Thursday, October 24, 2019

በድንገት የተቋረጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ረፋድ መግለጫ ይሰጣል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በ6 የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ተመድበው ይሰማራሉ

73108746_732445340607253_5028854134598533120_n
  • የምልአተ ጉባኤው መግለጫ እና ለባለሥልጣናቱ የሚላኩት ደብዳቤዎች ቢዘጋጁም፣ በትክክለኛ መረጃዎች ተደግፈው እስኪጠናከሩ ድረስ ለነገ ማደሩ አስፈልጓል፤
  • የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ከትላንት ጀምሮ በ6ቱ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት የተገደሉና የተጎዱ ምእመናንን፣ በጥቃት ከበባ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያንን ሪፖርቶች እና መረጃዎች እያሰባሰቡ ነው፤
  • የባሌ፣ የአርሲ፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ሸዋ፣ የሻሸመኔ እና የድሬዳዋ አህጉረ ስብከት ሓላፊዎች፣ ዝርዝር የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችን ለየክፍላቱ ሊቃነ ጳጳሳቱ እየላኩ ናቸው
  • በባሌ ሮቤ ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ብቻ፣ ስድስት ምእመናን መገደላቸውን ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል፤ አባት እና ልጅ በአሠቃቂ ኸኔታ ተገድለዋል፤ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ቦምብ ተወርውሯል፤
  • ብፁዕነታቸውን ጨምሮ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሥራ አስኪያጆች በሚደርሷቸው መረጃዎች እና ሪፖርቶች በእጅጉ የተበሳጩትንና “ዛሬውኑ ከልጆቻችን ጋራ መሥዋዕት እንኾናለን የሚሉ አባቶችን ለማረጋጋት ምልአተ ጉባኤው በእጅጉ ተቸግሮ ነበር፤ በዚኹ ስሜት ውስጥ የነበሩት ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስም ባጋጠማቸው የነስር መታወክ ስብሰባውን ለመምራት ተቸግረው እንደ ነበር ተመልክቷል፤
  • ምልአተ ጉባኤው፣ በዚኽ መንፈስ ስብሰባውን ለመቀጠል እንደሚቸገር በመመዘን፣ ትላንት ከአጸደቃቸው 17 አጀንዳዎች መካከል፣ ጊዜ የማይሰጡትንና አስቸኳይ ውሳኔ የሚሹትን(እንደ በጀት ማጽደቅ የመሳሰሉትን) ብቻ ለይቶ ለመነጋገርና ሌሎቹን ለማሳደር፣ መደበኛ የጥቅምት ስብሰባውንም ለማቋረጥ ተስማምቷል፤
  • ምልአተ ጉባኤው፣ የነገ ረፋዱን መግለጫ ከመስጠትና ደብዳቤዎችን ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ከማድረስ ባሻገር፣ በስም በተጠቀሱት የባሌ፣ የአርሲ፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ሸዋ፣ የሻሸመኔ እና የድሬዳዋ አህጉረ ስብከት፣ በየክፍላቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶችን እንደሚመድብ ተጠቁሟል፡፡
Source: haratewahido
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤