል
W ለሕጻናት በፊታቸው ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ እና ሌሎችም face paint)
W ጫማ መጥረግ ሊስትሮ
W የተለያዩ የጸሎት እና የትምህርት መጻሕፍት
W መስቀሎች ለምሳሌ የአፍሮ አይገባ መስቀል fiber glass የተሠራ ለመኪና ውስጥ ጌጥ
W የመኪና ላይ እና በውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶች stickers )
W በኢትዮጵያ ሕብረ ቀለማት ያሸበረቁ በእጅ ላይ በእራስ ላይ የሚታሰሩ የኢትዮጵያ ባንዲራዎች
W የተለያዩ በራሪ ጽሁፎች በነጻ
W የማኅበሩ የእስካሁን ጉዞ እና የተያዩ ሥራዎችን የያዘ መጽሔት በነጻ የሚከፋፈል
W የመዝሙር እና የስብከት CDዎች
W የአንገት ማህተብ የመስቀሎች
W እንዲሁም ሌሎች ስላሉን ጎብኙን የገዳማውያኑን በረከት እቃዎችን የሥጦታ ጌጦችን ገዝተው ገዳማውያኑን በሥራቸው እናግዛቸው እግዚአብሔር ደግሞ በበረከት ሊጎበኘት የታመነ አምላክ ነው።
እስከ አሁን ላደረጋችሁት እግዚአብሔር አምላክ ዘወትር እናንተ የአባቴ ቡርካን ከሚላቸው ቅዱሳን ጋር ይደምልን፣ እስካሁን እድሉን ያላገኛችሁ እና ፍላጎቱ ያላችሁ በሙሉ በተጠቀሱት መንገዶች ባለንበት ቦታ በአትላንታ ብቅ ያላችሁ ደግሞ በቦታው በመገኘት እንድራዱ በእግዚአብሔር ስም በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
ለሃገር ለወገን በጸሎታቸው ዘወትር ስብሃተ እግዚአብሔር በሚያደርሱት አባቶቻችን እና እናቶቻችን በረከታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁንልን።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር አሜንLet's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤