Thursday, October 29, 2020

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እና የሽማግሌ ቡድኑ ሰብሳቢ ላእከ ሰላም ባያብል ሙላቴ፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና ስለተደረሰበት ስምምነት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

 • “ጥያቄአችን ከአስተዳደር ችግር የመነጨ እንጂ ሃይማኖታዊ አልነበረም፤ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ናት አሸናፊዋ፤ ቤተ ክርስቲያን አሸናፊ ከኾነች ኹሉም አሸናፊ ነው፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ እና በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ሥር ኾነን አገልግሎታችንን እንቀጥላለን፤ ሕዝባችንን እናገለግላለን፤ ያሳዘነውን እናስደስታለን፤
 • እኛ የቤተ ክርስቲያን ከኾን፣ የኦሲኤን ቴሌቪዥን ጣቢያም የቤተ ክርስቲያን ነው፤ ቤተ ክርስቲያን፥ ኹለት ሦስት ብቻ ሳይኾን ብዙ ያስፈልጋታል፡፡”

/ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን/

Saturday, October 24, 2020

መልአከ ገነት ዲበኩሉ በላይ

ሰበር ዜና – ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!

 • የሕግ ባለሞያዎች፥ በሀገር ውስጥ እና በውጪ አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያን ውክልና እየተሰጣቸው ግፈኞችንና ያለስሟ እና ያለግብሯ በሐሰተኛ ትርክት ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱትን እንዲፋረዱ ወሰነ!
 • በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመሩ ኹለት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ሰላም መንግሥትንና የፖሊቲካ ኃይሎችን በቀጥታ ያነጋግራሉ፤
 • ሕዝብ እየተገደለና አገር እየጠፋ ያለው፣ በፖሊቲካው ትርምስ በመኾኑ፣ በቅራኔ የተፋጠጡ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ ይማፀናሉ፤ ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ካሳን፣ ለተፈናቀሉት መመለስን፣ በሐሰት ተከሰው በእስር ለሚንገላቱት መፈታተን፣ ለተደፈሩት ይዞታዎች መከበርን እንዲያነብር መንግሥትን ይጠይቃሉ
 • የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን የመዘርጋቱ ሥራ፣ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአስቸኳይ እንዲጀመር፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቅላይ ጽ/ቤቱን አሳስቧል፤
 • ለድንገተኛ አደጋዎች እና ችግሮች ፈጣን ምላሽ እና ርዳታ የሚሰጥ አስተባባሪ አካል፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በማእከል እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል፤ በተለይ የውጪ አህጉረ ስብከት፣ ፋይናንሳዊ፣ ማቴሪያላዊ እና ሞያዊ ድጋፎችን እንዲያስተባብሩለት ተስማምቷል፡፡
Source: Hara Zetewahedo 
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት ለመከላከል በሚያስችሉ ስልታዊ አማራጮች ላይ እየተወያየ ነው

በቤተ ክርስቲያንና በምአመናን ላይ እየተባባሱ የመጡ በደሎችንና ጥቃቶችን ለማስቆም፣ ኹነኛ መፍትሔ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ የጋራ አቋም ላይ የደረሰው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ድርጊቱን ለማስቆም በሚያስችሉ ስልታዊ አማራጮች ላይ እየተወያየ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በዛሬ ጥቅምት 13 ቀን የቀትር በፊት ውሎው፣ ልዩ ልዩ ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው ከሚገኙት አህጉረ ስብከት መካከል ሦስቱ፣ በሚመሯቸው ሊቃነ ጳጳሳት አማካይነት በንባብ ያቀረቡትን ሪፖርት አድምጧል፡፡

Thursday, October 15, 2020

አጠቃላይ ጉባኤው: ለቅዱስነታቸው ራስን በራስ የመከላከል ጥሪ የጋለ ድጋፍ በመስጠት ዝግጁነቱን ገለጸ፤ ባለ15 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ዓመታዊ ስብሰባውን አጠናቀቀ

 • ቅዱስ ሲኖዶስ ግፉን ከመሠረቱ ለማስቆም፣በምልአተ ጉባኤው ጠንክሮ እንዲወያይበት ጠየቀ
 • በዓላትን በየሰበቡ የማስተጓጎል አድሏዊ አካሔድ እንዲታረምና ወጥ አሠራር እንዲበጅ አሳሰበ
 • የቅድመ አደጋ ስጋት ክትትልና መከላከል ሥርዓት እንዲዘረጋ የተወሰነው እንዲፈጸም አዘከረ
 • ቅዱስ ፓትርያርኩ ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ራሳችንን እናዘጋጅ፡፡

***

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የግፍ ጥቃት ለመግታት እና ፀራውያንን ለመቋቋም፣ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን አስተባብራ እና አደራጅታ ራስዋን በራስ ወደ መጠበቅ እንድትሸጋገር፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለአቀረቡት ማሳሰቢያ የጋለ ድጋፉን የሰጠው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ መላ አገልጋዮች እና ምእመናን ለተግባራዊነቱ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አስተላለፈ፡፡

Tuesday, October 13, 2020

ቤተ ክርስቲያን የሚዘንብባትን መከራ ለመግታትና ለመቋቋም፣ ልጆችዋን አስተባብራና አደራጅታ ራስዋን ወደ መጠበቅ እንድትሸጋገር ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

 • ከምንም ጊዜ በላይ ታጥቀን ለቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል እና ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሕይወት ዋስትና መረጋገጥ በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ነው፡፡

***

በየዓመቱ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ 39ኛ ዓመታዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስብሰባውን ዛሬ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ረፋድ ማካሔድ ጀምሯል፡፡

ዐዲስ በተገነባው እና “ጽርሐ ተዋሕዶ” ተብሎ በተሰየመው አዳራሽ በጸሎተ ወንጌል በተጀመረው በዚኹ ዓመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ መክፈቻ ላይ፣ “ወይኩን ቅኑተ ሐቈክሙ ወኅትወ መኃትዊክሙ፤ ወገባችኹ የታጠቀ፣ መብራታችኹም የበራ ይኹን፤”(ሉቃ. 12፥35)በሚል ርእስ መልእክት ያስተላለፉት ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፥ ቤተ ክርስቲያንን ከገጸ ምድር ለማጥፋት በየአቅጣጫው የተነሡ ኃይሎች በተበራከቱበት እና የሚፈጽሙባትም ግፍ እየተባባሰ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ፣ ጥቃቱን ለመመከት እና መከራውን ለመግታት፣ መላውን አገልጋዮች እና ምእመናን አስተባብሮ እና አደራጅቶ ራስን ወደ መጠበቅ አማራጭ መሸጋገር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፤ ጉባኤውም ተገቢውን መፍትሔ እንዲያስቀምጥ ኣሳስበዋል፡፡

Saturday, October 10, 2020

Saturday, October 3, 2020

ሊቀ ብርሃናት መልአክ አዲስ

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Thursday, October 1, 2020

ቀሲስ ኢዩኤል በርታ

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!