Sunday, May 24, 2020

ቤተ ክርስቲያን ለምታሳድጋቸው ችግረኛ ሕፃናት ድርጅቱ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

  • በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሳቢያ የበጎ አድራጊዎች ርዳታ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል
  • የመርጃ ማዕከሉን በግማሽ ቀንሷል፤ ከ39 ሺሕ በላይ ሕፃናትንና ቤተሰቦችን እየረዳ ነው፤
  • ከ1965 ዓ.ም. ጀምሮ 42ሺሕ ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር በሚጠቅሙ ሞያዎች አሰማርቷል፤
  • በዐቅሙ ተጠናክሮ ተልእኮውን ይቀጥል ዘንድ፣ ሥራ አስኪያጁ የርዳታ ጥሪ አቅርበዋል፤
  • የምግብ ግብዓቶች፣ የጽዳት፣ የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡
***
logo
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት፣ የኮሮና ቫይረስ ባሳደረው ተጽዕኖ ሳቢያ ችግር ውሰጥ በመግባቱ፣ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ አልባ ሕፃናት እና ችግረኞች ድጋፍ ጠየቀ፡፡
ድርጅቱ ከተቋቋመበት 1965 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በአገራችን የተለያዩ ከባቢዎች፣ 36 የሕፃናት መርጃ ማዕከላትን በመክፈት፣ 42 ሺሕ ያኽል ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር እና ለወገን በሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ሞያዎች ላይ አሰማርቷል፤ ጠቃሚ ዜጎች እንዲኾኑም አድርጓል፡፡የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ሶምሶን በቀለ ለኢ.ቴቪ. እንደተናገሩት፣ ከበጎ አድራጊዎች የሚገኘው ርዳታ በመቀነሱ፣ 36 የሕፃናት መርጃ ማዕከላቱን ወደ 18 በመቀነስ፣ በአኹኑ ወቅት 6ሺሕ 620 ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን በቀጥታ፣ 32ሺሕ 530 ችግረኛ ቤተሰቦችን ደግሞ በተዘዋዋሪ፣ በጠቅላላው 39ሺሕ 150 ወገኖችን እየረዳ ይገኛል፡፡
በአኹኑ ወቅት ችግሩ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ተባብሶ፣ ድርጅቱ በሥሩ የሚረዳቸው ሕፃናት እና ችግረኛ ቤተሰቦች አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ገቢ እና ግብዓት በማሰባሰቡ ሥራ፣ ኹሉም የበኩሉን እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡

ለድርጅቱ መጠነኛ ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙት፥ በአሜሪካ፣ በጀርመን፣ በቆጵሮስ፣ በሀንጋሪ እና በኤዥያ የሚገኙ በጎ አድራጊ ተቋማት፣ በአገራቸው እየተስፋፋ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ርዳታቸውን ሊያቋርጡ ወይም ሊያዘገዩ ይችላሉ ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ በዚኽም ድርጅቱ፥ የገንዘብ፣ የምግብ እና የንጽሕና መጠበቂያ ግብዓቶችን ከተለያዩ አካላት እና በጎ አድራጊዎች ይጠብቃል፤ ብለዋል፡፡
Kesis Samson Bekele
ሥራ አስኪያጁ ቀሲስ ሶምሶን በቀለ
የበጎ አድራጎት ልገሳዎችን በቀላሉ ለመሰብሰብ እንዲያስችል፣ ዐድዋ ድልድይ አቅራቢያ(ከሲግናል ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ) ባለው እና ድርጅቱ በሚያስተዳድረው የምግባረ ሠናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ ኹኔታዎችን አመቻችተው በመጠባበቅ ላይ እንደኾኑ ገልጸዋል፡፡ በገንዘብ ለመርዳት ለሚፈልጉም፣ በድርጅቱ የባንክ አድራሻ እንዲሁም በ6650 A ብለው በመላክ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ ሥራ አስኪያጁ ቀሲስ ሶምሶን በቀለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


📢 የሚፈለጉ የርዳታ ዓይነቶች


ምግብ፡-
የጤፍ ዱቄት፣ አተር ክክ፣ ሽሮ፣ የዳቦ ዱቄት፣ ማካሮኒ፣ ስኳር፣ ሻይ ቅጠል፣ ዘይት፣ ምስር ክክ፣ በርበሬ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ጨው፤


የጽዳት_ዕቃዎች፡-
ሳሙና፣ ኦሞ፣ አልኮሆል፣ ሳኒታይዘርመድኃኒት_እና_የሕክምና_መሣሪያዎች፡-
አልኮሆል፣ የፊት ጭምብል፣ ጓንት፣ ሕይወት አድን ንጥረ ነገር (ORS)… ወዘተ.


💵 በገንዘብ_ለመርዳት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥላሴ ቅርንጫፍ

🏛 ሒሳብ_ቁጥር
1000010870546
ስዊፍት_ኮድ- CBETETA
ኤስ_ኤም_ኤስ_ኮድ፡-
6650 A (3.00 ብር ብቻ)
————————————


📢  ለበለጠ_ማብራሪያ፤
ስልክ ቁጥር፡- +251-111-232754
ወይም +251- 911 – 226147
ፋክስ ቁጥር፡- +251-111-232755‚
✉︎ ፖ.ሣ.ቁ. 30269
ኢ.ሜይል፡- eoccfaomainoffice@yahoo.com

 Source: ሐራ ዘተዋሕዶ

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤