Friday, October 25, 2019

ከመንግሥት ጋራ የሚደረገው ውይይት ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና የሚያረጋግጥ ሊኾን ይገባል፤ “ለቋሚ ስጋታችን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ውል ላይ መደረስ አለበት”


EOTC and PM Office
 • መግለጫውን ከውይይቱ በኋላ ለመስጠት ታስቦአል፤ ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶች ይመደባሉ
***
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከሚመራው የመንግሥት ልኡክ ጋራ የሚያደርገው ውይይት፣ የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ቋሚ የጥቃት እና የተጽዕኖ ዒላማ እየኾነች ለምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት የሚደረስበት ሊኾን እንደሚገባው ተጠቆመ፡፡

Thursday, October 24, 2019

በድንገት የተቋረጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ረፋድ መግለጫ ይሰጣል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በ6 የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ተመድበው ይሰማራሉ

73108746_732445340607253_5028854134598533120_n
 • የምልአተ ጉባኤው መግለጫ እና ለባለሥልጣናቱ የሚላኩት ደብዳቤዎች ቢዘጋጁም፣ በትክክለኛ መረጃዎች ተደግፈው እስኪጠናከሩ ድረስ ለነገ ማደሩ አስፈልጓል፤
 • የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ከትላንት ጀምሮ በ6ቱ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት የተገደሉና የተጎዱ ምእመናንን፣ በጥቃት ከበባ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያንን ሪፖርቶች እና መረጃዎች እያሰባሰቡ ነው፤
 • የባሌ፣ የአርሲ፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ሸዋ፣ የሻሸመኔ እና የድሬዳዋ አህጉረ ስብከት ሓላፊዎች፣ ዝርዝር የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችን ለየክፍላቱ ሊቃነ ጳጳሳቱ እየላኩ ናቸው
 • በባሌ ሮቤ ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ብቻ፣ ስድስት ምእመናን መገደላቸውን ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል፤ አባት እና ልጅ በአሠቃቂ ኸኔታ ተገድለዋል፤ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ቦምብ ተወርውሯል፤

ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ ዐወጀ

 • አገሪቱን ለከፍተኛ ጥፋት እና ድህነት የሚዳርግ እጅግ አሳሳቢ ግጭት እየተስፋፋ ነው፤
 • የጸጥታ ኀይሎች ቅድመ ግጭትን መሠረት ላደረገ መከላከል ትኩረት እንዲሰጡ ጠየቀ፤
 • ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭት መንሥኤ ናቸው፤ ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል
 • ሶሻል ሚዲያውን ለሰላም፣ አንድነትና ተግባቦት በመጠቀም ኹሉም የበኩሉን ይወጣ፤
***
በአገራችን እንኳንስ ሊደረጉ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሣንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ ክልሎች እየተስፋፉ መኾኑ በእጅጉ ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ እንዲደረግ ዐዋጀ፤ ከመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች አንሥቶ ኹሉም አካላት እና ዜጎች በየድርሻቸው ለአገራዊ ሰላም፣ አንድነት እና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሰላም ጥሪ አስተላለፈ፡፡
ወቀተወ መገለጨ
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፡ የምልአተ ጉባኤውን የጸሎተ ምሕላ ዐዋጅ እና አስቸኳይ የሰላም ጥሪ መግለጫ በንባብ ሲያሰሙ

Thursday, October 17, 2019

ጾመ ጽጌ የእመቤታችን ስደቷን ልጇን እና ወዳጇን ይዛ የተቀበለችው መከራ የምናስብበት

Image result for የቅድስት ድንግል ማርያም ስደትጽጌ ጾም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያሉ አርባ ቀናት ዘመነ ጽጌ (ወርሃ ጽጌ) እንደሚባሉ ይታወቃል። የቤተክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገስት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል ። “ጾምስ በታወቀው ዕለት ፣በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው። ይህም ኃጢአቱን ለማስተስረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ህግን ለሰራለት  እየታዘዘ፤ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ፤ ሥጋም ለነባቢት ነፍሥ ትታዘዝ ዘንድ ነው” /ፍት.ነገ.ፍት.መን.አንቀጽ 15፥564/። 

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው። ለፈቃደ ሥጋም  መንፈሳዊ ልጓም ነው። ሰው ፈቃደ  ሥጋን እየገታ ነፍሱን  የሚያለመልምበት ስንቅ ነው። “ጾም ቁስለ ነፍስን የምፈውስ ፣ ኃይለ  ፍተዎትንም የምታደክም ፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፣ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣የጽሙዳን ክብራቸው ፣የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው ፣የጸሎት ምክንያት/እናት/ የእንባ መገኛ ምንጭ፣አርምሞን የምታስተምር፣ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።/ማር ይስሐቅ አንቀጽ 4 ምዕራፍ 6/

Wednesday, October 9, 2019

እነቀሲስ በላይ መኰንን “የምንጠይቀው ይቅርታ የለም” አሉ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የክሕደት ድርጊታቸውን በጽኑ አወገዘ፤ በሕግ እንዲጠየቁ ወሰነ!

69677888_1657044637765158_1035298022705070080_n
ከኦሮሞ ሕዝብ አብራክ ተገኝተው፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ ሳይኾን፤ ለሀገር አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ነፃነት ሰማዕት  የኾኑትን፤ ዛሬም ለክልሉ ሰላም እና አንድነት ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አባቶችን፣ የቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችንና መዋቅሮችን አገልግሎት ፈጽሞ የካደ አድራጎት በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ እያወገዘ፣ እየተሳተፉ ያሉት ግለሰቦች እና ቡድኖች ከዚህ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
~~~
 • ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና እና ፈቃድ ውጪ አዲስ መዋቅር ፈጥረው መግለጫ መስጠታቸው አግባብ አለመኾኑን አምነው ይቅርታ ለመጠየቅ፣ ከሌሎች የኮሚቴ አባላት ጋራ ተወያይተን እንመለስ፤ ብለው በጠየቁት መሠረት፣ ለዛሬ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 2፡30 ቢቀጠሩም፣ በዕለቱ የኮሚቴው ዋና ተጠሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን አልተገኙም
 • ኹለት የኮሚቴው አባላት ብቻ፣ ከተሰጣቸው ሰዓት አሳልፈው ከመምጣታቸውም በላይ፣ ኹለቱ ግለሰቦች በጽሑፍ በአቀረቡት ምላሽ፣ በሕገ ወጥ አቋማቸው እንደሚጸኑ ገልጸዋል፤
 • በመኾኑም፣ የግለሰቦቹ እንቅስቃሴም ኾነ “የኦሮሞ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት” ተብሎ የተጠቀሰው አደረጃጀት፣ ሕጋዊ ዕውቅና እንደሌለው መላው ካህናት እና ምእመናን አውቀው፣ የግለሰቦቹን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ በመቃወም እና በቀደመው አንድነታቸው ጸንተው፣ ቤተ ክርስቲያናቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲጠብ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል፤
 • ምንም ዓይነት ሕጋዊ ውክልናም ኾነ ከሕግ የመነጨ ሥልጣን ሳይኖራቸው፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ከሕግ የመነጨ ሥልጣን በመጋፋት፣ የቤተ ክርስቲያንን ዓርማ እና ማኅተም እንዲሁም መጠሪያ ስያሜ መጠቀም የማይችሉ በመኾናቸው፣ መንግሥት አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምት እንዲወስድባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡
***

Friday, October 4, 2019

በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” ጸሐፊ “መምህር አባ ገብረ እግዚአብሔር” ወደ ዋልድባ አበረንታንት መግባት ውዝግብ እያስነሳ ነው

 በላፈው ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ውዝግብ ከሚያስነሱ ጽሁፎች መካከል አንደኛው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” በተሰኘ ርዕስ በአባ ገብረ እግዚአብሔር ተጽፎ የተሰራጨው መጽሐፍ አንደኛው ነው “ የምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት መጽሐፍ ውግዘት” ሙሉውን ለማየት ይሄን ይጫኑ ፤ በመጽሐፉ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን አስተምህሮ የሚያፋልስ እና እጅግ ጽርፍ የተሞላበት መጽሐፍ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በታህሣስ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓም (12/11/2005) በብፁዕ አቡነ ማቲዎስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤው መጽሐፉም ጸሐፊውም ተወግዘው እንደተለዩ ይታወቃል፤