Tuesday, April 14, 2020

በኢትዮጵያ ታላቅ መናወጥ ይመጣል በሙሉጌታ ውዱ ከሦስት ዓመት በፊት የተነገረ

በኢትዮጵያ ታላቅ ነውጥ እንደሚመጣ አቶ ሙሉጌታ ዘርፉ ውዱ ከሦስት ዓመት በፊት በሕይወት እያለ ተናግሮ ነበር፥ በኢትዮጵያ ይሄ ነውጥ የሚመጣው በኢትዮጵያ ላይ እጆቻቸውን በሚያነሱ ሃይሎች እንደሆነ እና ይሄም ለብዙ ሃገሮች እና ሕዝቦች ፍጅት እንደሚያመጣ ተናግሮ ነበር፥ በተለይ ምዕራባውያን በሚያደርጉት ጣላቃ ገብነት ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ ሕዝቦቿን ለመበታተን ሃገሪቱን ወደ ፍጅት ለመውሰድ የሚጣደፉ ሊጠነቀቁ እንደሚገባ በግልጽ አማርኛ አስቀምጦታል፥ በተለይም በዘር እና በሃይማኖት በሀገረ ውስጥ ፍጅት ለማምጣት የሚጣደፉትን በሃይማኖታቸው ላይ ክህደት እየፈጸሙ እንደሆነ ይናገራል፥ ታዲያ ከሦስት ዓመት በፊት የተነገረው እውን እየሆነ አይደለም፥ አንባቢ ሆይ ልብ ብለህ አድምጥ፤ ተናጋሪ ሆይ በዝግታ ተንፍስ ተብሎ እንደተጻፈ ሁሉም የሚናገረውን እና የሚለውን ልብ ሊለው ሊያጤነው እንደሚገባ የሚያስታውስ ነው፥ በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እጆቻችሁን ያነሳችሁ በሙሉ፥ እነዚህ የተነሱ እጆች እንዳይቆረጡ አስተውሉ ይላል፤ እስቲ በተመስጦ እንስማው፥ ዘወትር ሐሙስ በጉባኤ ለመሳተፍ የምትፈልጉ በሚከተሉት ቁጥሮች በጉባኤ ለመታደም ይቻላል፤ የዚያ ሰው ይበለን Dial:1-848-220-3300 Pass Code: 3760937# ዋልድባን እንታደግ ©SaveWaldba2020
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤