Saturday, May 30, 2020

መጋቢ አዕላፍ ሥንታየሁ ደምስ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፪ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፈው የዋልድባን እንታደግ መደበኛ ጉባኤ በሐሙስ ግንቦታ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓም በመጋቢ አዕላፍ ሥንታየሁ ደምስ “. . .ወደ ሰማይ እየተመለከታች ሁ ፥ ለምን ቆማችኍል . . ." የሐዋርያት ሥራ ፩ ፥ ፲፩ በሚል ያስተላለፉት ትምህርት እንደሚከተለው ቀርቧል፥ እንድንማርበት በሕይወታችንም እንድንጠቀምበት ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን እና በየሳምንቱ የሚተላለፈውን ትምህርት ለመከታተል ቢፈልጉ ሐሙስ ከ9:00 PM ጀመሮ በዋሺንግተን አቆጣጠር ይቀርባል፤ የሚከተሉትን ቁጥሮች በመጠቀም የጉባኤው ታዳሚ ይሁኑ፥ ዘወትር ሐሙስ ከ9:00 PM EST ጀምሮ ይተላለፋል Dial: 1(848)220-3300 Passcode: 376 0937#
https://www.instagram.com/kiduswaldba/ ዋልድባን እንታደግ ዓለምአቀፈ ትብብር ግንቦት ፳፻፲፪ ዓም
©SaveWaldba2020
 Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, May 24, 2020

ቤተ ክርስቲያን ለምታሳድጋቸው ችግረኛ ሕፃናት ድርጅቱ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

  • በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሳቢያ የበጎ አድራጊዎች ርዳታ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል
  • የመርጃ ማዕከሉን በግማሽ ቀንሷል፤ ከ39 ሺሕ በላይ ሕፃናትንና ቤተሰቦችን እየረዳ ነው፤
  • ከ1965 ዓ.ም. ጀምሮ 42ሺሕ ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር በሚጠቅሙ ሞያዎች አሰማርቷል፤
  • በዐቅሙ ተጠናክሮ ተልእኮውን ይቀጥል ዘንድ፣ ሥራ አስኪያጁ የርዳታ ጥሪ አቅርበዋል፤
  • የምግብ ግብዓቶች፣ የጽዳት፣ የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡
***
logo
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት፣ የኮሮና ቫይረስ ባሳደረው ተጽዕኖ ሳቢያ ችግር ውሰጥ በመግባቱ፣ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ አልባ ሕፃናት እና ችግረኞች ድጋፍ ጠየቀ፡፡
ድርጅቱ ከተቋቋመበት 1965 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በአገራችን የተለያዩ ከባቢዎች፣ 36 የሕፃናት መርጃ ማዕከላትን በመክፈት፣ 42 ሺሕ ያኽል ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር እና ለወገን በሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ሞያዎች ላይ አሰማርቷል፤ ጠቃሚ ዜጎች እንዲኾኑም አድርጓል፡፡

Saturday, May 23, 2020

መምህር አቡኑ ማሞ ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ፳፻፲፪ ዓም


ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፈው የዋልድባን እንታደግ መደበኛ ጉባኤ በሐሙስ ግንቦታ ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓም በመምህር አቡኑ ማሞ “. . .በረከተ በጻድቃን እራስ ላይ ነው . . ." ምሣሌ ፲ ፥ ፮ በሚል ያስተላለፉት ትምህርት እንደሚከተለው ቀርቧል፥ እንድንማርበት በሕይወታችንም እንድንጠቀምበት ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን እና በየሳምንቱ የሚተላለፈውን ትምህርት ለመከታተል ቢፈልጉ ሐሙስ ከ9:00 PM ጀመሮ በዋሺንግተን አቆጣጠር ይቀርባል፤ የሚከተሉትን ቁጥሮች በመጠቀም የጉባኤው ታዳሚ ይሁኑ፥ ዘወትር ሐሙስ ከ9:00 PM EST ጀምሮ ይተላለፋል Dial: 1(848)220-3300 Passcode: 376 0937# https://www.facebook.com/savewaldba/ https://www.facebook.com/KidusWaldba https://www.youtube.com/savewaldba https://www.instagram.com/kiduswaldba/ ዋልድባን እንታደግ ዓለምአቀፈ ትብብር ግንቦት ፳፻፲፪ ዓም ©SaveWaldba2020

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Wednesday, May 13, 2020

በወረርሺኙ ተጽዕኖ: የቤተ ክርስቲያን ቤቶች ኪራይ እየተጠና ቅናሽ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፤ ስብሰባውን አጠናቀቀ፤ ነገ ረፋድ መግለጫ ይሰጣል

  • በተስፋ ልኡክ ዐቢይ ግብረ ኃይል የተከፈቱ ሦስት የድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንቶች፣ ለተቸገሩ አብያተ ክርስቲያን ድጎማ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፤
  • ገዳማት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣ ዐቅም የሌላቸው አድባራት፣ የሕፃናት እና አረጋውያን መርጃዎቻችን፣ ቤተ ክርስቲያንንን የተጠጉ ነዳያን በቅደም ተከተላቸው ተለይተዋል
  • ለደረቅ ምግቦች እና ለጽዳት ግብኣቶች መግዣ 4.2 ሚሊዮን ብር፣ ከልማት ኮሚሽንና ከሌሎች አካላት ጋራ በመኾን ለ51 ገዳማት ተደልድሎ ተግባራዊ በመኾን ላይ ነው፤
  • ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መቀጠል ላሳለፈው ውሳኔ ውጤታማ አፈጻጸም፣ የአህጉረ ስብከት ክትትል ወሳኝነትን አሥምሮበታል፤
***

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የፀረ ኮቪድ-19 ተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት

  • አህጉረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያንንና ዝቅተኛ አቅም ያላቸውን የከተማ አድባራት፣ ከካዝናቸው እንዲደጉሙ ሐሳብ አቅርቧል
***
የኮሮና ቫይረስ/ኮቪድ-19 ወረርሺኝ፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ደረጃ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ እና ለመከላከል ይቻል ዘንድ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤት ደረጃ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል፣ ካለፈው መጋቢት አጋማሽ አንሥቶ ሲያከናውን የቆየውን ተግባር ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቧል፡፡
በስምንት ዐበይት ነጥቦች ተለይቶ እና በ14 ገጾች ተጠናቅሮ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በፊት የቀረበው ሪፖርቱ፣ ግብረ ኀይሉ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመበት ካለፈው መጋቢት 12 ጀምሮ በማዕከል እና በአህጉረ ስብከት በየዘርፉ የተከናወኑ ወረርሺኙን የመከላከል ተግባራትን አትቷል፡፡