Friday, October 4, 2019

በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” ጸሐፊ “መምህር አባ ገብረ እግዚአብሔር” ወደ ዋልድባ አበረንታንት መግባት ውዝግብ እያስነሳ ነው

 በላፈው ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ውዝግብ ከሚያስነሱ ጽሁፎች መካከል አንደኛው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” በተሰኘ ርዕስ በአባ ገብረ እግዚአብሔር ተጽፎ የተሰራጨው መጽሐፍ አንደኛው ነው “ የምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት መጽሐፍ ውግዘት” ሙሉውን ለማየት ይሄን ይጫኑ ፤ በመጽሐፉ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን አስተምህሮ የሚያፋልስ እና እጅግ ጽርፍ የተሞላበት መጽሐፍ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በታህሣስ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓም (12/11/2005) በብፁዕ አቡነ ማቲዎስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤው መጽሐፉም ጸሐፊውም ተወግዘው እንደተለዩ ይታወቃል፤የዚህ አወዛጋቢ መጽሐፍ ጸሐፊ ዋልድባን እንታደግ በ March 30, 2014 ለንባብ በቅቷል የመጽሐፉ ጸሐፊ የሆኑት ሰው “አባ ገብረ እግዚአብሔር” ወደ ዋልድባ አበረንታንት መመለሳቸው እና በተለይ ደግሞ የቤተ ጣዕመ አባቶች ተቀብለው ማስቀመጣቸው በገዳሙ ውስጥ የነበረው ልዩነት ይበልጥ እያካረረው ይገኛል፤ በዋልድባ አበረንታንት ውስጥ ሁለት የተለያዩ ሃሳብ ያላቸው አባቶች በልዩነት እንደሚኖሩ ይታወቃል እነሱም ቤተ ሚናስ እና ቤተ ጣዕመ ክርስቶስ በመባል ይታወቃሉ፤ የቤተ ሚናስ አባቶች አብዛኛዎቹ የዋልድባን ገዳም መታረስ እና መንግሥት እየወሰደ ያለውን የገዳሙን ማፍረስ ሥራ የሚቃወሙ ብዙ አጽዖተ መከረን የተቀበሉ፣ የታሰሩ፣ የተገደሉ እንዲሁም የተሰደዱ መነኮሳት ያሉበት ቦታ ሲሆን፤ በአንጻሩ ደግሞ የቤተ ጣዕመ ክርስቶስ ማሕበር ደግሞ የመንግሥት ተወካዮች ያሉበት ለመሣሌ “አባ ገብረ ሕይወት መስፍን” ወይም “ሻምበል” በመባል የሚታወቁ መነኮሳት ያሉበት እና አብዛኛውን ጊዜ መንግሥት የሚፈልገውን ነገር እንዲደረግ ግፊት የሚያደርጉ እና ለገዳሙ መፍረስ ብዙም ግድ የሌላቸው አብዛኛዎቹ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የገዳሙ አባላት ናቸው፤ በዚህ ቦታ ላይ ነው አባ ገብረ ክርስቶስ ከተወገዙ ከ ፯ ዓመት በኃላ ብቅ በማለት እንደ እንግዳ መነኮስ ሆነው የተከሰቱት፤ የቤተ ጣዕመ ክርስቶስ አባቶችም ምንም ችግር የለም ብለው በመቀበል በልዩ መስተንግዶ ማስቀመታቸው አብዛኛውን የቤተ ሚናስ አባቶችን በማስከፋቱ እና ቤተክርስቲያን ያወገዘችውን ሰው ወደ  ገዳም መምጣት ለሌላ ተልዕኮ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋታቸውን አጠናክሯል በዚህም ብዙ ውዝግብ በቦታው ላይ መነሳቱን ከገዳሙ በደረሱን እማኞች ለመዳት ችለናል።

ለብዙ ዓመታት የዋልድባ አበረንታንት ዘቤተሚናስ ገዳም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ቤተክህነት ተደጋጋሚ ውትወታዎችን ማድረጋቸው ያታወሳል፤ በተለይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ዘመን ሰሚ ሳያገኝ ጆሮ ዳባ ልበስ በሚል ሰሚና ተመልካች አጥቶ የነበረው ይሄ የመንፍቅና መጽሐፍ ጸሐፊው እራሳቸውን “መምህር አባ ገብረ እግዚአብሔር አብርሃ አክሱማዊ ውሉደ ዘሳሙኤል” በሚል ስም  የጻፉት ይሄ መጽሐፍ በብዙ ሊቃውንት ተመርምሮ በውሥቱ ብዙ የክህደት ትምህርቶች የተካተቱበት እንደሆነ ይነገራል፤ መጽሐፉ በርዕሱ እንደሚናገረው “ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” የምስጢረ ሥላሴን የሚተነትን መጽሐፍ ሲሆን በመጽሐፉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሆነውን ሥላሴዎች አንድም ሦስትም ናቸው የሚለውን ምስጢረ ሥላሴ የሚያፋልስ አስተምህሮ የሰፈረበት መጽሐፍ ነው፤ ይህንንም መጽሐፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ሊያወግዙት እንዲህ አይነት እንግዳ አስተምህሮ የሚያመጡትን በሙሉ በሕግ አምላክ ልንላቸው ይገባል። 

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤